#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተ_ክርስቲያናት_ካውንስል_የሚዲያና_ህዝብ_ ግንኙነት_ ክፍል "የተሻለ ሚዲያ ለተሻለ አገልግሎት " በሚል ርዕሰ #ለሚዲያ_ባለሞያዎች_ያዘጋጀው_ስልጠና_ተካሄደ።
ሰኔ 15/2015 በማግኖሊያ ሆቴል በካውንስሉ የሚዲያ ኮሚሽን አባላት አስተባባሪነት በተካሄደው በዚህ ስልጠና ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ መገናኛ ብዙሃን የተጋበዙ የሚዲያ ተቋማት ሃላፊዎችና ባለሞያዎች ተሳትፈዋል ።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የካውንስሉ ፅህፈት ቤት ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ ባደረጉት ንግግር ስልጠናው በመንፈሳዊ ሚዲያዎች ዙሪያ በጎ አስተዋጽኦ እንደሚያመጣ እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
የሃገራችን ቀደምት የወንጌል አማኝ ቤተ እምነቶች የሚዲያ ታሪክና ያበረከቱትን አስተዋፅኦ እንዲሁም የወንጌል አማኝ ቤተ እምነቶች ወቅታዊ የሚዲያ አገልግሎት ዕድልና ተግዳሮቶች በተመለከተ በሚዲያ ኮሚሽን ም/ሰብሳቢ ወንድም ጌታቸው በለጠ ገለጻ ተሰጥቷል::
የሚዲያ ስነምግባር እና የሚዲያ ህግን በተመለከተ በመጋቢ እሸቴ በለጠ እና በዶክተር ማንደፍሮ እሸቴ ሰፊ ማብራሪያ ቀርቧል።
በሚዲያ ኮሚሽኑ አባላት በተዘጋጀው የኤዲቶሪያል ፖሊሲ ዙሪያም የሚዲያ ተቋማት ይህንን እንደምሳሌ ወስደው መርሆችና እሴቶቻቸውን እንዲቃኙ ይህንንም በማድረግ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ በማሳሰብ በሚዲያ ኮሚሽን ሰብሳቢ ሳራ ወልደአማኑኤል ጠለቅ ያለ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በቀጣይም ከተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የመንፈሳዊ ሚዲያ ባለሞያዎች ህብረት አስፈላጊነት ላይ በመነጋገር ህብረቱን ሊመሩ የሚችሉ ሰዎች ተመርጠዋል።
በመጨረሻም የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የመንፈሳዊ ሚዲያዎች አላማ ወንጌል ብቻ ይሁን የሚል መልዕክት ያሰተላለፋ ሲሆን ይህንን ስልጠና እንዲሳካ የካውንስሉ የሚዲያ ኮሚሽን አባላት ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጸኦ ከልብ በማመስገን ለተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/klDMYU768PU
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍1