#የኢትዮጵያ_የሃይማኖት_ተቋማት_ጉባኤ_በስልጤ_ዞን #ቅበት_ከተማ_በነዋሪዎች_መካከል_የተፈጠረውን_አለመግባባት_ለመቅረፍ_እየሰራ_መሆኑን_ተገለጸ።
ጉባኤው፤ አለመግባባቱ ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ ችግሩን ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አንስቷል፡፡
ረዕቡ ዕለትም የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለን ጨምሮ ሌሎችም የጉባኤው ከፍተኛ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮችን፣ በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ የሚገኙ ሀዘንተኛ ቤተሰቦችን እንዲሁም በሕክምና ላይ የሚገኙ ተጎጂዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ጉባኤው፤ ለተፈናቃዮች እና ለተጎጂዎችም የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የተፈጠረውን ችግር በውይይት እና በቀደመ የአብሮነት ባህል መፍታት እንደሚገባ የተናገሩት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ የኅብረተሰቡ ፍላጎት በጋራ መኖር እንጂ መለያየት አለመሆኑን በጉብኝታችን መረዳት ችለናል ብለዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች ለዓመታት በመከባበር የኖሩ መሆናቸውን ያነሱት ጠቅላይ ጸሐፊው፤ ቅራኔ የሚፈጥሩ ነገሮችን ከማባባስ ይልቅ አንድነትን በሚያጠናክሩ መንገዶች ላይ ለመወያያት ዝግጁ ስለመሆናቸው አሳውቀዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው የሚመለሱበት፣ የአከባቢው መስተዳድር ለተፈናቃዮች የህይወት እና የንብረት ዋስትና
ውይይቱ፤ ዛሬ ሀሙስ ዕለትም ቀጥሎ እንደተካሄደ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ አሳውቋል።

👍2