የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.36K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#አስቸኳይ_መግለጫ

#መብታችንን_መጠቀም_የማንንም_ደጅ_መጥናት_አስፈላጊ_አይደለም
#ጥቅም_ስላላገኙበት_ሊያስረክበን_ያልቻለው_የአዲስ_አበባ_ከተማ_የመሬት_ማናጅመት_ጽ/ቤት ነው።

የተከበራችሁ የሚዲያ አካላት በቅድሚያ ስለተገኛችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን
የዛሬው መግለጫ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያት ካውንስል የቦታ ጉዳይ ላይ መግለጫ የምንሰጥ ሲሆን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በአዋጅ የተሰጠውን ከፍተኛ አላፊነት ለማስፈጸም አንዲረዳው ካለው ተደራሽነትና ከሚሰራቸው ከፍተኛ የማህበራዊ ስራዎች አንጻር ታይቶ 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ እንዲሰጠን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ተወስኖ መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

ይህንንም ውሳኔ ላስተላለፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አባላት ከፍተኛ ምስጋና ያለን ሲሆን ክብርት ምክትል ከንቲባም ወደ አመራር ከመጡበት ቀን ጀምሮ በሕዝቡ የተጣለባቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት በታማኝነት እና በትጋት በመወጣት ባለባቸው አገራዊ ሀላፊነትና የስራ ጫና ላይ ጨምረው ይህ ጉዳይ እንዲፈጸም ያላሰለሰ ጥረት እንዳደረጉ ስለምናወቅ ለክብረት ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ለካቢኔያቸው ምስጋናችንን ሳላቀርብ አናልፍም፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአገር ውስጥ እና በመላው አለም የሚገኙ የወንጌል አማኞች ይህ ቦታ እንደተሰጠ ሲሰሙ እግዚአብሔርንም በጋራ አመስግነን በቦታው ላይ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችንም ስላዘጋጀን ጉዳዩ የት ደረሰ ፤ ፕሮጀክቶቹ መች ይጀመራሉ ፤ የመሰረት ድንጋይ መች ይጣላል ፤ በእርግጥ የተወሰነልን 20ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ተሰጥቶናል ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች በስፋት ሲነሱ ቆይተዋል፡፡

ለዚሁም ምላሽ እንዲሆን በሂደት ላይ ነው በማለት ስንመልስ የቆየን ሲሆን ዛሬ ላይ ግን ጉዳዩ ያለበትን ሁኔታ ማሳወቁ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የዛሬው መግለጫ እንዲሰጥ ተደርጎአል፡፡

ኢትዮጵያ የሁላችን አገር ናት ስንል በምክንያት ነው፡፡ በህገ መንግስቱ የተሰጠንን መብታችንን ማንም ሊቆርስብንና ሲፈልግ ሊሰጠን ሲያሻው ደግሞ ሊከለክለን አይችልም፡፡ ካውንስሉ በህግ የተቃቋመ ተቋም እንደ መሆኑ መጠን ከሚወክላቸውን ቤተ እምነቶችና ሕብረቶች ቁጥር አንጻር ሲታይ ይህ ግዙፍ ተቋም መብቱ ሊከበርለትና ጥያቄው በህግ እና በአግባቡ ሊመለስለት ይገባል ብለንም እናምናለን፡፡

በዚህ ምክንያት መብታችንን ለመጠቀም የማንንም ደጅ መጥናት አስፈላጊ አይደለም በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ከፍተኛ በደል ያደረሰብን እና በካቢኔ የተወሰነልንን ቦታ በተደራጀ እና በተቀናጀ አሰራር ጥቅም ስላላገኙበት ሊያስረክበን ያልቻለው የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ማናጅመት /ቤት ሲሆን

ለዚህ ደግሞ ተደጋጋሚ ለአንድ ዓመት ያህል ደጅ ጠንተን ሊሰማን የሚችል ሰው ባለማግኘታችን እና እጅግ የተደራጀ አካል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ማነጅመነት /ቤት ውስጥ ያለ ሲሆን የሚፈልጉትን ተቋም ወይም ግለሰብ ጉዳዩን በአንድ ሳምንት ውስጥ ጨርሰው ቦታውን አጽድተው ካርታ ሲያስረክቡ ያልፈለጉትን ደግሞ ደጅ በማስጠናት ህዝቡ በመንግስት ላይ እንዲያጎረመርም ፤ ህዝቡ ከመንግስት ጋር ግጭት እንዲፈጥር ሆን ብለው እየሰሩ በመሆናቸው ይህ አደረጃጀት ደግሞ ከከተማው መሬት ማነጂመንት ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ የተቀናጀ መሆኑን ተመልክተናል፡፡

እንደ ካውንስል በካቢኔ የተወሰነልንን 20ሺህ ካሬ ቦታ ስንጠይቃቸው 10ሺውን አዘጋጅተናል ቦታው ላይ ያሉ አካላት ግን ለመልቀቅ ፍቃደኛ አይደሉም ስለዚህ ጉዳዩ አስቸጋሪ ነው ቀሪውን 10ሺህ ካሬ ደግሞ ለመስጠት ቦታ የለንም ብለው በቅርቡ ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመሬት ማነጅመነት /ቤት ካቢኔ የወሰነውን ውሳኔ ማስፈጸም ሲገባው ቦታ የለኝም ካለ እና በአንድ ቀን በአንድ ቃለ ጉባኤ የተወሰነውን ለሌላው ሰጥቶ የካውንስሉን ቦታ ከከለከሉ ይህ ታስቦበት እየተሰራ ያለ የመንግስትን መዋቅር በመጠቀም የግል አጀንዳቸውን በማስፈጸም በተገልጋዩ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ በደል የሚያደርሱ አካላት በህግ ሊጠየቁ የከተማ አስተዳደሩም ህጋዊ እርምጃ ሊወስድባቸው ይገባል።

በቀጣይ የአዲስ አበባ አስተዳደር ም/ከንቲባ በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመምከር ለጥያቄያችን አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጠን እየጠየቅን ይህ ቦታ የአንድ ግለሰብ ወይም የአንድ ቤተ እምነት ሳይሆን የመላው የወንጌል አማኞች የአገሪቱ 1/3ኛ ቁጥር የሚወክል ተቋም ጥያቄ በመሆኑ ወንጌል አማኙ መብቱን በጋራ ማስከበር አስፈላጊ በመሆኑ ጥያቄው እስኪመለስ ድረስ በምናደርገው ጥረትና ሂደት ላይ ከጎናችን እንድትቆሙ ድምጻችን በጋራ እንድናሰማ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል /ቤት

ለአዳዲስ የካውንስሉ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://tttttt.me/EGBCC

አዲሱን የፌስ ቡክ ገፃችንን ላይክና ፎሎው በማድረግ ይከታተሉን:: https://www.facebook.com/ETGBCC

አዳዲስ ካውንስሉን የቪዲዮ መልዕክቶችን ለመከታተል የዩቱብ ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCJogO8wWASAthyoScuiYuwQ?view_as=subscribe

የinstagram https://www.instagram.com/ethiopiancouncilbelievers1208/?

እና Tiktok አካውንታችን ቤተሰብ ይሁኑ!!! https://www.tiktok.com/@etgospelbelieverscouncil?lang=en

የቲውተር ገጻችንን ይከተሉ!!! https://twitter.com/CouncilGospel