ስንክሳር
7.33K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
የክርስቶስ ደመ-ወዝ (ያልተቆጠረው ሕማማተ መስቀል)
ከዲ/ን አብነት ተስፉ

ክርስቶስ ማለት በደካማነት ውስጥ የተደበቀ አሸናፊነት፤ በፍርሃት ውስጥ የተሰወረ ጥብዓት፤ በትኅትና ውስጥ የተከለለ ልዕልና ነው፡፡ ይህንን እውነት መረዳት የዓለም ሞኝነት የመንፈስ ልህቀት ምልክት ነው፡፡ ይህንንም ማወቅ ለመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ጉልሕ ምስክር ነው፡፡ ለዚህም ድንቅ ማሳያ በጌቴሴማኒ የሆነው ኩነት ነው፡፡
        
‹‹ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታ መልአክ ታየው። በፍርሃትም ሲጣጣር አጽንቶ  ይጸልይ ነበር፤ ወዙም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ነበረ ›› ሉቃ 22፡42-44

ጌታችን በመጨረሻ ያደረጋቸው ነገሮች እጅግ ይገርማሉ፡፡ ‹‹የሰውን ልጅ ሊያገለግሉት አልመጣም›› እንዳለ የማበሻን ጨርቅ ይዞ ውሃውን በኩስኩስት ሞልቶ በአቧራ ያደፈውን የደቀ መዛሙርቱን እግር ለማጠብ መነሣቱ የትዕግሥቱን ጥግ ያሳያል፡፡ በዚህም ሁላችንን ‹‹እንደ ጌታችን በሰማይና በምድር የከበረ፤ እንደ እርሱም ፍጹም ራሱን ዝቅ ያደረገ የለም›› ያስብለኛል፡፡

ዳግመኛም አስቀድሞ ‹‹ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ›› (ዮሐ14፡27) ብሎ ሰላሙን፤ ‹‹ነፍሴን ስለበጎቼ እሰጣለሁ . . .›› ብሎ ነፍሱን የሰጠን ጌታ በዚህ ደግሞ ‹‹ሥጋዬን . . . ደሜን ›› ብሎ እንበላው . . . እንጠጣው ዘንድ ራሱን ሲሰጥ ማየት ምንኛ የፍቅሩን ጥግ ያሳይ ይሆን?......

መሉ ጹሑፉን ያንብቡ http://daregot.com/የክርስቶስ-ደመወዝ/

Join us @daregot @senkesar
ቅዱስ መሸነፍ

ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ በምን አይነት ሞት እነደሚሞት እንዲሁም ሞቱም ምን እንደሚያመጣ ሲያጠይቅ እነዲህ አለ። ”አመ ተለአልኩ እምድር እስህብ ኩሎ ኃቤየ … ከምድር ከፍ ከፍ ባልኩ ጊዜ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ (ዮሐ 12:32 ) አለ።

በዚህም እነደምን ባለ ሞት እንደሚሞት ገለጠ። ይኸውም ከሞቱ አስከፊነት የተነሳ ሮማዊያን ዜጎቻቸው እንዲቀጡበት የማይፈቅዱት፤ ለዕብራዊያንም ”ዘተሰቅለ በመስቀል ርጉም ውእቱ … በመስቀል የተሰቀለ የተረገመ ነው” ብለው የርግማን ምልክት ባደረጉት በመስቀል መሆኑን አስረዳ.....

ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡ http://daregot.com/ቅዱስ-መሸነፍ/

Join us @daregot @senkesar
❖~ እራቁትነት~ ❖

ዕጸ በለስን አዳም ከበላ በኋላ ዕራቁቱን እንደ ሆነ አወቀ፡፡ ዕራቁትነቱም የልብስ ብቻ ሆኖ አልቀረም፡፡ ከጸጋ ሁሉ መራቆት እንጂ፡፡ ከዔደን ገነት በመባረሩ የሰዉ ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር ዳግመኛ እንደ ቀድሞዉ ለመገናኘት  “ወዴት እንዳገኘው ምነው ባወቅሁ! ወደ ተቀመጠበትስ ስፍራ ምነው በደረስሁ!” ብሎ የሚቃትት ሆነ (ኢዮ 23፡3)፤ ለዚህም ጥያቄዉ እግዚአብሔር “በመካከላችው አድር ዘንድ መቅደስ ሥሩልኝ” (ዘጸ 25፡8) ብሎ አዘዘ፡፡

አምላኩን ቢያገኝ እንኳን “ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣ” የሚለዉ እነ ሚክያስን የሚያስጨንቅ ነበር (ሚክ 6፡6)፡፡ “አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ” ተብሎ ስለተፈረደበት “ለዚህ ለሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?” የሚለዉም ያልተፈታ ዕንቆቅልሽ ሆነበት (ሮሜ 7፡24)፡፡ በዚህም ምክንያት ካህን ይሆኑ ዘንድ ያለመሃላ የተሾሙት ካህናት እንኳን ጩሀታቸዉ ”ሰው እግዚአብሔርን ቢበድል ስለ እርሱ የሚለምን ማን ነው?” እያሉ አስታራቂ ይፈልጉ ነበር (1 ሳሙ 2፡25 )፡፡

