#ብሔራዊ_የመጽሐፍ_ቅዱስ_ሳምንት
#National_Bible_Week
ሐሙስ, መጋቢት 15 2014 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በወንጌል ተልዕኮ እና ቲዎሎጂ መምሪያ ሥር የቋንቋ ልማት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እና የቅዱሳት መጻሕፍት አጠቃቀም አገልግሎት ክፍል ከቤተክርስቲያኑ ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል ጋር አጭር ሴሚናር አካሂዷል።
በስብሰባው ወቅት፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ታሪክ ውስጥ የነበራት የላቀ ተሳትፎ፣ እና አሁን በመሪነት ያላት ተሳትፎ፣ ቤተ ክርስቲያን የቋንቋ ማህበረሰቡን የእግዚአብሔርን ቃል በልባቸው ቋንቋ ለመድረስ እያደረገች ያለው ትጋት እና ለዚህ አገልግሎት ዘላቂነት እየተሠራ ያለው የፕሮጀክት ሃሳብ ቀርቧል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ 17ኛ ካውንስል ሰኔ 21 ቀን "ብሔራዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ሳምንት" ተብሎ እንዲከበር መወሰኑን ለስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባላት ይፋ አድርጓል።
©The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus