ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
"አሜን" በሉ!
(ሰይፉ ወርቁ)

° ° °........
ፀሐይ ባለበት ሁሉ፣
የትም "ጥላዎች" አሉ፤
የሚያለቅሱ ድፍርስ ዐይኖች፣
ድፍርስ ብርሃን ያያሉ!
•••
ግርዶሾቹ ምን ቢያይሉ፣
አማኞች "አሜን" ይላሉ!
ፀሐይ በሣቀች ጊዜ፣
ደመናዎች ይቀልጣሉ!
••
አማኞች "አሜን" ይላሉ፤
አሜን ያሉ ይሥቃሉ፤
የኮኮብን ትልቅነት፣
በግርዶሾች ልክ ያውቃሉ!
°°° ....

#ሠይፈ__ወርቅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #tba #tibebbeadebabay #tibeb2020 #artinaddis #digitalartfestival
#ትሁት_ካልሆንክ_ጠቢብ_አይደለህም!
• እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ትሁት ካልሆንክ #ጥበብን_አታውቃትም__ጥበብም_አንተን_አታውቅህም
...
ጠቢብ የብርሐን ተምሳሌት ነው። ብርሐን ተፈጥሮው መብራት ነው። ፀሐይ የምትለየው በብርሐኗ ለሌሎች መትረፍ ነው። በመስጠት። ፅልመትን በመግፈፍ። የጠቢብ ባህርዩ የሌሎችን መልካምነትና ውበት ገላልጦና አጋልጦ ማሳየት ነው።

ፀሐይ ፅልመትን ስትገፍ፣ 'ጀብድ ሰራሁ' ብላ አትዘግብም። ጮሃም አትናገርም። ቅንነት ተፈጥሮዋ ነውና። ጠቢብም የልቦና ብርሐን ነውና፤ የሌሎችም ፅልመት በቅንነት ብርሐኑ፣ በፍቅር ፀሐዩ ገልጦ ውበታቸውን ያጎላል እንጂ ስለ ፅልመታቸው እየተረከ ገናናነቱን አይዘግብም።

መጀመሪያ ሰው ሆኖ መቅረብ ይቀድማል። ከዚያም ፍቅርና ብርሐናችንን መግለጥ። በፍቅርና በብርሐናችን ሁሉን ማቀፍ መቻል። ለሁሉ ማብራት፤ ሁሉን ማክበር። እኛ ብርሐን ነን አንልም። ሌሎች በብርሐናችን ያውቁናል እንጂ። እኛ ስለሰዎች ፅልመት አናወራም። ሰዎች ስለብርሐናችን ኃይል ይናገራሉ እንጂ።

ጠቢብነት በትህትና ይመዘናል። ሌሎችን አክብሮ በመውደድ ኃይል። ሁሉን መቀበል፣ ሁሉን መውደድ በመቻል ኃይል።

ጠቢብ ድክመት ነቃሽ አይደለም። ደካማውን አበርቺ፣ የተሰወረውን ጥንካሬ ነቅሶ አውጪ እንጂ። በትችት አይጠመድም። በማሳነስ ገዝፎ ለመታየትም አይሞክርም። ማግዘፍ እንጂ ማኮሰስ የባህርይ ገንዘቡ አይደለም።

ጠቡብ ቡድን የለውም። ፀሐይ መንደር መርጣ፣ ያ ክፉ ያኛው ደግ ብላ አዳልታ እንደማታበራ ሁሉ። ለበዳይም ለተበዳይ፣ ለገፊም ለተገፊም በእኩል ብርሐኗን ትለግሳለች። ተፈጥሮዋ መስጠት ብቻ ስለሆነ። #ትህትና

እውነት እውነት እልሃለሁ። ሰዎችን የምትጠላ፣ የምታበላልጥና ስህተታቸውም ነቅሰህ በጎአቸውን የምትጋርድ ከሆንክ፣ ጥበብን አታውቃትም፤ ጥበብም አንተን አታውቅህም።

#ትህትና__ትህትና
#የግዝፈቶች_አክሊል_የቅንነት_ካባ
#ባክህ__ልቤ_ግባ!

