ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
ና ኢትዮጵያ የተለዩ
ሀገሮች ናቸው፡፡ እሥራኤል በተለይ በብሉይ ኪዳን፤ ኢትዮጵያ ደግሞ
በተለይ በሐዲስ ኪዳን፡፡ ስለ እሥራኤል ያለውን ትቼ ስለኢትዮጵያ ያለውን
ግን ትንሽ ላቅርብ፡፡ የሙሴ ሚስት ኢትዮጵያዊት የሆነችው በአጋጣሚ
አልነበረም፡፡ ከሌላ ወገን አትጋቡ የሚለውን ትእዛዝ ከእግዚአብሔር
ተቀብሎ ለሕዝቡ ያስተላለፈው ሙሴ ይሄን ሲፈጽም አንተ ልዩ
(exceptional) ልትሆን አትችልም ብለው የተቃወሙት አሮን ወንድሙና
ማርያም እህቱ በአግዚአብሔር የተቀጡት ዝም ብሎ አልነበረም፡፡ ሙሴ
ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው የክርስቶስ ምሳሌ ስለሆነ ክርስቶስ በሥጋ
በተገለጠ ዘመን ከእሥራኤል ይልቅ በሌሎች ይልቁንም ኢትዮጵያ
አማናዊ ምሳሌ የምትሆንበት ድንቅ ምልክት ስለሆነ ነበረ እንጂ፡፡ ንግሥተ
ሳባ ኢየሩሳሌም ሄዳ አሁንም የክርስቶስ ምሳሌ የሆነውን ሰሎሞንን
አግኝታ ከዚያም የተነሣ በታሪካችን ትልልቅ የሆኑ ነገሮች (ታቦተ ጽዮንን
ጨምሮ) ወደ እኛ የመጡት ዝም ብሎ አይደለም፡፡ እነዚህን ታሪኮችና
ሌሎች ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ታሪኮችንና ምሳሌዎችን አስመልክተው
አብራርተው የጻፉት እነ ኦሪገን፣ ዮሐንስ አፈወርቅና ሌሎች ሊቃወንትም
ኢትዮጵያን ልዩ መሆኗንና ገልጠው ገና ከ2ኛው መቶ ዐመት ጀምረው
ያሰተማሩት ሁነቶቹ ቀላል ስላልሆኑ ነው፡፡
ይህ ማለት ግን ልዩ ስለሆነች ምንም ችግር ዐይነካትም ማለት ደግሞ
አይደለም፡፡ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በስፋት የሚነግሩን እግዚአብሔር
እሥራኤልን እንድታሸንፍ መርዳቱን ብቻ ሳይሆን ከፈቃዱ ስትወጣ ደግሞ
ለአሰቃቂ መከራዎችም አሳልፎ ይሰጣት እንደነበርና በንስሐ ስትመለስ
ደግሞ እንዴት ወደ ክብር እንደሚመልሳትም ጭምር ነውና፡፡
የኢትዮጵያም እንዲሁ ነው፡፡ በታሪካችን ውድቀቶቻችንም ሆኑ
ትንሣኤዎችቻን ካልተጠበቁ ሁኔታዎች የሚነሡ መሆኑን የታሪክ አጥኚዎች
ሳይቀሩ የመሰከሩለት ጉዳዩ ከአምላክ ጣልቃ ገብነት ጋር በእጅጉ የተያያዘ
ስለሆነ ነው፡፡
ከዚህም በላይ ደግሞ እግዚአብሔር በየትኛውም ሀገር ጣልቃ
የገባባቸው ታሪኮች ብዙዎች ናቸው፡፡ የአግዚአብሔር ማዳን በግልጽ
የሚታየው ደግሞ እርሱ ጣልቃ እንዲገባ የሚያስገድዱ የአማኞች
ሁኔታዎች በየሀገሮቹ ሲኖሩ ነው፡፡ ከእነዚያ ምሳሌ ለማምጣት አሁን
ቦታውም ጊዜውም አይፈቅድም፡፡ በኢትጵያም ከቅጣት ባለፈ
እግዚአብሔርን ጣልቃ ገብቶ ከፍጹም ጥፋት እንዲያድናት የሚያስገድድ
ሁኔታ በእኛ ዘመንም መኖሩን ግን እኔ በግሌ የማውቀውም የማምነውም
ነገር ነው፡፡ በዚህ እውቀትና እምነት የሚስማሙ ብዙዎች መኖራቸውንም
ደግሞ አውቃለሁ፡፡ የዚህን ዕወቀቴን ምንጭ ግን መናገር
አያስፈልገኝም፡፡ በርግጠኝነት ግን አውቃለሁ፡፡ አዎን ድፍን ያለ አውቃለሁ
ለመቀበል የሚያስቸግር ብቻ ሳይሆን ሊያስገምትና ሊያሰተች ቢችልም
ለዛሬ ግን ከዚህ ውጭ አማራጭ የለኝምና እምነቴን በመግለጽ ብቻ
እተወዋለሁ፡፡ ይህ እንዳለ የማውቀው ነገር ደግሞ እግዚአብሔርን
እንዲረዳን እንዲያስገድድ አምናለሁ፡፡ ስለዚህም በርግጠኝነት ኢትዮጵያ
ወደ ተሻለ መንገድ እንደምትሔድ ከተስፋ በላይ አምናለሁ፡፡ በዚህ ጊዜ
ተሻግረው የሚገኙትን ሰዎች የሚያውቀው ግን እግዚአብሔር ብቻ
እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ይህን የማያምኑ ሰዎች መኖራቸውም
እንደማያስቀረውም አምናለሁ፤ ይህንንም ኖረው የሚያዩት ደጋግመው
የሚመሰክሩት ሀቅ ይሆናል፡፡
ታዲያ ይህ ሁሉ ለምን ይደርስብናል?
አንዳንድ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች በተገናኘን ቁጥር ከሚያሳስቧቸው
ጭንቀቶች አንዱ ይህ ሁሉ ግፍና መከራ፤ ስደት፣ መፈናቀል፣ ግጭት፣
ሞት፣ የአብያተ ክርስቲያን ቃጠሎ፣ የሰዎች መለዋወጥ፣ … ለምን
ይደርስብናል የሚለው ነው፡፡
ለዚህ ሁሉ ጉዳታችን እውነተኛውና የማያወላዳው ምክንያት በአንድ ነገር
ሊጠቃለል የሚችል ይመስለኛል፡፡ ከአባቶቻችን ዘመን ጀምሮ እስካሁን
እኛን ጨምሮ እግዚአብሔርን በእጅጉ በድለናል፤ አጥፍተናል በሚለው፡፡
አሁን መዘርዘር የማያስፈልገኝ ብዙዎቻችንም በደንብ የምናውቃቸው
በደሎቻችን ብቻ ከጽዋ አይደለም ከጋን ሞልተው ፈስሰዋል፡፡ የማናውቀው
በደላችን ደግሞ እጅግ ብዙ ሊሆን ይችላል፡፡ እውነቱን እንነጋር ከተባለ
ኢትዮጵያ የብዙ ስውራን ቅዱሳን ሀገር በመሆኗ በእነርሱ ጸሎትና እኛ
እናውቅልሃለን በምንለው በብዙው ገጠሬ የዋሕ ሕዝብ ቅንነትና
ትዕግሥት ትኖራለች እንጂ እንደ እኛማ ቢሆን ከዐሥር በላይ ብነከፋፈልና
ብንጠፋፋ እንኳ ይገባን ነበረ፡፡ ሌላው ቀርቶ ዝርክርክ ምግባረ
ቢስነታችንን ትተን ሃይማኖትን እንደ ርእዮተ ዐለምና እንደፖለቲካ መሣሪያ
ብቻ ለመጠቀም የሚዳዳን ሰዎች የምናደርገው ድርጊት ብቻ ስንት
መዐትና ቁጣ ሊያመጣብን የሚገባ ነበር፡፡ ስለዚህ ማንኛችንም ሌላውንና
የትኛውንም ነጥለን ተጠያቂ የምናደርግበት ምንም ዐይነት ሃይማኖታዊ
ምክንያት ቢያንስ ለእኔ ፈጽሞ አይታየኝም፡፡ ከእኛ የባሱ የሚመስሉን
ሰዎችም መባሳቸው የተረጋገጠ እንኳ ቢሆን አብረን ባጠፋነው ጥፋት
የጉዳቱ ቀዳሚ ሰለባዎች ከመሆናቸው ያለፈ የተለየ ነገር አይታየኝም፡፡
የአንድን በሽታ ቫይረስም ሆነ ባክቴሪያ ቀድሞ የተሸከመ ስናይ ደግሞ
በሽታውንና በሽተኛውን በመለየት እርሱን በማዳን እኛንም ማትረፍ
ይገባናል እንጂ ለቫይረሱና ለባክቴሪያው ጉዳት ተጎጂውን ተጠያቂ
ማድረግ አይገባንም፡፡
ስለዚህ ለወቅታዊ ችግራችን መፍትሔው አሁን እንደምናደርገው
በመካሰስ፣ በመነቃቀፍና በመወነጃጀል ብቻ የሚመጣ አይመስለኝም፡፡
በአክቱቪዝምና በአድቮካሲ ወይም በተቋርቋሪነት መንፈስ ምንም ያህል
ብንተጋና ብንጋደል የምንፈልገውን ውጤት ለማምጣት ይቻለናል ብሎ
ለማሰብ በግሌ እቸገራለሁና፡፡ ወደ ጠቃሚ መፍትሔ ማምራት
የምንፈልግ ከሆነ ልንጀምርበት የሚገባውን ቀዳሚ ነገር መርሳት ተገቢ
አይመስለኝም፡፡ ከችግሮቻችን ወጥተን በተሻለ ሁኔታ ላይ ለመገኘት
ያስችላሉ ብዬ እንደ መፍትሔ የማስባቸውን እንደሚከተለው በአጭር
በአጭሩ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡
የመፍትሔ ጥቆማዎች
1) ብሔራዊ /ዐለም አቀፋዊ/ ንስሐ
በእኔ እምነት ችግሮቻችን የበደሎቻችን፣ የጥፋቶቻችን፣ የስሕተቶቻን፣
የድንቁርናችን ውጤቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ የሚያስፈልገን
በእውነት ጥፋተኝነታችንን ማመንና ከልብ ወደ እግዚአብሔር መመለስ
ነው፡፡ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ፣ ከሊቃነ ጳጳሳት እስከ ምእመን፣ ከሊቅ እስከ
ማይም፣ ሁላችንም መበደላችንን ዐለም ራሱ ያውቃል፡፡ ታሪክም
ይመሰክርብናል፡፡ እንኳን ዛሬ ጥንትም አባቶቻችን ከእግዚአብሔር ጋር
ያላቸውን ወዳጅነት አጽንተው የሚዘልቁት በእውነተኛ ተነሣሂነት ነው፡፡
ለመሆኑ እውነተኛ ብሔራዊ ንስሐ የምትለው ምንድን ነው የሚለኝ ቢኖር፡-
ሀ) ንስሐን እውነተኛ የሚያደርው የመጀመሪያው እንኳን በሕይወት ስላሉ