አስቀድሞ ግን “እግዚአብሔር አዳምን ንጉሥ ካህን እና ነቢይ አድርጎ ፈጥሮታልና” መቅደስ በሆነችዉ ሰዉነቱ አንድም በመቅደስ በምትመሰለ በዔደን ገነት ያለ መካከለኛ በራሱ ክህነት ምሥጋናዉን እና ጸሎቱን ያሳርጋል ምህረትና ትዕዛዝን ይቀበላል፡፡ ከዉድቀት በኋላ ግን የሰዉነቱ መቅደስነት ቀረና መቅደስ በአንድ ስፍራ የተከለለ ህንጻ ሆነ፤ ክህነቱም ለሌዊ ብቻ በመሰጠቱ የአዳም እራቁትነት ቀስ በቀስ ተገለጠ....

ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ http://daregot.com/እራቁትነት-ለአዳም-ኃፍረት-ለክርስቶስ-ክ/

Join us @daregot @senkesar
Forwarded from Daregot Media
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይዕዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሠላም.....

ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ዲያብሎስን አሰረው፤ አዳምን ነጻ አወጣው፡፡ ሰላም! ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ኾነ፡፡”

መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንላችሁ!

Join Us https://tttttt.me/daregot
የዳረጎት ሚዲያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዲያቆን ዶክተር አቤል ኃይሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ በቆይታቸውም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ሰፊ ሃይማኖታዊና ሞያዊ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡

ቢያነቡት ለተከታዮቹ ጥያቄዎች መልስ ያገኙበታል፡-

- አሁን ያለው ሁኔታ ከከፋና ከበረታ፣ ከፍቅር አንጻር ከሕዝብ ምን ይጠበቃል?

- ኮሮና የፈጣሪ ቁጣ ነው የሚሉ አሉ፣ በአንጻሩ አይደለም ሲሉ ሳይንሳዊ ትንታኔ ብቻ የሚሰጡም ይሰማሉ፤ ሆነ ተብሎ የተፈጠረ ነው የሚሉም ይገኛሉ። በዚህ ላይ ምን ሐሳብ አለዎ?

- ጥንቃቄ ከእምነት ማነስ ጋር ይገናኛል?

- ኮሮና የጋራ ጠላት ሆኖ በጎ ነገር ያወጣልን ይሆን?

- ስለ ዳረጎት መጽሔት እናንሳና እንተዋወቃት? ምን ዓይነትስ ይዘት አላት?

- ዳራጎት ላይ የሴቶች ተሳትፎስ ምን ይመስላል?

መልካም ንባብ!

ተከታዩን ሊንክ ተጭነው ያንብቡ https://addismaleda.com/archives/11126

Join us https://tttttt.me/daregot
Forwarded from Daregot Media
ዳረጎት መጽሔት 3ኛ ዓመት ቁጥር 6.pdf
4.2 MB
ዳረጎት መጽሔት ቁጥር 6 በpdf ላላገኛችሁ ላልደረሳችሁ በጠየቃችሁን መሰረት ይኸው አቅርበንላችኋል፡፡ ታዲያ ተካፍሎ መብላት ወትሮም ባህላችን ነውና ሥጋዊ መብሉን ለሌላቸው እያካፈልን በመንፈሳዊው ደግሞ ይህችን ዳረጎታችንን ወንድም እህቶቻችን እንዲያነቧት እያካፈልን ይህንን ክፉ ጊዜ በእምነት፣ ጥንቃቄና በብልሃት እንለፈው፡፡

ለሚኖራችሁ አስተያየት @DaregotComment_bot

#Staysafe #stayhome

Join us https://tttttt.me/daregot
🙏ሚያዝያ 16

📖ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት📖

1.ቅዱስ አንቲቦስ ዘሃገረ በአርማ (ሐዋርያዊ ጳጳስና ሰማዕት)

2.ቅዱስ ሳባ ሰማዕት

📖ወርኀዊ በዓላት📖

1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)

2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)

3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም)

4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ

5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ

6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ

7.አባ ዳንኤል ጻድቅ

📜 (ዕብ. ፲፫፥፯)

"የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ:: የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው:: ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ: እስከ ዘለዓለምም ያው ነው:: ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምሕርት አትወሰዱ:: ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም:: በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና::"

