#የወንጌል_አርበኛ_አባባ_ባንጫ_ያያ_ወደ_አገለገሉት_ጌታ_በክብር_ተሰብስበዋል።
የወንጌል አርበኛ የነበሩት አባባ ባንጫ ያያ "ቃለ ሕይወት" የሚለውን ስያሜ የሰጡ እና አባባ ባንጫ ያያ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የመጀመሪያ ዋና ፕረዝዳንትም ነበሩ።
አባባ ባንጫ የተወለዱት በዎላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ሞኮኒሳ ወይጌ ቀበሌ ነበር። ወንጌል ወደ ዎላይታ በ1919 ዓ.ም ሲገባ እርሳቸው የ 32 ዓመት ወጣት ነበሩ።
አባባ ባንጫ ያያ "ቃለ ሕይወት" የሚለውን ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰጥተዋል።እንዲሁም "ወልድ ያለው ሕይወት አለው" የሚለዉ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን መሪቃል በተከፈተ መጽሐፍ ላይ "logo" ወይም አርማ እንዲሠራ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀሳብ የሰጡም ናቸው።
አባባ ባንጫ በዎላይታ ቀጣና የጫራቄን ክፍለ ማህበርን ከ 40 ዓመታት በላይ በዋና ጸሐፊነት አገልግለዋል።
ከእርሳቸው በኋላ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆን የቻሉ የወንጌል አርበኛ አባቶች እነ ሾንጋንና ዳልኬ የመሳሰሉትን የሰበኩ እና የጠመቁም ነበሩ።
የክርስቶስን ወንጌል ከዎላይታ ውጭ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ዞረው ሰብከዋል።በኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ/ያን የበላይ ጠባቂ ሆኖ ሌሎች በእርሱ ስር እንዲተዳደሩ የወጣውን አዋጅ የተቃወሙ ጀግና አባት ነበሩ።
በዚህም ምክንያት በቀዳማዊ ኃይሌ ስላሴ ዘመነ መንግሥት ታስረዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተንገላተዋል። አባባ ባንጫ ያያ በፖለቲካውም ዘርፍ በመሳተፍ የቀድሞ ዎላይታ አውራጃን መርተዋል።አባባ ባንጫ በተወለዱ በ 137 ዓመታቸው ወደ አገለገሉት ጌታ በክብር ተሰብስበዋል።
የዝግጅት ክፍላችን እግዚአብሔር ለመላው ለኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተሰቦች እና ለዎላይታ ቀጣና አገልጋዮች እንድሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል ።

❤43👍13😢4🔥1