#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_ድሬዳዋ_ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሳልቬሽን ቮይስ የወንጌል አገልግሎት ጋር በመተባበር 120 ለሚጠጉ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና አገልጋዮች #መንፈሳዊ_የአቅም_ግንባታ_ስልጠና ሰጠ።
በድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን አዳራሽ በተሰጠው በዚህ ስልጠና የእግዚአብሄር ራእይ በሚል ርእስ እግዚአብሔር የራእይ ባለቤት እንደሆነና አገልጋዮች የእርሱን ተልእኮ የመፈጸም አደራ እንዳለባቸው ትምህርት ቀርቧል ።
ስልጠናውን የሰጡት የሳልቬሽን ቮይስ ሚኒስትሪ መስራች እና መሪ የሆኑት ሐዋርያው መክብብ ሙላቱ ሲሆኑ በስልጠናው የተካተቱ ሐሳቦች ለጊዜው የሚያስፈልጉና ሕይወት ለዋጭ እንደነበሩም የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
በቀጣይም እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች ቢበራከቱ የአካባቢው የወንጌል እንቅስቃሴ እንደሚያግዝ ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል።
የድሬዳዋ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ቦርድ ሰብሳቢ ወንድም በላቸው ላምቦሮ ሳልቬሽን ቮይስ የወንጌል አገልግሎት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀው ሚኒስትሪው በድሬዳዋ ከተማ መንፈሳዊ ንቅናቄ የሚፈጥር እና በአይነቱ ልዩ የሆነ ከተማ አቀፍ ክሩሴድ ከጥቅምት 8- እስከ 11 ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
‘ሁላችንም ስለወንጌል አንድ ሆነን እንደ ተማርነው እንደ አንድ የክርስቶስ አካል ተልእኮአችንን ልንፈጽም ይገባል’ም ብለዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/SHjyVAQRTzU
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

👍1🙏1