ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.84K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ምታት ምታት አለኝ፤ እራስ እራሴን
ከፍ ዝቅ አረገኝ፤ አንጀት አንጀቴን

ዞር ዞር እላለው፤ እንደነኩት መሪ
ጎንበስ ጎንበስ እኔው፤ ደርሶ እንደአፋሪ

ቅልሽልሽ ቅልሽልሽ ፤ ቂም እንዳረገዘ
ድንብርብር ድንብርብርብር፤ ሰርቆ እንደተያዘ

መሀል አየት ፤ ጥግ ለየት
ድንገት ፍክት፤ ወድያው ጥፍት

ደሞ ልስልስ፤ ከዚያ ውል'ፍት
አይቶ ክስስ፤ ሰምቶ ምልስ

አውቆ መርሳት፤ ጥሎ ማንሳት
ይህን መንካት ፤ ያን ማንኳኳት

ትቶ መተው፤ ቂሎ ማቄል
ስሎ ማሾል፤ ስቶ ማ'ሴት

እንዲህ እንዲያ፤ እንዲያ እንዲህ
እዚህ እዚያ ፤ እዚያ እዚህ

እኔን ያደርገኛል፤ እኔ አደርገዋለው
ዛሬ ይሆነኛል፤ ዛሬን ሆነዋለው
ነገን ይተወኛል፤ ትላንትን ትቻለው።

ዛሬ
ዛሬ ይሆነኛል፤ ዛሬን ሆነዋለው
ነገን ይተወኛል፤ ትላንትን ትቻለው።

ርብቃ ሲሳይ @Ribki
#ግጥምሲጥም #ግጥማዊ_ቅዳሜ #ርብቃ_ሲሳይ