ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
+"+ # ቅዱስ_ይሁዳ ሐዋርያ +"+
=>በዘመነ ሐዋርያት # ይሁዳ ተብለው ይጠሩ ከነበሩት አንዱ የሆነው ቅዱሱ የአረጋዊው
# ቅዱስ_ዮሴፍ ልጅ ሲሆን እናቱ #ማርያም ትባል ነበር:: እናቱ ስትሞትበት ተጎድቶ የነበረ
ቢሆንም ገና በልጅነቱ # ድንግል_ማርያም አግኝታው በፍጹም ጸጋ አሳድጋዋለች::
አስተዳደጉም ከጌታችን ጋር በአንድ ቤት ነበር::
+ጌታችን እርሱንና ወንድሞቹን (ያዕቆብና ስምዖንን) ከ72ቱ አርድእት ቆጥሯቸዋል:: ቅዱስ
ይሁዳ ወንጌል ላይ ከጌታችን ጋር መነጋገሩን # ዮሐንስ ወንጌላዊ መዝግቧል:: (ዮሐ.
14:22)
+ቅዱስ ይሁዳ ከጌታችን እግር 3 ዓመት ተምሮ: መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ ብዙ
አሕጉራትን ዙሯል:: አይሁድንም አረማውያንንም ወደ ክርስቶስ ይመልስ ዘንድ ብዙ ድካምና
ስቃይን በአኮቴት ተቀብሏል:: አንዲት አጭር (ባለ አንድ ምዕራፍ) መልእክትም ጽፏል::
አጭር ትምሰል እንጂ ምሥጢሯ እጅግ የሠፋ ነው::
¤ቅዱስ ይሁዳን በዚህች ቀን አረማውያን ገድለውት በሐዋርያነቱ ላይ የሰማዕትነትን ካባ
ደርቧል::
+"+ ቅዱሳን # ዺላጦስና_አብሮቅላ +"+
=>ብዙዎቻችን መስፍኑን ዺላጦስ #መጽሐፍ_ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል
ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን:: የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት
የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል:: የዺላጦስ ታሪክ ግን እዚህ
ላይ አያበቃም::
+ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በሁዋላ ትንሳኤውን በራዕይ
ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል:: ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል:: በመጨረሻ ግን
በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ
ተሠይፏል::
=>ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት
ነው:: ጌታችንን ተከትላ: ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ: ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ
ዐርፏለች:: ዛሬ ሁለቱም ቅዱሳን ይታሠባሉ::