በታሪክ ስለምናውቃቸው ስለየትኞቹም ሰዎች ከልባችን ምሕረትን
ከመለመን በቀር ምንም ዐይነት ነገርን አለመመኘትና እንዳጠፉ ብናስብ
እንኳ ይቅር ማለት አለብን፡፡ በቅዳሴያችን ሁልጊዜ በምልጃ
ከምናቀርባቸው ጸሎቶች አንዱ "እግዚአብሔር እንዳይቀየማቸው
ከመዓትም ተመልሶ ፍጹም ዕረፍትን ይሰጣቸው ዘንድ ስለበደሉ
አባቶቻችንና ወንድሞቻችን እንማልዳለን" የሚለው የተካተተው እኛ
ባናስታውለውም ክርስቲያን ልቡ ከዚህ መንፈስ መውጣት ስለሌለበት
ነው፡፡ እኛ ግን እንኳን ከልባችን ስለበደሉት ልንለምን ይቅርና ስላለፉ
ሰዎች ምን እያልን እንደምንጽፍ ለሚያይ ሰው እንኳን እግዚአብሔርን
አንዳንዱ ነገራችን ሰይጣንንም የሚያስደንቅ ይመስለኛል፡፡
ሁለተኛው እውነተኛ የሚያደርገን አሁንም በቅዳሴያችን ላይ "ስለ ዐለም
ሁሉ እግዚአብሔር ማሰብን ያስቀድም ዘንድ ለእያንዳንዱም
የሚያስፈልገውን ያማረውን የሚሻለውንም ያስብ ዘንድ ስለ ዐ
ለም ሁሉ
እንማልዳለን" እያልን ደጋግመን በየዕለቱ እንደምንጸልየው በዚሁ መንፈስ
በእውነት መለመን አለብን፡፡ ከጥቅሱ እንደምንረዳው ክርስቲያን ሁሉ
ግዴታው ስለ ዐለም ሁሉ ማማለድና ጌታችን በመስቀል ላይ እንዳደረገው
ዐለምን ከእግዚአብሔር የማስታረቅ ኃላፊነት መቀበላችንን መርሳት
የለብንም፡፡ ጎላ ብሎ የተሠመረበትን ስናየው ደግሞ ምልጃችን
የሚፈልጉትን ሳይሆን የሚያስፈልጋቸውን፣ እነርሱ ያማራቸውን ሳይሆን
በእግዚአብሔር ፊት ያማረውን (ማንንም የማይጎዳውን)፣ እንዲሁም
ዐለምና ሰዎች የሚመኙትን ሳይሆን ለሁላችንም የተሻለውን
እንዲያስብልን መሆኑን ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡ በዚህ ከልብ አምነንበት
የምናስቀድስና የምንጸልይ ከሆነ ጽሑፎቻችንና ንግግሮቻችንም ሌላ
መንፈስ ሊጠናወጣቸው አይገባም፡፡ ከቅዳሴያችን ባሻገር ያሉ
የመስተብቁዕና የምልጃ ጸሎቶቻችን በሙሉ በዚሁ መንፈስ የተቃኙ
ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል በዐርብ የሊጦን ጸሎታችን ላይ "አድኅን እገዚኦ
ዛተኒ ሀገረ፤ ወካልአተኒ አህጉረ ወበሐውርተ እለ በሃይማኖተ ዚአከ
የኀድሩ ውስቴቶን - አቤቱ ይህችን (የምንኖርባትን) አገር አንተን በማመን
የሚኖሩባቸውን በዐለም ያሉ ሌሎች ሀገሮችን ሁሉ አድን"እያልን
የምንጸልየውን ማንሣት ይቻላል፡፡ እነዚህ እንግዲህ ለማሳያ ያህል ብቻ
ናቸው፡፡ ስለዚህ እውነተኛ ንስሐ ማለት ቃለ እግዚአብሔራችን፣
ቅዳሴያችን፣ ጸሎታችን እንደሚያዘው ብቻ ሆኖ መጸለይና ሁሉንም ነገራችን
ከዚያ አለማራቅን የሚመለከት ነው፡፡
ብሔራዊ ንስሐ ማለት ደግሞ ለምሳሌ መጪውን ዐመት በሙሉ ወደ
እግዚአብሔር መመለሳችንን የሚያሳዩ ድርጊቶችን በሁሉም
አጥቢያዎቻችንና በየግላችንም ማሳየት፡፡ ይህም ማለት በየትኛውም በዐለ
ንግሥ ሳይቀር ከበሮ እየደለቁ በከፍተኛ ደስታ ሆኖ መዘመሩን ትቶ ከንስሐ
ጋር የተገናኙ ቀለሞችን በለቅሶና በሐዘን እያመረገዱ (በማስረገጥ ብቻ
ሆኖ መተው)፡፡ ለምሳሌ ያህል በአምስቱ ዐመት የጣልያን ጦርነት ዘመን
እንኳን በሌላው ክብረ በዐል እንደ ልደት ባሉት ዕለታት እንኳ "ኢየሱስ
ክርስቶስ አስተጋብአነ፤ እስመ ዝርዋን አግብርቲከ ንሕነ" የሚሉት ዐይነቶች
ብቻ በለቅሶ በማመርገድ ብቻ ይባሉ እንደነበር በዘመኑ የነበሩ ሊቃውንት
ነግረውኛል፡፡ ለድልም ያበቁን እነዚያ ሀገራዊ ንስሐዊ ጸሎቶች እንደሆኑ
የታመነ ነው፡፡ እኛም መከራው፣ ሐዘኑ፣ ስደቱ፤ መፈናቀሉና ሞቱ ከልብ
የሚሰማን ከሆነ ዳንኪራ እስኪመስል ድረስ ከበሮ መደለቁን ትተን ከልብ
በቃለ እግዚአብሔሩ ሁሉ እግዚአብሔርን መለመንና መለማመጥ እንጂ
እንደ ኖኅ ዘመን ሰዎች ከአስረሺ ምቺው መሰል ሁኔታ ሳንላለቀቅ ለምን
ይህ ሁሉ ደረሰብን ማለት ተገቢ መስሎ አይታየኝም፡፡ በግላችንም ቢሆን
ጋብቻው ባይቀር ሰርጉን መተው፤ ሰርጉም ካልቀረ ቢያንስ ድለቃውን
መተው፡፡ አሁን እኮ በየሚዲያው የምናየው በየሁኔታው ኮምፕሌክስን
የሚያመለክቱ ከወትሮው የተለዩ ፈር የለቀቁ ድለቃዎች ናቸው፡፡ እነዚህ
ቀርቶ ሌላውንም ቢሆን ዘፈንና ልክ ያለፈ የደስታና የድግስ ዝግጅት ሁሉ
ለአንድ ዐመት ብንተወዉና ወደ ምጽዋትና ለተፈናቀሉት ዕርዳታ
ብናደርገው መልካም ይመስለኛል፡፡ ብሔራዊ ወይም ሀገራዊ ንስሐ
የሚባለው ሁኔታዎች ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ወደ ይቅረታና ወደ ፍትሕ
መመለስ የሚያመለክቱ ሲሆን ነው፡፡ ይህ የምናደርግ ከሆነ በሦስት ቀናት
ልባዊ ጸጸት ለነነዌ ሰዎች በይቅርታ የተመለሰ አምላክ ወደ እኛም
ይመለሳል፡፡ ቢያንስ ከሚጠፉት ጋር አብረን ከመጥፋት እንድናለን፡፡
ለሀገርም ለሁሉም ሰውም እንጠቅማለን እንጂ አንጎዳም፡፡ ሌሎቹ
ድርጊቶች ሁሉ ከዚህ ዐይነት መመለስ ጋር መሆን አለባቸው ብዬ
አምናለሁ፡፡
2) ነገሮችን በውል መረዳት
ወደ እግዚአብሔር የመመለስ መንገድን ከጀመርን በኋላ እንደ ሰው
ድርሻችን ለመወጣት የምናስብ ከሆነ ደግሞ አስቀድሞ ነገሮችን በውል
ለመገንዘብ መጣር ያለብን ይመስለኛል፡፡ በሚዲያ ከምናያቸው ነገሮች
ቅርንጫፉን ይዞ ከመሮጥ ረጋ ብሎ በማድመጥ ነገሮችን ከሥር
መሠረታቸው ማየት በእጅጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህን ለሁላችንም ቢያንስ
እኩል ማድረግ የሚቻል እንዳልሆነ የታወቀ ነው፡፡ ይህን የምናምን ከሆነ
በየፊናችን ከመንጫጫትና በየመሰለን ከመተቻቸት ረጋ ብሎ ሀሳብ
ማቅረብ የሚችሉ አካላትን ማዳመጥ ተገቢ ነው፡፡ በሰለጠነው ዐለም
ሀገሮቹንም ሆነ ሕዝቡን ስልጡን ከሚያሰኙት ነገሮች አንዱ አብዛኛው
ሕዝብ በርጋታ ነገሮችን አዳማጭ መሆኑ እንደሆነ ከብዙ አካላት
ሰምቻለሁ፡፡ ድጋፍና ተቃውሞውን የሚገልጸው መስማት ካለበት አካል
በአግባቡ ካዳመጠ በኋላ በሚይዘው አቋም አንጂ አንድ ነገር በሆነ ቁጥር
በመጯጯህ አይደለም፡፡ በፍጹም ሕዝብ ሁሉ አስተያየት ሰጪ ሊሆንም
አይችልም፡፡ እኛ ሀገር ግን ሁሉም በሁሉም ጉዳይ ተናጋሪ አስተያየት ሰጭ
ከመሆኑ በላይ በትዕግሥት ነገሮችን ለመመርመር ጊዜ የሚወስዱ እንኳ
ይሰደባሉ፤ ይወገዛሉ፡፡ ምን ዐይነት በሽታ እንደሆነም በእውነት ሊገባኝ
አይችልም፡፡
ከዚህም አልፎ ተቋማት በግለሰቦች መንገድ፣ ከግለሰቦችም በችኩሎችና
እንደፈለጋቸው በሚናሩ ግለሰቦች መጠን እንዲናገሩ ሲገፋፉ ስመለከት
ሁኔታዎቻን ሁሉ ወደ ጥፋት እንጂ ወደ ድኅነት የሚወስዱ ስለማይመስለኝ
በእጅጉ እፈራለሁ፡፡ በዚህ ሁኔታ በማዘን ብዙ ሀሳብ ያላቸውና ከሰው ሁኔታ
አንጻር አስተያየት መስጠታቸው ትርጉም የለሽ መሆኑን አስበው ዝም ያሉ
ሊቃውንትን ሳስብ ደግሞ መንገዳችን ሁሉ ያለማስተዋል፣ የድንቁርናና
የጨለማ ጉዞ ለማድረግ ሳንመካከር የወሰንን ስለሚመስል ብዙዎችን
እንደሚያስፈራ ከአንዳንድ ውይይቶቼ ተገንዝቤያለሁ፡፡ ባሉ ተቋማት
እምነት ከሌለን እንኳ ተቋማዊ አሠራር ፈጥሮ መሥራት የሚገባውን
መሥራት እንጂ በደመነፍስ መሔድ ከጥፋት ውጭ የሚፈይድልን ነገር
ስለማይኖር ነገሮችን በርጋታ ከመመርመርና ከማዳመጥ መጀመር በእጅጉ
አስፈላጊ መሆኑን መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም፡፡
ለምሳሌ ያህል የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን የሚያጠቋት ለምንድን ነው
