ስንክሳር
7.33K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
የቤላሩስ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጥሪ
#ምንአዲስ

ቤላሩስ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ከኮሮና ቫይረስ [ COVID-19 ] ያገገሙ ምዕመኖቿ ፕላዝማ የሚባለውን የደም አይነት እንዲለግሱ ጥሪ አቅርባለች፡፡ ይህ በኮሮና ቫይረስ በጠና ለታመሙ ሰዎች ህክምና ወሳኝ መሆኑ የተነገረለት ፕላዝማ የተባለው የደም አይነት ከቫይረሱ ካገገሙ ሰዎች ብቻ የሚወሰድ ሲሆን ይህም በቻይና ውጤታማነቱ ከታየ በኋላ በቤላሩስ፣ በራሽያ እንዲሁም በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም ይህን አይነቱን የህክምና ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ በኢትዮጵያ የደም ባንክ በኩል እንቅስቃሴ መጀመሯን ገልጻለች፡፡

በቤላሩስ በሚያዚያ 16 እንደተገለጸው የፕላዝማ የደም አይነትን በጠና ለታመሙ ዘጠኝ(9) ሰዎች ተሰጥቶ በስድስቱ(6) ላይ የማገገም ምልክቶች ተስተውለዋል፡፡ ይህ እስከተገለጸበት ጊዜ ድረስም በሀገሪቱ አንድ ሺ አንድ መቶ ሀያ(1,120) ከበሽታው ያገገሙ ለጋሾች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በቤተክርስቲያኗ ወገን ይህንን የደም ልገሳ መርኃ-ግብር እያስተባበረ ያለው በቤላሩስ ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የተቋቋመው የቤተክርስቲያኗ የበጎ አድራጎት እና ማህበራዊ አገልግሎት ከፍል ነው፡፡

ይጎብኙ http://daregot.com