ጌታ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ከሰው ወገን እነማን ነበሩ?
- በኢየሩሳሌም በይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያሉ ሰዎች፡፡
- ኃጢአታቸውን ተናዘው ንስኃ የሚገቡ ሰዎች
- ቁጥሩ ከ12ቱ ሐዋርያት የሆነውና በመጨረሻም ሰማዕትነትን የተቀበለው ቅዱስ እንድርያስ
- ፈሪሳውያንና ሰዱቃዊያን
- ቀራጮች
- ጭፍሮች ተገኝተው ነበር፡፡
ታዲያ የዮሐንስ ትምህርት ምን ይል ነበር?
- ንስኃ ግቡ ይል ነበር፡፡
- ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል፥ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ ይል ነበር።
- ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ ይል ነበር።
- በማንም ግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ ይላቸው ነበር።
በዚህች በዮርዳኖስ በምትመሰል የጥምቀተ ባህር የምንሰበሰብ ሁሉ ዛሬም መጥምቁ ይጮሀል! ብንችል እስከመስቀሉ የምንታመን ካልሆነም የንስኃውን ድምጽ የምንሰማ እንጂ በሌላውስ አንተባበር!
@senkesar

ሞት በጥር ነሀሴ መቃብር ።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩላ?
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ይዞ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እመቤታችን
ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ የሔደው የዕረፍቷ ጊዜ መድረሱን ለማብሠር ነበር፡፡ የድል
ምልክት የሆነውን ፍሬው የተንዠረገገ የቴምር ፍሬ የሚያፈራውን ዘንባባ ይዞ ለሁለተኛ ጊዜ
እርሷ ወዳለችበት ይዞ ገብቶ ደስ ይበልሽ ሲላት አሁንም እየሰገዳና እጅ እየነሣ ነበር፡፡
ጌታችን እንዳዘዘውም "ልጅሽና ጌታሽ እናቴ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ ጊዜው ደርሷል ብሏል፡፡
ከሴቶች ተለይተሸ የተባረክሽ ቅድስት ሆይ ስለዚህም ለሁለተኛ ጊዜ ይህን መልካም
የምሥራች እነግረሽ ዘንድ ላከኝ፡፡ ብፅዕት ሆይ በምድር የሚኖሩትን ሁሉ በደስታ
እንደሞላሻቸው አሁን ደግሞ በዕረፍትሽና በዕርገትሽ ምክንያት የሰማይ ኃይላት በደስታ
ይሞሉ ዘንድ በሰማይ ያሉ ነፍሳትም ሁሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ በክብር ያበሩ ዘንድ
ምክንያት ትሆኛለሽ፡፡ ደስተኛይቱ ፍስሕት የሚል ማዕረግ ለዘላለም ተስጥቶሻልና ስታዝኝና
ስታለቅሽ በኖርሽው መጠን ደስ ይበልሽ፡፡ ጸሎቶችሽና አስተብቁዖቶችሽ በሙሉ በልጅሽ
ፊት ወደ ሰማይ ዐርገዋል፤ ስለዚህም ይህን ዓለም ትተሽው ወደ ሰማይ ትሔጅና ፍጻሜ
በሌለው የዘላለም ሕይወት ከልጅሽ ጋር ትኖሪ ዘንድ አዝዟል" ብሎ ዘንባባውንም በእጇ
ሰጣት፡፡ የነበረውን ትውፊት ሁሉ አሰባስቦና አጠናቅሮ በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በግሪክ
ቋንቋ ሕይወቷንና ተጋድሎዋን በተሻለ ሁኔታ የጻፈው መክሲሞስ ዘኢየሩሳሌም
እንደመዘገበው እመቤታችን የመልአኩን ብሥራት በሰማች ጊዜ እጅግ ተደስታ እንደ
ቀድሞው ሁሉ በፍጹም ትሕትና "እነሆ የእግዚአብሔር አገልጋዩ፤ አሁንም እንደቀድሞው