የሚለውን በአግባቡ ሳንመልስ ዘልለነው ብንሔድ አስቦና አቅዶ ለተነሣ
ጠላት ከማገዝ በቀር የምንፈይደው ነገር አናሣ መሆኑን መካድ
አይቻልም፡፡ ከዐፄ ልብነ ድንግል መማር ካልቻልን ከማን ልንማር
እንችላለን? ነገር ከሥሩ ውኃ ከጥሩ እንደሚባለው አጥርቶ መነሣት
ቢጠቅም እንጂ አይጎዳም፡፡ ከሚታየው ሞኝ መልእክተኛ አለፍ ብሎ
የማይታየውን ለማየትና ተገቢውን ክርስቲያናዊም ሆነ ሕጋዊ ጥብቅና
ለመስጠትም ያመቻል፡፡ እንደ አባቶቻችን ለፍርድ ከጠነቀቅን
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑ አይጠረጠርም፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ
ከሆነ ደግሞ እርሱን የሚያሸንፈው ማን ሊሆን ይችላል? ስለዚህ የሌሎች
አሰላለፎች ሳያስፈራን ይልቁን በርጋታ ሆኖ አሰላለፍን ከእውነትና
ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግ ይገባናል፡፡
3) አጋጣሚውን በአግባቡ መጠቀም
ብዙ ስሕተቶችና ጥፋቶች እንደነበሩብና እንዳሉብን ከልብ ከተሰማን ምን
አልባት አንዳንዱ ጫና ያንንም ለማስተካከል እንድንችል እግዚአብሔር
የፈጠረልን ዕድልም ሊሆን ይችላል፡፡ ነገሮችን ሁሉ በውልና በአግባቡ
ከመረመርን ከስሜተዊነት ተላቅቀን ጠቃሚ፣ ዘላቂና ሥልታዊ ነገሮችን
በተግባር እንድናውል ሊጠቅሙን ይችላሉ፡፡ የዚህ ጽሑፍ አላማ
ጥንካሬያችንን ያለንን አሳይቶ መከራከር ያልሆነውም ለዚህ ነው፡፡ ከዚያ
ይልቅ ድክመቶቻችን ለመመርመር ብንጠቀምበት የበለጠ እንጠቀማለን፡፡
ካበለዚያ ግን ጥንካሬያችንንም ልናጣው እንችላለን፡፡ ስለዚህ ከቅዱስ
ሲኖዶስና ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ የሥልጠናና የሰው ኃይል ማፍሪያ
ተቋሞቻችን ፈትሾ ተቋማዊ አስፈላጊና ኦርቶዶክሳዊ ለውጦችን
ከማካሔድ አንሥቶ እስከ ምእምናን የአ
ስተሳሰብ ሥሪት ግንባታ ድረስ
አስበን ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ እስከሚገባኝ ድረስ የእብዛኛው የእኛ
ምእመናን አስተያየት ምንጩ የየግለሰቡ ሕይወትን መሠረት ያደረገ
ልምድ ነው፡፡ ይህ ተፈጥአዊ ቢሆንም በተደራጀና ኦርቶዶክሳዊ
አስተምሮአችንን በጠበቀ መንገድ እንዲሆን ብንሠራ አብዛኛዎቹ
ልዩነቶቻችን በፍጥነት ሊስተካከሉ ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም የብዙዎቻችን
እስተያየት ምንጩ የፖለቲካ ፍልስፍና ያደረሰብን ተጽእኖ፤ ከዘመኑ
የተበድያለሁ ትርክት፣ ከዐለማዊ ተቋማት አሰራር እና ከመሳሰሉት
እንደሚነሣ ሚዲያዎቹ ምስክር ናቸው፡፡ ከተጠቀሱትም ሆነ ካጠጠቀሱት
የሚጠቅም ነገር ሊገኝ እንኳ ቢችል ያ ሁለተኛ ነገር ድጋፍ እንጂ ቀዳሚ
ሊሆን አይችልም፡፡ ከዚህም በላይ ውስብስብ ስለሆነ ወደ አንድ
ለማምጣትም ቢያንስ አድካሚ ያደርገዋል፡፤ ከኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮና
ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ከተነሣን ግን ችግሮቻችን በአግባቡና
በፍጥነት ልንፈታ እንችላለን፡፡ ለዚህ ደግሞ ከምእመኑ እስከ ሲኖዶስ ባሉ
ተቋሞቻን ላይ ተገቢውን ጫና በተገቢው መንገድ ማድረግና
አስፈላጊውንና እውነተኛውን ለውጥ በማምጣት ከችግሮቻችን
ለመውጣት አጋጣሚውን መጠቀም ይገባናል፡፡
4) ለሰማዕትነት መዘጋጀት
ከላይ የተጠቀሱትን እያደረግን ምንም ቢመጣ ችግር ያለው
አይመስለኝም፡፡ በተገቢው መንገድ በእውነተኛ ንስሐና ለዐለም ሁሉ
በጎውን ከመመመኘት አልፈን፤ ጸልየን፣ ፍርድና ፍትሕ ለመጠንቀቅ
በምንችለው ሁሉ ካደርግን በኋላ ደግሞ መፍራት፣ መበርገግ፣
መንጫጫት ሳይሆን ለእውነተኛ ሰማዕትነት መዘጋጀት ነው፡፡ የክርስትና
ሃይማኖት የሚጠይቀው ይህንን ነው፡፡ እውነተኛ ሰማዕትነት ካለ
እግዚአብሔር አንዳንዱን እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ የት ትሸሻለህ የሚል
ድምጽ ያሰማዋል፡፡ አንዳንዱን ደግሞ በቃ ሲል እንደ ቆስጠንጢኖስ
መስቀል አሳይቶ መንገዱን ይመራዋል፡፡ እንደ ዳዊትም እኔ ከአንተ ጋር
ነኝና አትፍራ ውጣ የሚለውንም ካገኘ እርሱ ስለሚያውቀው እኛ መርጠን
ልንሰጠው አንችልም፡፡ በእውነትና ለእውነት ከሔድን እውነት እኔ ነኝ
ያለው አምላክ እውነተኛውን፣ የሚያስፈልገንን እና የሚሻለውን ሁሉ
ያደርግልናል፡፡
እንግዲያውስ በሀገራችን ያሉ ክስተቶች በቀስታና ያለማንም ከልካይ
የሚጀመሩበት ዘመነ ዮሐንስ እየገባ መሆኑን ተገንዝበን እጆቻችን ንጹሕ
አድርገን ወደ እግዚአብሔር እናንሣ፡፡ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር
ታደርሣለች ተብሏልና እጆቻችን ለጸሎት ተነሥተው በፊቱም ደርሰው
ተመልክቷቸው ፍትሕ ከእርሱ ለመቀበል ያብቃን፤ አሜን፡፡
#የምስራች !
💠 #በጉጉት ስንጠባበቃት የነበረችው ድንቅ የስነ ፍጥረት መፅሐፍ በአበው አስተምህሮ በሚል #በዲያቆን ኢንጂነር ዮሐንስ ጌታቸው የተዘጋጀችው ድንቅ መፅሐፍ በሀገረ ስብከቱ ጭምር ምስክርነት ተስጥቷት በሁላችንም እጅ ሊትገባ ነው። እንኳን ደስ አላችሁ!
መፅሐፉ በሰባት ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን 22ቱን ሥነ ፍጥረት በስፋትና በጥልቀት ያጠቃልላል።
#ምዕራፍ 1 የሥነ ፍጥረት ምንነትና ትርጉም ፣ ሥነ ፍጥረት የመማር ጠቀሜታ ፣የሥነ ፍጥረት መገኛ ...የሚሉትና ሌሎች።
#ምዕራፍ 2 በዕለተ እሁድ የተፈጠሩ ፍጥረታት ፦ ጨለማ ፣ ሰባቱ ሰማያት ፣ ቅዱሳን መላእክት ፣ ብርሃን ...ወዘተ።
#ምዕራፍ 3 የሰኞ ፍጥረታት ፦ ስለ ጠፈር በስፋትና በምልዓት።
#ምዕራፍ 4 የማክሰኞ ፍጥረታት ፦ በድንግል ማርያም የምትመሰለው የመጀመርያዋ ምድር (እርሻ)ና ሌሎች።
#ምዕራፍ 5 የረቡዕ ፍጥረታት ፦ስለ ከዋክብት ፣ ፀሐይና ጨረቃ በሚገርም መልኩ...።
#ምዕራፍ 6 ድንቅና አስገራሚ ስለሆኑት ፣ ዓለምን እንደ ቀለበት ጠቅልለው ስለያዙት ስለ ብሔሞትና ሌዋታ የተባሉ ግዙፋን የአዕዋፍ ዝርያዎችና ሌሎች...።
#ምዕራፍ 7 የዕለተ ዓርብ ፍጥረታት በድንቅ የአባቶች ትምህርት ስለ አዳምና ሔዋን ፣ ስለ ሥጋ ክብር ፣ጨየነፍስ ተፈጥሮና ህልውና ...በስፋትና በምልዓት ። ሌላው በታላቅ ጉጉትና ናፍቆት መፅሐፉን አንብባችሁ በሥነ ፍጥረት ውስጥ ከቅዱሳን አባቶች ጋር በመንፈስ አንድ ሆናችሁ ትመሰጡ ዘንድ ግብዣዬ የው ።
🔰🔰🔰
ሥነ ፍጥረት ሁሉ ያነበው ዘንድ ተገልጦ ያለ ድንቅ መፅሐፍ ነው። ሁል ግዜም የማይታጠፍ ተዘርግቶ ያለ ልዩ መፅሐፍ ነው። ይህም የቋንቋ መለያየት የማያግደው ሁሉ በእኩል እንድያነበው የተሰጠ መመርያ ነው ።በምድር ላይ የሚራመድ ማንኛውም ሰው ሁሉ ሥነ ፍጥረትን በመመልከት የእግዚአብሔር መኖርና መግቦት ማንበብና መረዳት ይችላል ። በሥነ ፍጥረት ውስጥ የእግዚአብሔር በፍጡር የማይመረመር ድንቅ ጥበብ የምናይበት ልዩ ውበት ፣ ኅብረ ብዙ ፍጥረት ፣ ታላቅ ሥርዓት ፣ ታላቅ ምስጢርና ኃይል የሚናይበት ነው።።።
#ከመፅሐፉ የተወሰደ
ቅዱስ ሲኖዶሱ በዛሬው አስቸኳይ ጉባኤው በሶስት ጉዳዮች ላይ ይወያያል ተብላል!

በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በሦሰት ዐበይት ጉዳዮች ጥልቀት ያለው ውይይት አድርጎ የመፍትሄ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ለዋዜማ ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡

በመጀመሪያ የሚያየው አጀንዳ ሕዝቡንና ቤተ ክርስቲያናን የመጠበቅ ሓላፊነት ስላለበት ቅዱስ ሲኖዶስ የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይመለከተዋል ብለዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ እንዳሉት መግለጫውን የሰጡት አካላት ጉዳዩ የማይመለከታቸው ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያንንም አይወክልም፡፡ ምክንያቱም መግለጫ ሰጭዎች የራሳቸውን አሳብ ይዘው ነው የተነሡት፡፡ አሳቡ በራሱ የቤተ ክርስቲያኗን መዋቅር የሚጻረር ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ቤተ ክርስቲያን እስከወዲያኛው እንደማትደግፋቸው አበክረው ተናግረዋል፡፡

ሁለተኛው አጀንዳ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጣይ ከመንግሥት ጋር እንዴት መቀጠል እንዳለባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይወያያል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የቤተ ክርስቲያን ጥያቄዎች መንግሥት በቀጣይ በምን አግባብ መመለስ እንዳለበት እንዲሁም በቤተ ክርስቲያን በኩል ደግሞ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች ካሉ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደሚወያይባቸው ተገልጿል፡፡ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ አያይዘውም መንግሥት በልዩ ልዩ ችግሮች የተወጠረ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያን ትረዳለች ብለዋል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-05

@TSEGABWOLDE @TIKVAHETHIOPIA
🚶ጉዞ ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ

👉አዘጋጅ #ማህበረ አሮን

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ከሀዋሳ ወደግሸን ደብረከርቤ በማህበረ አሮን ስለተዘጋጀ መጓዝ እምትፈልጉ ምእመናን በሙሉ ከወዲው መመዝገብ እና ቦታ መያዝ እምትችሉ መሆኑን በልዑል እግዚአብሔር ስም እንገልፃለን።

👉መነሻ ሀዋሳ ቅድስተ ስላሴ ቤተከርስቲያን

👉መነሻ ቀን መስከረም 18/01/2012 ዓ/ም

👉መመለሻ መስከረም 22/01/2012 ዓ/ም

📎በጉዞው እሚካተቱ ቦታዎች

👉ሃይቅ እስጢፍኖስ፣ሲሪንቃ አርሴማ 👉ጻድቃኔ ማርያም፣ ኩኬለሽ ማርያም 👉ሰሚነሽ ኪዳነምህረት እና ኢቲሳ ተክለሃይማኖት ።

💸አጠቃላይ ክፍያ የትራንስፖርት ማረፊያ ቦታ ምግብ እና መጠጥን ጨምሮ #1500 ብር ብቻ ።

👉ለበለጠ መረጃ

☎️ 09-88-06-36-02
☎️ 09-19-81-97-66

👉@DnEsube በ inbox ያናግሩን

ደውለው መጠየቅም ሆነ መመዝገብ ይችላሉ ።
‹‹ሩፋኤል›› (ጳጉሜን 3) እና የልጅነት ትዝታዬ !…
በየዓመቱ ጳጉሜን 3 ሲሆን ከጓደኞቼ ጋር በጠዋቱ እንነሳለን፡፡ ከእኛ ቤት ፊት ለፊት ካለው
ለምለም ሳር እንሰባሰባለን፡፡ ሰማይ ሰማዩን እናያለን፡፡ ከሰማይ የምንጠብቀው ከዝናብ ጋር
የሚወርድ በረከት ስላለ በዚህ ቀን ዝናብ አልዘነበም ማለት… በቃ ዕደለ ቢስነት ነው፡፡
የሩፋኤል ጠበል በቀጥታ ከሰማይ የሚወርድበት ቀን ነዋ፡፡ ስንሰማ ያደግነውና
ታላላቆቻችንም ሲያደርጉት ያየነው በዚህ ቀን ዝናብ ሲዘንብ እራቁት ሆኖ በደስታ እዘለሉ
መጠመቅ ነው፡፡ ሰማያዊ የበረከት ጥምቀት… እንዴት ደስ ይል ነበር……
ዝናቡ ሲዘገይ ይህንን ግጥም በዝማሬ እንጫወት ነበር፡-

ዝናቡ ናና ናና
ታዝለህ በጳጉሜን ደመና
ሩፋኤል ናና ናና
አዝዘው ይህን ደመና
ካፊያ ክፍክፍ… ክፍክፍ
ከሰማይ ደጅ በረከት አርግፍ
ዝናብ ዱብዱብ… ዱብዱብ
ለነፍሳችን ጽድቅ ለሥጋ ምግብ

ዝናቡ እስኪመጣ እያረፍንም ቢሆን እንዘምራለን… እንጨፍራለን… እንቦርቃለን፡፡ ልክ ዝናቡ
እንደመጣ (ገና ማንጠባጠብ ሲጀምር) ልብሳችንን ለማውለቅ እንጣደፋለን፡፡ ባዶ
መለመላችንን… ምንም ዓይነት ልብስ መልበስ ከበረከቱ የሚቀንስብን ስለሚመስለን
ውልቅልቅ… አይ ልጅነት! ማፈር የለ… መኩራት የለ… በቃ ለበረከት መጣደፍ ብቻ፡፡ ታዲያ
ዝናቡ ቀላልም ይሁን ከባድ ጉዳያችን አልነበረም፡፡ በዘናቡ መሐል እየዘለልን…
….
ሩፋኤል ገደፋዬ
እንደማዬ እንዳባዬ
ትልቅ ልሁን አሳድገኝ
ከክፉ ሁል - ታደገኝ
ጠበልህን ተጠመቅሁት
ዝናብ ሆኖ አገኘሁት
በጳጉሜን ወር ዓመቱ ሲያልቅ
በረከትህን ስንጠብቅ
ይኸው ሰማይ ተከፍቶልን
በረከትህ ወረደልን
የዛሬ ዓመት በዚች ቀን
እንመጣለን ልብስ አውልቀን….

ይህንና የመሳሰሉትን ጨዋታዎች ያለ መታከት እንጫወታለን፡፡ ለምን ሙሉ ቀን
አይዘንብም… እያረፍንም ቢሆን እንጫወታለን፡፡ ብዙ ዝናብ ሲወርድ ብዙ በረከት እንደወረደ
እናምናለን፡፡
ከዕለታት ባንዱ ቀን ታዲያ ዝናቡ አልዘንብ ብሎ … ሙሉ ቀን ‹‹ዝናቡ ናና ናና…›› ስንል
ውለን አመሸን፡፡ በሰማዩ ጌታና በሩፋኤል ተናደድን፡፡ ‹‹እንዴት ዝናብ ማውረድ ያቅታቸዋል?
ቀኑን ሙሉ እየለመናቸው እንዴት አይሰሙንም?›› የሚሉ ጥያቄዎችን እያነሳን መጨቃጨቅ
ጀመርን፡፡ አንደኛው ጓደኛችን ቆጣ ብሎ… ‹‹ከመካከላችን የሆነ ሌባ ወይም ውሸታም ልጅ
ከሌለ በቀር እንዴት ጌታ አይሰማንም? እራሳችንን እናጋልጥ… ምናምን…›› እያለ ያፋጥጠን
ጀመር፡፡ ‹‹አንተ ነህ ውሸታም! አንተ ነህ ሌባ!... አውቅሃለሁ አንተ ነህ… ባለፈው እሸት
ከሰው ማሳ ስትሰርቅ አላየሁህም?...›› እርስ በርስ መካሰስ ጀመርን፡፡
ጭቅጭቃችን ወደ ጠብና ድብድብ ሊያመራ ጥቂት ሲቀረው… መምሬ ጥበቡ በመንገድ
ሲያልፉ ጩኸታችንን ሰምተው ኖሮ ወደ እኛ መጡና ‹‹ልጆቼ… ምን ሆናችሁ ነው
የምትጨቃጨቁት?›› አሉን፡፡ እኛም የሆነውን ሁሉ ነገርናቸው፡፡ መምሬም እየሳቁ… ‹‹አይ
ልጆቼ… በሉ ቁጭ በሉና ላጫውታችሁ›› አሉን፡፡ እርሳቸው ትልቅ ድንጋይ ላይ ተቀመጡ፡፡
እኛ ደግሞ በለምለሙ ሳር ላይ በዙሪያቸው ተኮለኮልን፡፡ መምሬ ያኔ ከነገሩን
የማስታውሰው……፡-
‹‹…. እየውላችሁ ልጆች… ዛሬ ቀኑ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሩፋኤል የሚነግሥበትና
የሰማያት በሮችን ለበረከት የሚከፍትበት፣ ዕለተ ምጽአትም የሚታሰብበት ልዩ ቀን ነው፡፡
ሩፋኤል የሚለው የስሙ ትርጓሜ … ‹‹ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ…›› ማለት
ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ‹‹የሰላምና የጤና መልአክ›› ይባላል፡፡ ለእናንተም ከፈጣሪ ዘንድ
ሰላምና ጤናን አምጥቶ ይሰጣችኋል፡፡ በሰው ልጆች ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቁስል
ይፈወስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በሰው ቁስል ላይ የተሾመ
ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ይህም በመጽሐፈ ሄኖክ በምዕራፍ 6 እና
በምዕራፍ 10 ላይ ተጽፏል፡፡ የሰው ልጆች ከተያዙበት የኃጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ
በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል
ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡
ለሴቶችም ልዩ ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል
አይለያትም፡፡ የተፀነሰው ሕፃንም እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡
ሴቶች በምጥ ጊዜ በሩፋኤል ስም አምላክን ሲማጸኑት ምጡን ያቀልላቸዋል፡፡ አያችሁ…
ሁላሁንም ከእግዚአብሔር ታዝዞ ተንከባክቦ የጠበቃችሁና የሚጠብቃችሁ እርሱ ነው፡፡
ሩፋኤል የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም
ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ ብሎ ራሱ በመጽሐፈ ጦቢት
ምዕራፍ 12 ተቁጥር 15 ላይ ተናግሯል፡፡
ታዲያ ልጆች… የቅዱስ ሩፋኤልን በረከት ለማግኘት መሰብሰባችሁ መልካም ነው፡፡
ስትጠላሉና ስትደባደቡ ግን አይወድም፡፡
በዚህች ልዩ ቀን ሰማያት ስለሚከፈቱ ዝናቡን እንደጠበል መጠመቅ በረከት ያሰጣል፡፡ ነገር
ግን ዝናብ ባይዘንብም አትጨነቁ፡፡ ፈጣሪ ጸጋው ብዙ ነው፡፡ ዝናብ ባይዘንብም በምንጭና
በወንዝ መታጠብ ትችላላችሁ፡፡ በረከቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ ደግሞ ዛሬ እናንተ ባታዩትም
ፈጣሪ ከላይ ሆኖ ሲያያችሁ ነበር፡፡ የቅዱስ ሩፋኤልን በረከት ለማግኘት መፈለጋችሁን
ያውቃልና ዝናቡ ቢቀርም በረከቱ አይቀርባችሁም፡፡
እየውላችሁ ልጆች… ጻድቁ እዮብ በሰይጣን ተንኮል ሰውነቱ ሁሉ ቆስሎበት ሳለ በዚህች
በጳጉሜ ወቅት ነው በውሐ ታጥቦ የተፈወሰው፡፡ ይህንን ትውፊት ደግሞ ኢትዮጵያ አክብራ
አቆይታዋለች፡፡ ሁሌም በየዓመቱ በጳጉሜ ወቅት ወደ ወራጅ ውሐዎች በመሄድ መታጠብ
በረከት አለው፡፡ በተለይም በሩፋኤል ዕለት፡፡ ስለዚህ አሁኑኑ ወደ ወንዝ ሂዳችሁ ሰውነታሁን
ታጠቡ፡፡ ልክ ዝናቡ ሲዘንብ የምታገኙትን ሁሉ ታገኛላችሁ፡፡ በሉ ሂዱ..››

መምሬን እጅ ነስተን ወደ ወንዙ እሽቅድምድም….
ከዓመት ዓመት ያድርሰን!!
🚶ጉዞ ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ

👉አዘጋጅ #ማህበረ አሮን

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ከሀዋሳ ወደግሸን ደብረከርቤ በማህበረ አሮን ስለተዘጋጀ መጓዝ እምትፈልጉ ምእመናን በሙሉ ከወዲው መመዝገብ እና ቦታ መያዝ እምትችሉ መሆኑን በልዑል እግዚአብሔር ስም እንገልፃለን።