@senkesar @senkesar
ቅዱስ አንቲቦስ ሐዋርያ

ቅዱስ አንቲቦስ በአርማ በምትባል ሐገር በእረኝነት (ጵጵስና) ያገለገለ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙር ነው:: ቅዱሱ ስለ ክርስቶስ መንጋ ብዙ መከራን ተቀብሏል:: በእሥር ቤት ሳለም ከቅዱስ ዮሐንስ ነባቤ መለኮት (ወንጌላዊ) ክታብ (መልእክት) ደርሶታል::

በክታቡም ከሐዋርያትና ሰማዕታት መቆጠሩን ነግሮታል:: ጊዜው 1ኛው ክ/ዘ ሲሆን ክታቧ ከእኛ አልደረሰችም:: ከቅዱስ ዮሐንስ እግር ቁጭ ብሎ በመማሩ እንደ መምሕሩ የንጽሕና ሰው ነበር:: ከብዙ ዓመታት አገልግሎት በኋላ ስለ ፍቅረ ክርስቶስ በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አልፏል::

በታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ደግሞ የዚህ ቅዱስ ስም መጠቀሱን ምስራቅ ኦርቶዶክሶች ያምናሉ:: በዮሐንስ ራዕይ 2:12 ላይ የእኛው (ግዕዙ) "ጻድቅየ መሃይምን" ሲለው የግሪኩ ግን በቀጥታ በስሙ "አንቲጳስ (አንቲቦስ) ብሎ ይጠራዋል፡፡ እርሱም በታናሽ እስያ ከነበሩት 7 አብያተ ክርስቲያናት የአንዱ (የጴርጋሞን) አለቃ የነበረ ሲሆን ሰማዕት መሆኑም በዚሁ ምዕራፍ ላይ ተጠቅሷል:: (ራዕይ 2:12-17)

ከቅዱስ አንቲቦስ በረከትን ያሳትፈን!


via Dn yordanos ababa
"በብፅዕ አቡነ ሄኖክ ላይ እየተደረገ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻና ዛቻ አሳስቦናል" (የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት)

የምዕራብ አርሲ ሀ/ስብከት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሄኖክ ላይ እየተደረገ ነው ያለውን የስም ማጥፋት ዘመቻ አወገዘ።

ሀ/ስብከቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ብፁዕነታቸውን ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ፈልገው ያልተሳካላቸው ኃይሎች በፈጠራ ወሬ ያልተናገሩትን ተናገሩ በማለት በስፋት በማኅበራዊ ሚዲያ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደከፈቱባቸው ገልጿል።

በተጨማሪም ይህ ድርጊት በንቀትና በዝምታ ማለፍ ጉዳዩን እያባባሰው እንዳለ ጠቅሶ የሐሰተኞችን አካሄድ ማጋለጥ አስፈላጊ በመሆኑ መግለጫ ማውጣቱ አስፈላጊ መሆኑን አስታውቋል።

ሀገረ ስብከቱ እውነቱን ለምዕመናን ማሳወቁንና በተለይ የዋሃን ምዕመናን በሚናፈሰው የበሬ ወለደ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዳይረበሹና በሐተኛ አልሉባልታዎች ግራ እንዳይጋቡ አሳስቧል።

ሀ/ስብከቱ ብፁዕነታቸው በዘመነ ጵጵስናቸው ያስመዘገቡት አመርቂና አኩሪ ታላላቅ ሥራዎች እንዲሁም ታሪካዊ የብፁዕነታቸውን ተግባራት ገልፆ እነዚህን "የከሰሩ የፖለቲካ ነጋዴዎች ሴራ ማጋለጡንም" እንደሚቀጥል በመግለጫው አትቷል።

Via አደባባይ ሚዲያ

@senkesar
የቤላሩስ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጥሪ
#ምንአዲስ

ቤላሩስ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ከኮሮና ቫይረስ [ COVID-19 ] ያገገሙ ምዕመኖቿ ፕላዝማ የሚባለውን የደም አይነት እንዲለግሱ ጥሪ አቅርባለች፡፡ ይህ በኮሮና ቫይረስ በጠና ለታመሙ ሰዎች ህክምና ወሳኝ መሆኑ የተነገረለት ፕላዝማ የተባለው የደም አይነት ከቫይረሱ ካገገሙ ሰዎች ብቻ የሚወሰድ ሲሆን ይህም በቻይና ውጤታማነቱ ከታየ በኋላ በቤላሩስ፣ በራሽያ እንዲሁም በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ይህን አይነቱን የህክምና ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ በኢትዮጵያ የደም ባንክ በኩል እንቅስቃሴ መጀመሯን ገልጻለች፡፡