እንደቃልህ ይደረግልኝ አለችው" ይላል፡፡ ከዚህ በኋላ አሁን በዚህ ጽሑፍ የማልገልጻቸው
እጂግ ብዙ ገቢረ ተአምራት ተፈጽመዋል፡፡ እመቤታችን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የሰጣትን
ዘንባባ ይዛ በደብረ ዘይት ተራራ ሔዳ ከጸለየች በኋላ ቀድማ ትነግረው ዘንድ ትፈልገው
የነበረውን ወንጌላዊና ነቢየ ሐዲስ ንጹሕ ድንግል ዮሐንስን በደመና አምጥቶላታል፡፡
ከዚያም ልዩ የእግዚአብሔር መቅደስ ወዳደረገቻት ቤቷ ከተመለሰች በኋላ ሐዋርያትና ብዙ
ተላውያነ ሐዋርያት ድንገት አንድ ጊዜ በደመና ደረሱ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ከደመናው
ከተቀበላቸው በኋላ ወደ እርሷ ይዟቸው ገባ፡፡ ሁሉም አንድ በአንድ እየሆኑ በፊቷ እያለፉ
ተሳለሟት፤ እርሷም አነጋገረቻቸው፡፡ ከአርድእት አንዱ የሆነው ተላዌ ቅዱስ ጳውሎስ
የሆነውና ከፍልስፍና የተመለሰው የአቴናው ዲዮናስዮስ ከተገኙት አርድእት መካከል እርሱ
ቅዱስ ጤሞቴዎስና ቅዱስ ሔሮቴዎስ እንደነበሩና ቅዱስ ጴጥሮስን፤ ቅዱስ ጳውሎስንና
ሌሎቹን ሐዋርያት ስታናግራቸው በዓይኑ እንዳየና ራሱም በፊቷ አልፈው እማሔ ካደረጉት
መካከል መሆኑን ለጢሞቴዎስ በላካት መልእክት ላይ መዝግቦታል፡፡ ከዚያም በኋላ መንፈስ
ቅዱስ ወርዶባቸው ሁሉም ሐዋርያትና አርድእት መንፈስ ቅዱስ እንደሰጣቸው መጠን
ተሰምቶ የማያውቅ ልዩ ምስጋና ማቅረባቸውን መዝግቧል፡፡ ከዚህም በኋላ የተደረጉት
ተአምራት ብዙዎች ስለሆኑ በሌላ ጽሑፍ እስክምለስ ድረስ አሁንም እነርሱን ከመዘርዘር
እቆጠባለሁ። በመጨረሻም ጌታችን በሚያስፈራና በልዩ ግርማ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር
መውረዱንና እነሙሴ እነዳዊት በአንድነት ከአእላፋት መላእክት ጋር ሲዘምሩና የሰማይ
ሠራዊት በደስታ ሲጥለቀለቁ ጽዮንም ስትናወጥ ማየታቸውን በእኛ የጥር ወር በልዩ ከብር
ማርፏን የነበሩት ሐዋርያትና አርድእት ሁሉ መስክረዋል፡፡
የአካላዊ ቃልን ወደዚህ ዓለም መምጣት ማብሠር እንደተሰጠህ የድንግሊቱንም
ወደዚያኛው ዓለም መሔድ ማብሠር ድጋሜ የተሠጠህ የታመንህና የከበርክ ቅዱስ
ገብርኤል ሆይ እባክህ መልካም ነገር እያለ የራቀውን የእኛን ትውልድም ከመልካሙ ነገር
አገናኝልን፤ መልካሙን አሰማን፡፡ ከድንግሊቱና ከደስተኛይቱ እናታችን በረከትም
አድርስልን፡፡ ክብሯን ግለጥ ፤ እኛንም ፈጽመህ አማልደን።
እንግዲያውስ ቅዱሳኑን ተከትለን እኛም እየዘመርንና እያመሰገንን የሰው ዘር መመኪያ
የሆነችውን የእናታችንና የእመቤታችን የንጽሕተ ንጹሐን የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል
ማርያምን በዓለ ዕረፍት በተከበረው ትውፊታችን መሠረት እናክብር፡፡
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስና ሶርያዊ ማር ኤፍሬም የመሥዋዕቱን በግ
ያስገኘሽልን፤ እረኛችን የወልድሽልን ንጽሕት በግ ሆይ የሚሉሽ ፍጽምትና የታመንሽ አማላጅ
ሆይ በፍጹም ምልጃሽ ሁላችን አስምሪ ።
እንኳን ለበዓለ ዕረፍታ ለንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም አደረሳችሁ፡፡

በሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ ዓሥሩ የእጆቻቸው ጣቶቻቸው እንደ ፋና የሚያበሩትና
ዛሬም ድረስ መካነ መቃብራቸው ቅብዓ ቅዱስ የሚያፈልቀውን ታላቅ ጻድቅ አቡነ ዮናስን
ይወቋቸው!
አቡነ ዮናስ አባታቸው ንዋየ እግዚእ እናታቸው ኂሩተ ማርያም ይባላሉ፡፡ በኅዳር 17 ቀን
1357 ዓ.ም በሀገረ ቡር (ሀገረ መስቀል) ሚባል ተወለዱ፡፡ አቡነ ዮናስ በሕፃንነታቸው
በጎች እየጠበቁ ሳለ መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም መዝሙረ
ዳዊት ኣስተማራቸው፡፡ እርሳቸውም ይህን ዓለም ንቀው ከመነኮሱ በኋላ 150 መዝሙረ
ዳዊት በአንድ ጊዜ እየጸለዩ 3 ሺህ ስግደት ይሰግዱ ነበር፡፡ ቀንና ሌሊት ሲጸልዩም
"ጠላቂት" በሚባል ሐይቅ ውስጥ እየገቡ እስከ አንገታቸው ድረው በሐይቁ ውስጥ
ገብተው ይጸልዩ ነበር፡፡ ከተሰጧቸውም ጸጋዎች ውስጥ አንዱ 10 ጣቶቻቸው ወደ ሐይቁ
ሲገቡ ይበሩ ነበር፡፡
አቡነ ዮናስ በየቀኑ ከ5 ፍሬ "ዳዕሮ" ወይም "ዓየ" በቀር ሌላ ምግብ አይመገቡም ነበር፡፡
ከዚኽም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ኀብስተ ኣኩቴትን ጽዋ በረከት ከሰማይ
አውርዶላቸዋል፡፡ ጻድቁ እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት ወደተለያዩ ቦታዎች እየዞሩ
የተለያዩ ተኣምራት በማድረግ ሕሙማንን በመፈወስ ሙታን በማስነሣት ብዙዎችን
ከክህደት ወደ እምነት ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ከጣኦት ኣምልኮ ወደ እግዚአብሔር ኣምልኮ
መልሰዋል፡፡
ጌታችን በአምላካዊ ቅዱስ ቃሉ ‹‹ከመቃብርህ ጸበል የተቀባ የጠጣ ከኃጥያቱ ይነጻል››
የሚል ቃልኪዳን አስቀድሞ የሰጣቸው ሲሆን በዚህ ድንቅ ቃልኪዳን መሠረት ዛሬም ድረስ
ከመካነ መቃብራቸው ላይ ፈዋሽ የሆነ ቅብዓ ቅዱስ ይፈልቃል፡፡ ይህንንም በ2011 ዓ.ም
ለአንድ ወር በአክሱምና ኤርትራ የዞር ጉዞ ባደረግንበት ወቅት ወደዚህ ታላቅ ገዳም ሔደን
የጻድቁን ገዳም ተሳልመን ቅብዓ ቅዱሱን በዐይናችን አይተን በአባቶች ተቀብተን
በረከታቸውን አግኝተናል፡፡ ቅብዓ ቅዱሱ በተለይም ጆሮውንና ዐይኑን ለሚያመው ሰው
መድኃኒት ነው፡፡
አቡነ ዮናስ ይይዙት በነበረው መቋሚያ በውኃ እየታጠበ ውኃው በጣም ለታመሙ ሰዎች
እየተሰጠ በቶሎ ከበሽታቸው ይድኑበታል፣ የማይድኑም ከሆነ ቶሎ በሞት ያርፋሉ፡፡
የሚታጠቡበት ሁሉ ለድኅነት ከሆናቸው በአጭር ጊዜ ይድናሉ ወይም ለዕረፍት ከሆናቸው
ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት ያሰናብታቸዋል፡፡ አቡ ዮናስ በቁርባን ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም
በሠረገላ መንፈስ ደርሰው ያስቀድሱ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡
ኣንድ ቀን የአቡነ ዮናስ ተማሪዎቻቸው አህያ ውሃ ሊያጠጡ በሄዱበት ጊዜ ልጁዋን
ያመመባት አንዲት ሴት ‹‹አህያው የማነው/›› ብላ ጠየቀቻቸው፤ እነርሱም ‹‹የአቡነ ዮናስ
ነው›› አሏት፡፡ እርሷም በእምነት ሆና የታመመ ልጅዋን በአህያው ላይ አኑሯ (አስቀምጣ)
አህያውን በባለቤትህ ጸሎት ተማጽኜሃለሁና ልጄን እንዲያድንልኝ እለምንልሃለሁ›› ብላ
ተናገረች፡፡ ልጇም ወዲያው ከሕመሙ ዳነ፡፡ እርሷም በሌላ ጊዜ አባታችንን ስታገኛቸው
በጸሎትዎ የዳነ የእኔ ልጅ ነው›› ብላ መሰከረችላቸው፡፡