👉መነሻ ሀዋሳ ቅድስተ ስላሴ ቤተከርስቲያን

👉መነሻ ቀን መስከረም 18/01/2012 ዓ/ም

👉መመለሻ መስከረም 22/01/2012 ዓ/ም

📎በጉዞው እሚካተቱ ቦታዎች

👉ሃይቅ እስጢፍኖስ፣ሲሪንቃ አርሴማ 👉ጻድቃኔ ማርያም፣ ኩኬለሽ ማርያም 👉ሰሚነሽ ኪዳነምህረት እና ኢቲሳ ተክለሃይማኖት ።

💸አጠቃላይ ክፍያ የትራንስፖርት ማረፊያ ቦታ ምግብ እና መጠጥን ጨምሮ #1500 ብር ብቻ ።

👉ለበለጠ መረጃ

☎️ 09-88-06-36-02
☎️ 09-19-81-97-66

👉@DnEsube በ inbox ያናግሩን

ደውለው መጠየቅም ሆነ መመዝገብ ይችላሉ ።አዲስ አበባ ላላቹ ኃይሌ ጋርመንት ጋር በ 18 ጥዋት ጠብቁን ደውላቹ አብራቹን መጓዝ ትችላላቹ ኦርቶዶክስ አንዲት ናት ።
የጌታችን ግማደ መስቀል ወደ ኢትዮጵያ እንዴትና
በማን መጣ +++ + #
:
………" ግብፅን ለመውጋት ሀገራቸው ድረስ ምን አስኬደኝ?
በጦርነትስ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ነፍስስ ምን አስጠፋኝ?
ከሀገሬ ምድር መንጭቶ የእነርሱ እስትንፋስ የሆነውን የአባይን
ወንዝ ለምን አልገድበውም "………
:
በመካከለኛው ዘመን ታሪክ በ14ኛው ምዕተ ዓመት የኦቶማን
ቱርኮች እስላማዊ እንቅስቃሴ መላው አለምን ወደ አንድ
ሃይማኖት ለመውሰድ አስቦ በተነሳበት ሰዓት በተለያዩ ሀገራት
ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች ላይ ትንሽ የማይባሉ ችግሮች መፈጠር
ጀምረው ነበር።የዚህ
ችግር ገፈት ቀማሽ ከሆኑ ሕዝቦች መሀከልም በግብፅ ውስጥ
የሚገኙ የእስክንድርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተከታዮች
አንደኞቹ ናቸው። በግብፅ ሀገሪቷን የሚያስተዳድሩት ከሊፋወች
የእስልምናን ሃይማኖት የያሚራምዱበመሆናቸው በዛ የሚገኙ
ክርስቲያኖች ላይ
የበዛ መከራን ያደርሱባቸው ነበር። ገዳማትና አድባራቶቻቸውን
ያወድሙባቸዋል፣የሃይማኖት አባቶቻቸውን ያሰድዳሉ እነሱንም
ይገሏቸው ነበር። ከመከራና ከእንግልት የተረፉት ደግሞ በዬ
አቅራቢያቸው ወደሚገኙት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ክርስቲያን
ነገሥታት ወደሚገዟቸው ምድሮች እየሄዱ እየደረሰባቸው ያለውን
በመናገር እንዲታደጓቸው እርዳታን ይጠይቁ ነበር።ያኔ ደግሞ
በሀገራችን ኢትዮጵያ ነገሠው የነበሩት ደጉ ንጉሥ አፄ ዳዊት
ነበሩና መልእክቱ በደረሳቸው ጊዜ ልክ ቀደምቶቻቸው እነ አፄ
ካሌብ እነ ቅዱስ ይምርኃነ ክርስቶስ እንዳደረጉት ክርስቲያኖችን
ለመታደግ ተነሱ በጊዜው የሚያስፈልገውን የጦር ዝግጅትም
አድርገው ወደ ግብፅ ዘመቱ መንገዳቸውም በሱዳን በረሀ በኩል
ነበርና ጉዟቸውን አጋምሰው ካርቱም አካባቢ ሲደርሱ የአባይን
ወንዝ ተመልክተው " ግብፅን ለመውጋት ሀገራቸው ድረስ ምን
አስኬደኝ? በጦርነትስ ክቡር
የሆነውን የሰው ልጅ ነፍስ ምን አስጠፋኝ? ከሀገሬ ምድር
መንጭቶ የእነርሱ እስትንፋስ የሆነውን
የአባይን ወንዝ ለምን አልገድበውም "ብለው አሰቡና
ሰራዊታቸውን እዛው አስፍረው አባይን ማስገደብ ጀመሩ የወንዙን
ውሀም ተፈጥሯዊ ከሆነ መንገዱ አስቀይሰው ወደ በረሀው ያለ
ጥቅም እንዲፈስ አደረጉትና ለግብፅ ሰወች ውሀውን የሚለቁት
በክርስቲያኖች ላይ የሚፈፅሙትን ግፍ ካቆሙ ብቻ እንደሆነ
የሚገልፅ መልእክት ላኩባቸው። ይህን የተመለከቱት የግብፅ
ከሊፋወች በሆነው ነገር እጅግ ተደናግጠው ንጉሡ አፄ ዳዊት
ያሉትን እንደሚፈፅሙና እስካሁን ላደረጉትም ይቅርታ በመጠየቅ
እጅ መንሻ የሚሆን 24ሺ ወቄት ወርቅ በማስያዝ የእስክንድርያ
አባቶችን ንጉሡ ወዳሉበት ሽምግልና ላኩባቸው። አፄ ዳዊትም
ሽማግሌወቹ ወደርሳቸው በደረሱ ጊዜ ነገራቸውን ሰምተው
በመደሰት ያመጡትን እጅ መንሻ ለፈራረሱት የእስክንድርያ
አብያተ ክርስቲያናት ማደሻ እንዲሆን
መልሰው ሰጧቸው። ነገር ግን የጌታችን የመድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል በእጃቸው እንደሚገኝ ሰምተው
ነበርና ቃል ኪዳናቸው በውል እንዲታሰር እንደመያዣ እርሱን
እንዲሰጧቸው ጠየቁ።አፄ ዳዊት የጌታችን ግማደ መስቀል
በግብፅ እንዳለ ያወቁትና
ጥያቄውን ለማቅረብ ምክንያት የሆናቸው ሰራዊታቸውን ይዘው
በሱዳን በረሀ በሚመጡበት ጊዜ የበርካታ
ሰወችን የወዳደቁ አፅሞች አይተው ስለነበር የዛን ምክንያት
ሲጠይቁ አንድ መነኩሴ ከመንገድ አግኝተው "ኢየሩሳሌም ሄደን
ቅዱሳና መካናትን እንሳለማለን፣ በግብፅ ከሚገኘውም የጌታ
ግምደ መስቀል በረከት እንቀበላለን ብለው ከሀገራቸው
ወጥተው በከባዱ ጉዞ ተዳክመው በበረሀ ወደቀው የቀሩ
የክርስቲያኖች በድን አንደሆነ "ነግረዋቸው ነበርና ነው። ይህ
ነገር ንጉሡን በሰሙት ነገር እንዲያዝኑና በዘመቻቸው የግብፅ
ክርስቲያኖችን ከመታደግ ሌላ ግማደ መስቀሉን ወደ
ኢትዮጵያ የማምጣት ፍላጎት እንዲያድርባቸው እንዳደረገ ታሪክ
ይነግረናል።ጥያቄውንም ያቀረቡት ከዚህ በኋላ ነው።
የእስክንድርያ አባቶች አፄ ዳዊት የጠየቁትን ነገር ሲሰሙ
የጌታችን መስቀል ለእነርሱ ምን ማለት
እንደሆነ ይረዳሉና ከፉኛ ተደናግጡ ተቆጡም ጭምር የግብፅ
አስተዳዳሪ ከሊፋወች ግን መስቀልን እንደተራ እንጨት
ቆጥረውና ውሀውን ለማስለቀቅ ቀላል ነገር
እንደተጠየቁ አስበው ግምደ መስቀሉ እንዲሰጣቸው
አዘዙ።በስተመጨረሻም የእስክንድርያ አባቶች በነገሩ መክረው
እኛ ጋር ሆኖ አህዛቦች ከሚያጠፉት፤ በክርስቲያኖች ሀገር
በክብር ቢቀመጥ ይሻላል ብለው ስላሰቡ ለመስጠት ፈቃደኞች
ሆኑ። አባ ሚካኤል አባ ገብርኤል በሚባሉ ጳጳሳት አባቶችን
አስይዘውም ከሌሎች ንዋየ ቅዱሳት ጋር ወደ ኢትዮጵያዊው
ንጉሥ ላኩት በ1395 ዓ,ም በመስከረም ወር በ10 ኛው ቀንም
ግማደ መስቀሉ በአፄ ዳዊት እጅ ገባ። ንጉሡም በሆነው ነገር
እጅግ ተደስተው የአባይን ውሀ ለቀቁላቸውና በሆታና በእልልታ
መስቀሉን ወደሀገራቸው ይዘው መመለስ ጀመሩ። ነገር ግን
ንጉሡ በጉዞው መሀል "ስናር" በተባለችው የኢትዮጵያና የሱዳን
አዋሳኝ ድንበር ላይ ሲደርሱ ከፈረሳቸው ላይ ወድቀው