#ፍቅር_በሌለበት_ጥበብ
#ጥበብ_በሌለበትም_ፍቅር_የለም

ጠቢብ መጀመሪያ ሰው ነው። መጀመሪያ የሁሉ ወዳጅ። ሁሉን አክባሪ። ሁሉን አበርቺ። ሁሉን አግዛፊ። ሚዛኑ ለሐሜት የማይታዘዝ። ልቡ ለአድልዎ የማይታጠፍ። የእነእገሌ አደግዳጊ፣ የእነእገሌ ጠላት አይደለም። የጠቢብ ነፍስ ጥላቻን ትጠየፋለች። የጠቢብ ልብ ከፍቅር በቀር አይዘምርም። የጠቢብ ዐይኖች ከፅልመት ውስጥ ብርሐንን፣ ከድክመት ውስጥ ብርታትን፣ ከጥመት ውስጥ ቅንነትን፣ ከፀያፍ ውስጥ ውበትን መንጥረው ያያሉ።

ጠቢብ ሁሉን ያለ ጥቅም ይወዳል። ተሥፋን፣ ፍቅርን፣ ክብርን፣ ነፃነትን ይለግሣል። ለማቅናት አያፈርስም፤ የፈረሰውን ያቀናል እንጂ። ለመወደድ አይወድም። ለመቀበል አይሰጥም፤ መውደድ ሰጥቶ መውደድ ይበዛለታል እንጂ።

ጠቢብ ውዳሤ ከንቱን ይፀየፋል። በማዕረግ አይታሰርም። በስምና በክብር ኬላ ከሰዎች መነጠል አይፈልግም። የትም፣ እንዴትም፣ ከማንም፣ ከምንም፣ ሁሌም ሰው አክሎ መገኘት ይችልበታል። ጎዝጉዙልኝ፣ አንጥፉልኝም አይልም። በተገኘበት ድባቡ ይነግሣል እንጂ። ፍቅሩ፣ ትህትናውና አክብሮቱ በመገኛው አድባር ያደርጉታል እንጂ።

ጠቢብ ዋርካ አይደል? ሁሉን ሰብሳቢ። በግዝፈቱ የሚያስመካ። በቅርንጫፎቹ የሚያስጠልል። ጥላ የሚሆን፣ የሚያሳርፍ፣ ተራማጁንም፣ በራሪውንም፣ ተሳቢውንም፣ አመንዣጊውንም፣ ሁሉን የሚያስጠጋ - ዋርካ ጠቢብ አይደል? ጠቢብም ዋርካ። ነፋስ የማይጥለው ሥሩ ጥልቅ፤ ዝናብ የማይጥለው ግንዱ ጥብቅ።

ትሁት ካልሆንክ ጥበብ ትጠየፍሃለች። ፍቅርም፣ ፍትህም ብርሐንም አይበቅሉብህም።

#ትህትና_ትህትና
#የግዝፈቶች_አክሊል__የቅንነት_ካባ
#ባክህ_ልቤ_ግባ!

#ሠይፈ__ወርቅ
#ስንት__ሞት__ይበቃል ?!
(ወደ ኋላ 1 ዓመት በፊት ምን ጽፈን ነበር...)
....
#ስንት__ሞት__ይበቃል ?
ስንት ደም?
ስንት አጥንት ?
ስንት ግፍ ?
ስንት ዋይታ ?
ስንት ህመም፣ ኡኡታ ?
ስንት በደል፣ ስቃይ ?
ስንት እሳት፣ ስንት ዋእይ ?
ስንት ቀስት፣ ካራ ?
ስንት ጦር፣ ገጀራ ?
ስንት ዱላ፣ ጥይት ?
ስንት ብረት፣ አለት ?

ስንት ዜና፣ አዋጅ?
ስንት ሺ መግለጫ ?
ስንት ፖለቲካ ?
ስንት ወሬ፣ ላንቲካ ?
ስንት ስድብ፣ ሐሜት ?
ስንት ባዶ ትችት ?

ስንት እንቅልፍ ዝንጋዔ
ስንት ዖም ሱባዔ ?
ስንት ሽምግልና ?
ስንት "ሽንግልና" ?
ስንት መለማመጥ ?
ስንት ሸር'፣ ማላገጥ ?

ስንት አዋጅ፣ መግለጫ
ስንት ሆታ፣ ፉከራ ?

ፍትሕ እስኪ'ሠራ'
(ወይ ገዳይ እስኪራራ')

ስንት ሰው ይወድቃል ?
ስንት ሞት ይበቃል ?

ምን ነበር ባወቅን ?
ተጣጥበን፣ ተጣጥነን - ሞትን በጠበቅን!!
.................................
( #ሠይፈ__ወርቅ )
•••• ••••• ••••• ••••• ••••• •••••
ዕረቡ - ታኅሣስ 15/2013 ዓ.ም

https://www.facebook.com/seifu.worku.7
👍3