በቤላሩስ በሚያዚያ 16 እንደተገለጸው የፕላዝማ የደም አይነትን በጠና ለታመሙ ዘጠኝ(9) ሰዎች ተሰጥቶ በስድስቱ(6) ላይ የማገገም ምልክቶች ተስተውለዋል፡፡ ይህ እስከተገለጸበት ጊዜ ድረስም በሀገሪቱ አንድ ሺ አንድ መቶ ሀያ(1,120) ከበሽታው ያገገሙ ለጋሾች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በቤተክርስቲያኗ ወገን ይህንን የደም ልገሳ መርኃ-ግብር እያስተባበረ ያለው በቤላሩስ ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የተቋቋመው የቤተክርስቲያኗ የበጎ አድራጎት እና ማህበራዊ አገልግሎት ከፍል ነው፡፡

ይጎብኙ http://daregot.com
Forwarded from Daregot Media
"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው"
ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ
@DaregotMediaComment_bot
ለምን እንታመማለን? ክፍል ሁለት
በዲ/ን አቤል ኃይሉ(ዶ/ር)

ለምን እንታመማለን ?……..ሥነ መለኮታዊ ፍለጋ

ለምን እንታመማለን?……….ሳይንሳዊ ነጽሮት

ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡ http://daregot.com/ለምን-እንታመማለን-ሥነ-መለኮታዊ-ፍለጋና-2/
በሽታ በቅርቡ እንደሚጠፋ ታምናለህ?
በዲ/ን አቤል ኃይሉ(ዶ/ር)

አንድ ወቅት በጠዋቱ ወደ አንድ ክሊኒክ ለሥራ እየሄድኩ ሳለ መንገድ ላይ ሁለት ሰዎች አስቁመውኝ ስለመጽሐፍ ቅዱስ እናውራ ተባልኩ፡፡ እሺ ብዬ ቆምኩኝ፡፡ ‹‹በሽታ በቅርቡ እንደሚጠፋ ታምናለህ?›› አሉኝ፡፡ የእኔ መልስ የነበረው ‹‹ለምንድነው የሚጠፋው?›› ነበር፡፡ ትንሽ ገረማቸው፡፡ በሽታ እንዲጠፋ የማይፈልግ ይህ ደግሞ ማነው? ሳይሉ አልቀሩም!

ቀጠሉ፡፡ ‹‹ዓለም በበሽታ ተጨንቃላች፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ከምድር ላይ በሽታን ያጠፋልና ‹‹እንድትጽናና›› ፈልገን ነው አሉኝ፡፡ የሚቀጥለውን ምክር አዘል ቃል ተናገርኩኝ፡፡ ‹‹በሽታ ይጠፋል፤ ፍጹም ሰላም ይመጣል፡፡ ለጥ ብላችሁ ትተኛላችሁ …ወዘተ ›› እያላችሁ ሰዉን አታስንፉት፡፡ ‹‹ለምን ይጠፋል?›› እንዲህ ብዬ የመለስኩት በበሽታ መኖር ደስተኛ ሆኜ አይደለም፤ ሀሳባችው ግን አጥፊ ስለሆነ ነው፡፡ በመቀጠልም ጌታ በወንጌል ለይ ያስተማረውን ቃል አስቀመጥኩላቸው፡፡‹‹በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፡፡ነገር ግን አይዟችሁ፡፡ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለው፡፡›› ዮሐ 16÷30

ይሄ እውነት እስከጌታ ምጽአት ድረስ ይቀጥላል፡፡ ጌታ ቃል የገባልን እንዳሸነፍኩት ታሸንፋላችሁ ነው እንጂ በሽታ ፣ስቃይ አይኖርባችሁም አላለንም፡፡ ሰዎችንም ዘወትር ልናስተምራቸው የሚገባው እንዴት ማሸነፍ እንደሚችሉ ነው እንጂ በቅርቡ በሽታ ይጠፋል ብለን ላያገባት አገባሸለው ብሎ ያልሆነ ተስፋ እንደተሰጣት ሴትዮ እንዳያደርጉን ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡ http://daregot.com/በሽታና-ፈውስ/

ዳረጎትን በቴሌግራም ይከታተሉ https://tttttt.me/daregot
ሕይወቱ፡-
ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ
"ሰማዕት"

በረከታቸው ይደርብን!

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://tttttt.me/daregot
አራተኛው መንግሥት ለቤተክርስቲያን ምን ይጠቅማታል?
#ወቅታዊ
http://daregot.com/አራተኛው-መንግሥት-ለቤተክርስቲያን-ምን/
ዜና ሕይወቱ፡-
ለቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
ዛሬ ( ግንቦት 7 ) እረፍቱ ነው፡፡ እንኳን አደረሳችሁ!

ቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ https://tttttt.me/daregot
Forwarded from Daregot Media
ዜና ሕይወቱ
ለቅዱስ ያሬድ
'ማኅሌታይ'
ግንቦት 11 በዓለ ስዋሬው ነው፡፡ እንኳን አደረሳችሁ!

ለአስተያየት
👉 @DaregotMediaComment_bot

ቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ
👉 https://tttttt.me/daregot