ሕይወታቸው በማለፉ የመስቀሉ ወደ መሀል ሀገር የመግባት ጉዞ
ተስተጓጎለ።አፄ ዘርዐ ያዕቆብ እስከነገሡበት ጊዜ ድረስም
ግማደ መስቀሉ በዛው ቦታ ላይ በግብፃውያኑ ጳጳሳት እጅ በአደራ
ተቀመጠ።
አፄ ዘርዐ ያዕቆብ የአፄ ዳዊት ስምንተኛ ወንድ ልጅ
ናቸው።አባታቸው የጀመሯቸውንም ነገር በማስፈፀም
ይታወቃሉ።የቅዱስ መስቀሉንም ወደ ኢትዮጵያ መግባት
ከእርሳቸው በፊት ነግሠው ከነበሩት ታላላቅ ወንድሞቻቸው በላይ
ይናፍቁ ነበርና ልክ ሀገርን የማስተዳደሩ ኃላፊነት ሲሰጣቸው
የእግዚአብሔርን መልካም ፈቃድ በመጠየቅ መስቀሉ ወዳለበት
ቦታ ተጓዙ። በመንገዳቸውም # አንብር_መስቀልዬ_በዲበ_
መስቀል (መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አስቀምጥ) የሚል ህልም
ይታያቸው ነበር።በቦታው ሲደርሱም ግብፃውያኑ አባቶች ሁሉንም
ንዋያትና ግማደ መስቀሉንን መስከረም 21·1443 ዓ,ም
በፍፁም ታማኝነት ጠብቀው አስረከቧቸው። አፄ ዘርዐ ያዕቆብም
በታላቅ ደስታና ምስጋና ቅዱሱን መስቀል ወደ ሀገራቸው ክልል
ይዘው በመግባት ሕልማቸው የሚፈፀምበትን መስቀለኛ ተራራ
እየተዘዋወሩ ይፈልጉ ጀመር። በዚህም ብዙ ቦታወችን አካለሉ
እንደ መናገሻ እና እንጦጦ ተራራወች ላይም አስቀምጠውት
ነበር ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ በዛ ቦታ ሳይሆን ሲቀር
ምልክት እያሳየ ቦታውን እንዲቀይሩ ያደርጋቸው ነበር። እንዲህ
እንዲህ እያሉ ታላላቅ ተራራወችን ሲመርጡ ቆይተው
በስተመጨረሻ ወሎ ውስጥ አምባሰል አውራጃ በግሸን ደብረ
ከርቤ መስቀለኛ ተራራ ላይ ሲደርሱ እግዚአብሔር አምላክ
ለመስቀሉ የመረጠው ቦታ ያ መሆኑን አሳወቋቸው በዚያ
እንዲያስቀምጡት አዘዘ። ንጉሡ አፄ ዘርዐ ያዕቆብም ወደ
ተራራው አናት ወጥተው ሲያዩት ቦታውን ስለወደዱት በአንደኛው
አቅጣጫ ላይ መስቀሉን ለማስቀመጫ የሚሆን ሰፊ ጉድጓድን
አስቆፈሩ የጌታችንን የቀኝ እጅ ያረፈበትን ግማደ መስቀሉንና
ሌሎች ቅዱሳን ንዋያትንም ከወርቅ፣ ከብር፣ከነሐስንና ከብረት
በተሰራ ትልቅ የመስቀል ቅርፅ ባለው ሳጥን ውስጥ በመክተት
በተቆፈረው ጉድጓድ መሀከል በብር ሰንሰለት ከአራቱም ማዕዘን
ተወጥሮ እንዲቀመጥ አደረጉ በላዩም ላይ እንጨት
አስረብርበው የእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን መቅደስ
አነፁበትና እለት እለት እየታጠነ እየተወደስ እንዲኖር አደረጉት።
እንግዲህ የጌታችን ግማደ መስቀል ወደ ሀገራችን የመምጣቱ
ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ከላይ እንዳየነው ነው። መስቀልን
የሚመለከቱ በዓላት በሀገራችን በስፋት የመከበራቸውም ነገር
የመጣው ከዚህ ዘመን በኋላ ነው። አፄ ዘርዐ ያዕቆብ መስቀሉን
በሚገባው ቦታ አስቀምጠው ካበቁ በኋላ
—መስከረም 1
7 ቀን ንግስት እሌኒ መስቀሉን ለማግኘት ቁፋሮ
ያስጀመረችበትን ቀን በማሰብ ሕዝበ ክርስቲያን ከዋዜማው
ጀምሮ በአደባባይ ወጥቶ ደመራ በማብራት
እንዲያከብር
—መስከረም 21 ቀን እርሳቸው መስቀሉን ከግብፃውያን
የተቀበሉበትን ቀንና በግሸን ደብረከርቤ አምባ ላይ
ያሰቀመጡበትን ቀን በማሰብ በቦታው ተግኝቶ እንዲያከብር
ሥርዓት እንዲሠራ አዘዙ። ይሄው እኛንም እስከ አሁኑ ዘመን
ድረስ ከዓመት ዓመት እነዚህ እለታት
ከታላላቅ ሃይማኖታዊ ክንዋኔወች ጋር ለማክበር እንድንበቃ
አደረጉን።
:
ወዳጆቼ እንኳን ለዚህ ታላቅ የብርሃነ መስቀል በዓል
አደረሳችሁ። አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
በመስቀሉ ኃይል የሀገራችንን አንድነቷን ይጠብቅልን እስከዛሬ
ድረስ ተጠብቆ የቆየውን ባህልና ሃይማኖታዊ ሥርዓታችንም
ያፅናልን በዓሉንም የሰላም ያድርግልን ለዘላለሙ አሜን።
# ምንጭ_መጽሐፈ_ጤፉት ዘግሸን ደብረ ከርቤ
መስቀሉን ያስወጣችው የእሌኒና የልጇ የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ
የመሰቀሉ ታሪክ❖
❖ ይኽ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ የአባቱ ስም ቊንስጣ የእናቱ
ስም እሌኒ ነው፤ ከሓዲውከሓዲው (ሶርያ) ላይ ትቷቸው ወደ በራንጥያ
ተመለሰ፡፡
❖ “ወይእቲ ነበረት እንዘ ተሐጽኖ ለወልዳ ወመሀረቶ
ትምህርተ ክርስትና ወኮነት ዘትዘርዕ ውስተ ልቡ ምሕረተ
ወሣሕለ ላዕለ ሕዝበ ክርስቲያን” ይላል፤ ርሷም ልጇን
የክርስትና ትምህርትን አስተማረችው፤ ይቅርታንና ርኅራኄን
በክርስቲያን ወገኖች ላይ እንዲያደርግ በልቡናው መልካም ዘርን
ትዘራበት ነበር፡፡
❖ ከዚያም ቈስጠንጢኖስ አካለ መጠን ሲያደርስ ወደ
አባቱ ሰደደችው፤ አባቱም የጥበቡን ብዛት አይቶ በመደሰት
ከበታቹ መስፍን አድርጎት በመሾም በመንግሥቱ ሥራ ላይ ኹሉ
ሥልጣንን ሰጥቶታል፤ “ወእምድኅረ ክልኤቱ ዓመት አዕረፈ
አቡሁ ወተመጠወ ቈስጠንጢኖስ ኲሎ መንግሥተ ወገብረ
ፍትሐ ርቱዐ” ይላል፤ ከኹለት ዓመት በኋላ አባቱ በማረፉ
ቈስጠንጢኖስ መንግሥቱን ኹሉ ተረክቦ የቀና ፍርድን የሚፈርድ
ኾነ፤ ከርሱ በፊት የነበሩ ነገሥታት የጫኑባቸውን ጽኑ አገዛዝ
ከሰዎች ላይ የሚያስወግድ ኾነ፤ በዚኽ ምክንያት ኹሉም
ወደደው፤ ዝናውም በብዙ ሀገሮች ላይ ተሰማለት፡፡
❖ በአንጾኪያ ያሉ ክርስቲያኖችም የቈስጠንጢኖስን ፍርድ
መጠንቀቁን፣ ድኻ መጠበቁን እየሰሙ ከከሓዲው
ከመክስምያኖስ አገዛዝ እንዲያድናቸው የልብሰ ተክህኖውን
ቅዳጅ፣ የመስቀሉን ስባሪ ይልኩለት ነበር፤ ርሱም ስለደረሰባቸው
መከራ በእጅጉ እያዘነ እንዴት አድርጎ እንደሚያድናቸው ያስብ
ነበር።
❖ “ወእንዘ ይነብር ውስተ ዐውድ ወናሁ አስተርአዮ
በመንፈቀ መዓልት መስቀል ዘሕብሩ አምሳለ ከዋክብት
ወዲቤሁ ጽሑፍ በልሳነ ዮናኒ ኒኮስጣጣን ዘበትርጓሜሁ በዝንቱ
ትመውዕ ጸረከ ወአንከረ ብርሃኖ ለመስቀል ሶበ ርእየ እንዘ
ይከድኖ ለብርሃነ ፀሓይ” ይላል ከዕለታት ባንዳቸው በአደባባይ
በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ከቀኑ በስድስት ሰዓት ጊዜ ሕብሩ