ከዕረፍታቸው በኋላ የተደረጉ በርካታ ታላላቅ ተአምራት አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ
እርሳቸው ካረፉ ከትንሽ ቀናት በኋላ በመቃብራቸው ላይ ዘይት ፈለቀ፡፡ ከዚያም በእንጨት
በተሰራ መቅጃ እየተቀዳ ወደ ትልቅ መጠራቀምያ ገብቶ ለቤተ መቅደስ መብራት በ12
ተቅዋም ተደርጎ ከዓመት እስከ ዓመት ይበራ ጀመር፡፡ ከተጠራቀመ ዘይቱም ለታመሙ
ይቀቡትና ከተለያዩ ሕመሞች ይድናሉ፡ ያዕ 5:14፡፡ ዳግመኛም ኤርትራ በሚገኙት በሌሎቹ
በአባታችን ደብር ውስጥ ከብዙ ጊዜ በኋላ በደብረ ሣህል ደብራቸውና በደብረ ጽጌ ፈለቀ፡፡
ቅብዓ ኑጉም ለታመሙ ፈውስ እየሰጠ ለቤተ መቅደስም መብራት ሆነ፡፡
ዳግመኛም ከተደረጉት ተአምራት ውስጥ አንዱ እንደ ቤተክርስቲያን ሕግጋት ጻድቁ ካረፉ
በኋላ ለጸሎትና ለኑዛዜ ሰዎች ተሰብስቦው እህል እና ውሃ ተዘጋጅቶ በነበረበት ሰዓት "በዚ
ቀን ሁሉ ሰው ተገኝቶ ያለሥጋ ዋልን›› ሲሉ ሦስት የተለያዩ ሚዳቆዎች በአቡነ ዮናስ ጸሎት
ድንገት መጥተው በሰዎቹ መሐል ተገኙ፡፡ ሰዎቹም ሚዳቆዎቹን አረደው በሉ፡፡
ጻድቁ በስማቸው የተገደሙ ገዳማት (ደብረ ድኁኃንበ-ቆሓይን፣ ደብረ ጽጌ ትምዛእ፣ ደብረ
ጽዮን ዓዲ ወሰኽ፣ ደብረ ጸሪቅ ትግራይ፣ እና ደብረ ሣህል ዓረዛ) ይባላሉ፡፡
አቡነ ዮናስ ያረፉት መጋቢት 17 ቀን ቢሆንም ይህ ወቅት ታላቁ ዐቢይ ጾም የሚውልበት
ስለሆነ በዓለ ዕረፍታቸውን ጥር 21 ቀን እንዲያከብሩ ለልጆቻቸው አስቀድመው
ነግረዋቸዋል፡፡ በመሆኑም በትናንትናው ዕለት ጥር 21 ቀን በሁሉም ገዳማቸው ውስጥ
በታላቅ ክብረ በዓል ታስበው ይውላሉ፡፡
የአቡነ ዮናስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
"ፍቅር የቅዱሳን ዜና ገድላቸውን ታሪካቸውን አገልግሎታቸውን ትሩፉታቸውን ተጋድሎቸውን
እመሰክር ዘንድ ግድ ይለኛል" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ... ከላይ (ከሰማይ) የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት
የዐብይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ዘወረደ ይባላል፡፡ ዳረጎት ዘተዋሕዶም ይህ ጾም ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትን የምንለምንበት እንዲሆንና ስለእኛ ፍቅር ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በቀራኒዮ በመስቀል ላይ የዋለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅሩን በልባችን እንዲስልብን፣ በእምነታችን እንዲያጸናን፣ በምህረቱ እንዲምረን የምንለምንበት፣ ሥጋችንን ለነብሳችን የምናስገዛበትና በለቅሶ በስግደት ወደ አምላካችን የምንመለስበት እንዲሆን እንመኛለን፡፡
© ዳረጎት ዘተዋሕዶ
ይቀላቀሉን @daregot @Senkesar

ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ.... Kan samiirra bu'e Ayudonni(yuhudonni) fannisan
