የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.61K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ቤዛ_ኢንተርናሽናል_ቸርች_የ2017_ዓ_ም_የአፍሪካ_ተነሺ_ኮንፍረንስ_ተጀመረ

የቤዛ ኢንተርናሽናል ቸርች ከ16 ዓመታት ቆይታ በኋላ አዲስ የአምልኮ አዳራሽ ወይም የአፍሪካ አምልኮ ማዕከል በይፋ ተጀምሮዋል።

የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ቤተ መንግስቱ ይህ የአካባቢ ለውጥ ብቻ አይደለም የእግዚአብሔር ታማኝነት ሙላት እና ለቤተ ክርስቲያናችን አዲስ ወቅት ነው።ወደዚህ አዲስ ጅምር ስንገባ፣ ከየት እንደመጣን እናስታውሳለን ጉዞው በትንሽ የቤት ውስጥ መሰባሰብ የጀመረው እና አሁን ወደዚህ አስደናቂ ጊዜ መርቶናል። በነገር ሁሉ የረዳንን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ታሪካችን የእምነት፣ የመለወጥ እና የማይካድ የእግዚአብሔር በህይወታችን የመገኘት ማስረጃ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሐፊ ቄስ ደረጀ በመገኘት በዚህ ሁሉ አመታት ውስጥ በነገር ሁሉ የረዳቸውን እግዚአብሔርን በማመስገንና “ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”ሐጌ 2፥9 የለውን የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብ ጸሎት አደርገዋል።

በተገነባው የአምልኮ አደራሽ ውስጥ ከየካቲት 2/2017 . የተጀመረው ተነሺ አፍሪካ እስከ የካቲት 6/2017 . የሚቀጥል እንደሆነና የአብያተክርስቲያናት መሪዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች እና አብረዉ በስራ ሲደክሙ የነበሩ የቤተክርስቲያን አባላት በተገኙበት የአምልኮ አዳራሽ በድምቀት ይመረቃል።
👍5🙏43