እንደከዋክብት የኾነ መስቀል በጸፍጸፈ ሰማይ ላይ ሲታየው፤
በላዩም በዮናኒ ቋንቋ ኒኮስጣጣን የሚል ጽሑፍ ነበረው፤
ትርጓሜውም በዚኽ ጠላትኽን ድል ታደርጋለኽ ማለት ሲኾን፤
ርሱም የመስቀሉ ብርሃን የፀሓይን ብርሃን ሲሸፍነው አይቶ
ተደንቋል፡፡
❖ ይኽነንም ያየውን ለሊቃውንቱ በጠየቃቸው ጊዜ
አውስግንዮስ የሚባል ሕጽው በዚኽ መስቀል አምሳል ጠላትኽን
ድል ታደርጋለኽ ማለት ነው ብሎ ተረጐመለት፤ መልአኩም
ሌሊት በራእይ ታይቶት አስረዳው፤ “ወነቂሆ እምንዋሙ ጸንዐ
ልቡ ወገብረ መስቀለ ዘወርቅ ወረሰዮ መልዕልተ አክሊለ
መንግሥቱ ወአዘዞሙ ለኲሎሙ መኳንንቲሁ ወሐራሁ ከመ
ይግበሩ መስቀለ በኲሉ ንዋየ ሐቅሎሙ” እንዲል ከእንቅልፉም
በነቃ ጊዜ ልቡ ጸናና የወርቅ መስቀልም አሠርቶ በነገሠበት
ዘውድ ላይ አደረገው፤ መኳንንቱንና ወታደሮቹን ኹሉ መስቀል
አሠርተው በጦር መሣሪያቸው ላይ ያደርጉ ዘንድ አዘዛቸውና
እንዳላቸው አደረጉ፡፡
❖ ከዚያም በክርስቲያኖች ጠላት በከሓዲው መክስምያኖስ
ላይ ዘመተበት፤ ከዚያም መክስምያኖስ ሰምቶ ጦሩን ይዞ
መጣበት፤ በመክስምያኖስ ጦር ላይ ዐድረው ድል ያደርጉ
የነበሩ አጋንንት በቈስጠንጢኖስ ጦር ላይ ያለውን ትእምርተ
መስቀል ባዩ ጊዜ ተለይተውት በኼዱ ጊዜ ድል ተነሣ፤ ርሱም
ከጥቂቶች ጋር ራሱን ለማዳን “ወተጽዕኑ ዲበ ተንከተም
ወተንከተምኒ ንህለ ወተሠጥመ መክስምያኖስ ምስለ ሰራዊቱ”
ይላል ወደ ሮሜ ለመሻገር በድልድይ ላይ ሲወጡ ድልድዩ ፈርሶ
ከሰራዊቱ ጋር ሰጥሟል፡፡
❖ ከዚያም በድል አድራጊነት ንጉሥ ቈስንጢኖስ ወደ ሮሜ
በገባ ጊዜ ካህናቱ ሕዝቡ መብራት ይዘው፤ “መስቀል ኀይልን
መስቀል ጽንዕነ መስቀል መዋዔ ጸር” እያሉ እየዘመሩ ተቀበሉት፤
ርሱም እናቱ ቅድስት እሌኒ እያስተማረች ያሳደገችው፤ በኋላም
ምእመናን ይልኩለት የነበረው፤ በሰሌዳ ሰማይ ላይ
የተመለከተው፤ አኹንም በአንጾኪያ ምእመናን ይዘው
የተቀበሉትን አይቶ ትክክለኛውን ሃይማኖት በመረዳት ከሀገሩ
ሶልጴጥሮስን አምጥቶ ተጠምቋል፡፡
❖ ከዚያም ዐዋጁን ባዋጅ በመመለስ “አብያተ ጣዖታት
ይትዐጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ” (አብያተ ጣዖታት
ይዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ) የሚል ታላቅ ትእዛዝን አዘዘ፤
የጌታችንንም መስቀል እንድታወጣ እናቱ እሌኒን ወደ
ኢየሩሳሌም ላካት፨
❖ ይኽስ እንደምንድ ነው ቢሉ የጌታችን መስቀል ከጌታችን
ዕርገት በኋላ ሙት እያነሣ፣ ደዉይ እየፈወሰ ለክርስያኖች ታላቅ
ክብር በመኾኑ፤ አይሁድ በዚኽ ቀንተው ጒድጓድ ቈፍረው
በይሁዳ እና በኢየሩሳሌም ኹሉ ቤቱን የሚጠርግ ጒድፉን
አምጥቶ እንዲያፈስስበት በማዘዛቸው ቦታው የቆሻሻ መጣያ
ኾኖ ዕሌኒ ንግሥት እስከ መጣችበት ድረስ ለ፫፻ ዓመታት ያኽል
ተቀብሮ ኖረ፡፡
❖ ልጇ ቆስጠንጢኖስም በመስቀሉ ኀይል የክርስቲያኖች
ጠላት የኾነውን መክስምያኖስን ድል ከነሣ በኋላ በሶል ጴጥሮስ
ተጠምቆ ክርስቲያን ኾነ፤ ርሷም ልጄ ክርስቲያን ከኾነ
ኢየሩሳሌም ኼጄ የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት አሠራለኊ፤
የጌታዬ መስቀልን ከተቀበረበት አስወጣለኊ ብላ ስዕለት ተስላ
ነበርና ያ በመፈጸሙ ደስ ተሰኝታ፤ ለልጇ ነገረችው፤ ርሱም
በደስታ ብዙዎች ሰራዊትን ስንቅ አስይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ላካት፤
በደረሰችም ጊዜ ሱባኤን አድርጋ የመስቀሉ ጠላቶችን በጽኑ
እስራት አሰረቻቸው፤ በኋላም አሚኖስና ኪራኮስ የሚባሉ
በዕድሜ የጠገቡ ሽማግሌዎችን ብትጠይቃቸው ሊነግሯት
ፈቃደኛ አልኾኑምና በጽኑ እስራት ብታስጨንቃቸው፤ ታሪኩን
ነገሯት፤ ቦታውንም ጠቈሟት፡፡
❖ ከዚያም በጸሎቷ ላይ ቅዱስ መልአክ ተገልጾላት በዕጣን
ጢስ አማካይነት እንደምታገኘው ተረድታ፤ መስከረም ፲፮
ደመራን አስደምራ በእሳት እንዲቃጠል አድርጋ እጅግ ብዙ
ዕጣንን ብታስጨምር ጢሱ ወደ ሰማያት ወጥቶ መስቀሉ
ካለበት ቦታ ላይ ተተክሎ ሰገደ፤ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይኽነን ድንቅ
ታሪክ ይዞ "ሰገደ ጢስ ኀበ አንጻረ መስቀል ሰገደ ጢስ ወባረከ"
እያለ አመስግኗል፡፡
❖ ርሷም ፈጣሪዋ እግዚአብሔርን በፍጹም ደስታ አመስግና
ቊፏሮውን ከመስከረም 17 ዠምሮ እስከ መጋቢት 10 ድረስ
እንዲቈፈር አስደርጋለች፤ በቊፋሮው ወቅትም የፈያታዊ
ዘየማንና የፈያታዊ ዘጸጋም መስቀል ቢገኙም ዕውር አላበሩም፣
ሕሙማንን አልፈወሱም፡፡
❖ ከዚያም መጋቢት 10, በ327 ዓ.ም. ጌታችን ክቡር
ደሙን ያፈሰሰበት ቅዱስ መስቀሉ ተገኘ፤ በዚኽ ጊዜ ከሕሙማን
ላይ ቢያደርጉት ኹሉንም ፈወሳቸው፣ ዕዉራን በሩ፣ ሙታንም
ተነሡ፡፡ ከዚኹም ጋር የተወጋበት ጦሩ፣ የተቸነከረባቸው ቅንዋት
ኹሉ ተገኝተዋል፤ ርሷም በፈረሷ ልጓም ላይ የመስቀል
ምልክትን አስቀርጻበታለች፡፡
❖ ርሷም ጌታችን ተአምራት በሠራባቸው ቦታዎች አብያተ
ክርስቲያናትን በማሠራት፤ በተለይም በጎልጎታ የተሠራው ቤተ
ክርስቲያን መስከረም ፲፯ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናን
በተገኙበት ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑ ተከብሯልና፡፡ ርሷም ለድኾችና
ለጦም አዳሪዎች ብዙ መልካም ነገርን በማድረግ ግንቦት ፱
በሰላም ዐርፋለች፡፡
❖ ሊቁ አርከ ሥሉስም ስለ ቅድስት እሌኒ በዐርኬው ላይ፡-
“ሰላም ለእሌኒ ውስተ ምድረ ሕይወት ኤልዳ
ምክረ መንፈስ ቅዱስ አመ ወሰዳ
ለዘሐይወ በድን በለኪፈ መስቀል ቅድመ ዐውዳ
እምአይቴ አንተ ትቤሎ ወእምአይ አንግዳ
ዘተረከብከ ግዱፈ በበዳ”
(የመንፈስ ቅዱስ ምክር በወሰዳት ጊዜ ኤልዳ ወደ ተባለች
የሕይወት ምድር የኼደች ለኾነች ለዕሌኒ ሰላምታ ይገባል፤
በአደባባይዋ ፊት መስቀ ልን በመንካት የዳነውን በድን በበረሓ
ወድቀኽ የተገኘኽ አንተ እንግዳ ከወዴት ነኽ አለችው) በማለት
መስቀሉ ከወጣ በኋላ ስለተደረገላት ተአምር ጽፏል፡፡
አመት አመት ያድርሰን ።