Torbeen Laguu Guddichaa kan jalqabaa 'Bu'ee' jedhama. Daaraagot Za Tawaayidoonis Laguun kun yeroo itti Nagaaf, Jaalalaafi tokkummaa itti kadhannu akkasumas Fayyisaa fi Qorichi keenya Iyyeesuus Kiristos jaalala keenyaaf jecha bantii samii olirraa dhufuun gadameessa durboo Haadha keenyaa Maariyaamii keessa buluun foon ishee irraa foon, lubbuu ishee irraa lubbuu qooddachuun Fannoo Qaraaniyoo irratti kan fannifame;jaalala isaa laphee keenya keessa akka bulchuuf, amantaatti akka nu jabeessuuf, dhiifama isaan akka nutti araaramuuf,foon keenya lubbuu keenyaaf yeroo itti ajajamuuf, bo'ichaa fi jilbeeffannaan gara Waaqayyoo keenyatti yeroo itti deddeebinu akka nuuf ta'u hawwina.
©Daaragot zatawahido
@daregot

ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ....The Jews crucified the one who came down from heaven
The first Sunday of Great lent is called Zewerede. it’s commemoration the incarnation of God who came from Heaven, born from Holy Virgin Mary in Bethlehem.
Daregot zetewahdo hereby, wishes peaceful, glories, joyful fast. May our Lord Jesus Christ help us through the fast of The Great Lent, Amen!
©Daregot Zetewahdo
Join us @daregot

ግነዩ ለእግዚአብሔር ❖ ለእግዚአብሔር ተገዙ ❖ Waaqaaf bitamaa
ግነዩ ለእግዚአብሔር ወጸውዑ ስሞ ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ ሀቡ ስብሐተ ለስሙ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ ዝግቡ ለክሙ መዝገበ ዘበሰማያት ኀበ ፃፄ ኢያማስኖ ወኢይረክቦ ሰራቂ ድልዋኒክሙ ንበሩ ዘበላዕሉ ጸልዩ ኀበ ሀሎ ክርስቶስ”
፠፠፠
ለእግዚአብሔር ተገዙ ስሙንም ጥሩ ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሯቸው ለስሙም ምስጋናን አቅርቡ ሰንበትን አክብሩ እውነትንም አድርጉ ብል የማያበላሸው ሌባም የማያገኘው በሰማያት ያለ መዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ፤ ተዘጋጅታችኹም ተቀመጡ ክርስቶስ ወዳለበት ወደላይ አስቡ፡፡
፠፠፠
Waaqaaf bitamaa maqaa isaas waama hojii isaas warra hin amannetti himaa maqaa isaas galata galchaa sanbata kabajaa dhugaa hojjadhaa.rirmi kan hin balleessine hattuunis kan hin argine galmee samiirra jiru ofii keesaanif walittii qabaa; qophaa'atii taa'aa; iddoo Kiristoos jiru gara olii yaadaa.
