ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ሲያምር - ሲያስጠላ (ሲያስጣምር)
---------------------------------
ውበትሽ ሲያስጠላ - ውበትሽ ክፋቱ
ፈገግታሽ አይገባ - ልብሽ ላልገቡቱ፡፡

ዐይንሽ ሲመነጥር - ነፍስያን እ’ያየ
ጣትሽ ያሳምማል - ልብ እያበራየ!

ውበትሽ ሲያስጠላ - ማማርሽ ሲያስጠላ
እውነቱን ሸሽጎ - በውሸት የሚያጣላ፡፡

. . . ደሞስ ይሄ መርገም
መጥላት ይሉት መክሰም
ስንቱን አስጠልቶ
ስንቱን አስጠልሽቶ!
‘ሚሰራው ሲያሳጣው - የሚያረገው ሲያጣ
እንዴት ባንዷ ባንቺ - በውበትሽ ይምጣ?!
. . .
‘ውበትሽ ሲያስጠላ!’ - ያስባለን ያ… መጥላት
በራሱ እንዳያስረን - ነገር ተሳክቶለት
አዙረን አየነው - አየነው በዙረት

እንኳንስ ፈገግታሽ እንኳን አይንሽ እና እንኳን'ና ጣትሽ
. . . ማስጠላትሽ ሲያምር - ሲያምር ማስጠላትሸ!

ሰይፈ ተማም 2012
#ግጥም_ሲጥም #ሰይፈተማም #poetic_Saturdays #ሰይፉ_ወርቁ_አ.