ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
#gitemsitem #poetic_saturdays #ግጥም_ሲጥም #ግጥማዊ_ቅዳሜ #seifetemam

ህመሜን ላጣጥም
-----------------------
እስቲ ልንቆራጠጥ ተዉኝ ላቃስትበት
ህመሜን ላጣጥም እስክፈወስበት
እንዳትወጉኝ ማደንዘዣ
እንዳትሰጡኝ ማስታገሻ
በሰፊ አውታር መገናኛ
በብልጭልጭ መሸፈኛ
የዘመን ጎርፍ አግበስብሶ
በከሰተው መከወኛ
ከኔ በላይ ላያማችሁ
ከህመሜ ላይ ሰራርቃችሁ
በሽተኛ ስንኩል ሳለሁ
አታፍጥኑት ሞቴን ካለው
እያላችሁ ጤነኛ ሰው
ልዳን እንጂ አታስታግሱኝ
ተዉኝ ተዉኝ ልንቆራጠጥ
ላተኩሰው ሆዴ ይቁረጥ
እራሴ ይምታ አይኔ ይበጥ
ሰው አድርጉኝ የሚሰማው
ከራሱ ጋር የሚታደም
በሽታዬን ካልተቀማሁ
በህመሜ ነው የምታከም

ሰይፈ ተማም 2009
ምታት ምታት አለኝ፤ እራስ እራሴን
ከፍ ዝቅ አረገኝ፤ አንጀት አንጀቴን

ዞር ዞር እላለው፤ እንደነኩት መሪ
ጎንበስ ጎንበስ እኔው፤ ደርሶ እንደአፋሪ

ቅልሽልሽ ቅልሽልሽ ፤ ቂም እንዳረገዘ
ድንብርብር ድንብርብርብር፤ ሰርቆ እንደተያዘ

መሀል አየት ፤ ጥግ ለየት
ድንገት ፍክት፤ ወድያው ጥፍት

ደሞ ልስልስ፤ ከዚያ ውል'ፍት
አይቶ ክስስ፤ ሰምቶ ምልስ

አውቆ መርሳት፤ ጥሎ ማንሳት
ይህን መንካት ፤ ያን ማንኳኳት

ትቶ መተው፤ ቂሎ ማቄል
ስሎ ማሾል፤ ስቶ ማ'ሴት

እንዲህ እንዲያ፤ እንዲያ እንዲህ
እዚህ እዚያ ፤ እዚያ እዚህ

እኔን ያደርገኛል፤ እኔ አደርገዋለው
ዛሬ ይሆነኛል፤ ዛሬን ሆነዋለው
ነገን ይተወኛል፤ ትላንትን ትቻለው።

ዛሬ
ዛሬ ይሆነኛል፤ ዛሬን ሆነዋለው
ነገን ይተወኛል፤ ትላንትን ትቻለው።

ርብቃ ሲሳይ @Ribki
#ግጥምሲጥም #ግጥማዊ_ቅዳሜ #ርብቃ_ሲሳይ
Forwarded from Seifu
#እባካችሁ_ለቢኒ__እንድረስለት!!
BINI ቢኒን እዚህ መንደር የምታውቁት እና ስለ #Poetic_Saturdays ፖኤቲክ ሳተርዴይስ (#ግጥማዊ_ቅዳሜ) የጥበብ ምሽትን በአካልም ሆነ በኦንላይን የታደማችሁ፣ እንዲሁም ለሰዎች ፈጥናችሁ የምትራሩ ሁሉ ደጋጎች ሁሉ #ስለ_ቸርነታችሁ_ትለመናላችሁ!!!

ለብዙዎቻችን መሰባሰቢያ የነበረውንና በፈንዲቃ የባህል ማዕከል ሲዘጋጅ የነበረውን የጥበብ ምሽት ሲያስተባብርና ደፋ ቀና ብሎ ሲያገለግል የነበረው ባለብሩህ ፈገግታው እና ትሁቱ ወንድማችን ቢኒ ከ"#ብሬይን_ቲዩመር" ጋር እየታገለ ይገኛል። ... በአገር ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ቀዶ ጥገና የተደረገለት ቢሆንም፣ ... በፍጥነት ወደ ሕንድ አገር ሄዶ መታከም ይኖርበታል!!!...

• ፈጣሪ ጨርሶ እንዲምረው በጸሎታችሁ አግዙት! አቅማችሁ የፈቀደውን በሁለት ወዳጆቻችን ስም በተክፈተው በቀጣዩ አካዉንት እርዱ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000529173435

ከአገር ውጭ ያላችሁ ወዳጆች በክሪስ አማካኝነት በተከፈተው የgofundme አካዉንት እገዛችሁን አድርጉ።

https://gofund.me/da6fcd7f
👍6