©ዳረጎት ዘተዋሕዶ
ዳረጎትን ይቀላቀሉ @daregot

ተዋሕድዋ
የዓድዋ ድልና ተዋሕዷዊ ገድል
በዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ
፩.የእግዚአብሔርና የምኒልክ ሰይፍ
፪.ጣይቱ ምዕመኒቱ
፫. ካህናት፣ ታቦታት ፣መነኮሳት ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር
፬. የኢትዮጵያ ገበዝ በዓድዋ ጦሩን ሲመዝ
፭.የወታደሩ ሃይማኖት ይባስ!
፮. ቤተ ክርስቲያን ግን ለምን በጦርነቱ ተሳተፈች?
እንኳን ለሰማዕቱ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓልና ለ124ኛው የአደዋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ተከታዩን ጹሑፍ ታነቡት ዘንድ ዳረጎት ማዕዷን አቅርባለች፡፡
ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡ 👉 https://telegra.ph/ተዋሕድዋ-03-01

#ምኩራብ
"እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ፤ ትዕይርቶሙ ለእለይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ፤ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡"
" የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና ነፍሴን በጾም አስመረርኋት፡፡"
❝Mana keetiif hinaafuun na gube, arrabsoon ittiin si arrabsanis ana irra bu'e; soomuun koo, lubbuu koos dhiphisuun koo arrabsoodhaaf anaaf ta'e.❞
መዝ 68(69)÷9-10 / Far. 68(69): 9-10
JOIN US 👉 https://tttttt.me/daregot

ኦርቶዶክስ ላይ ያለ ጥላቻ ክንፍ አብቅሎ ሲበር አየን!!
ምናለ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትን ባረገን!! ምናለ ለቤተክርስቲያን ያላቸውን
ጥላቻ እንዲህ እንደሱ በኛ ትከሻ በተሸከምን!! ግድ የላችሁም ኦርቶዶክስ ላይ የተደራጀ፣
የተናበበ ከመሬት ከፍ ያለ ጥላቻ አለ!! እንኳንም አየነው፣ እንኳንም ሰማነው፡፡
ሁሌም የሚገርመኝ ዳኒን በመስደብ የተሰለፉ ኃይሎች ብዛት ነው፡፡ ጂሃዲስት ሙሰሊም
የሙስሊም ጠላት ብሎ ይጠለዋል(ያዘጋጁትን ገጀራ ለቤተክርስቲያን አካላት አሳየብኝ
ብሎ)፡፡ እንኳንም ጠላኸው፡፡
መናፍቃን ተሃድሶ እና ፕሮቴስታንት ለቤተክርስቲያን ጥብቅና ቆመ ብለው ይጠሉታል፡፡
የእነሱ ባለሥልጣን ፓርላማ ቁጭ ብሎ የሁሉ ዜጋ ንብረት የሆነውን ፓርላማ ከውጭ
በተከራየ ፓስተሮች ሲያስጸልይበት ምንም አይታየውም፡፡
በብሔር ሰይጣን የተለከፉ በሽተኞች አምርረው ይጠሉታል(የትግራይም፣ የአማራም፣
የኦሮሞም) ይከሱታል፡፡ ለምን በኛ ልክ እራስህን አላዋረድክም ብለው፡፡ ለበሽታችሁ ጸበል
ሂዱበት እንጂ!!
የሚያሳፍረው ደግሞ ክር አንጠልጥሎ የሴራውን ግብ ሳያይ ከሰዳዎች እኩል በአደባባይ
አፉን የሚከፍትበት ኦርቶዶክስ ማየት ነው፡፡ በሌላው መናደድ አያስፈልግም፣ የሚያሳፍረው
ግን ይኅኛው ነው፡፡ እንቁዎቻቸውን በእሪያ ፊት የሚጥሉ ውለታቢሶች፣ በቤተክርስቲያን
አትሮኖስ ፊት ስለ አንዲት የክርስቶስ መንግስት እያስተማራቸው በአህዛብ ፊት የሚከሱት
ፈሪሳውያን ይኸው ዛሬ ፍሬአቸው!!
ምናለ እንዲህ ስለ ቤተክርስቲያን ብለን በተጠላን!!