የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.33K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከዋን_ኢን_ክራይስት_ኢንተርናሽናል_ሚኒስትሪ_ጋር_በመተባበር ከተለያየ አብያተክርስቲያናት ህብረት ለተወጣጡ አገልጋዮች #የአመራር_ዘይቤዎች በሚል ርዕስ በጉዲና ቱምሳ የመሰብሰቢያ አዳራሽ #ስልጠና ተሰጠ። ስልጠናዉ ግንቦት 29 እና 30 ቀን 2015ዓ/ም የሚከናወን ሲሆን ዛሬ በተጀመረዉ የስልጠና ጊዜ የካዉንስሉ መንፈሳዊ ዘርፍ ክፍል ሃላፊ ፓስተር ስንሻት ተካ ፕሮግራሙን በፀሎት አስጀምረዋል። ስልጠናዉን የተሰጠዉ ከሪል ላይፍ ሚኒስትሪ ከአሜሪካን ሃገር በመጡ ጥንዶች ሬቨረንድ እስቴሲ ኒኮል አና ሬቨረንድ ኢቫን ሲመንስ ሲሆኑ የዋን ኢን ክራይስት ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ የሚኒስትሪው ዳይሬክተሮች ናቸዉ።በስልጠናዉ አምባገነናዊ አመራር፣ጣልቃ የማይገባ አመራር፣የማህበራዊ እኩልነት አመራር፣ዉጣ ዉረድ የሚያበዛ አመራር እና የአሰልጣኝ አመራር በሚሉ ሃሳቦች ስልጠናዉ ተሰቷል። ኢቫንጀሊካል ቲቪ ያነጋገራቸዉ የስልጠናዉ ተካፋይ አገልጋዮች በስልጠናዉ ተጠቃሚ መሆናቸዉን ገልፀዋል።ስልጠናዉ ግንቦት 30 ቀን 2015ዓ/ም የሚጠናቀቅ ይሆናል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፦ https://youtu.be/tmelkKyRnYs
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍3
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል መሪዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ 500 ሚልዮን ችግኝ ለመትከል በታቀደዉ መሰረት #በአረንጓዴ_አሻራ_መርሃ_ግብር_ላይ_ተሳተፋ
ሃምሌ 10 ቀን 2015ዓ/ም የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር “በጉለሌ እጽዋት ማዕከል” ተካሒዷል።በተዘጋጀዉ መርሃ ግብር ላይ የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ ጨምሮ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች የመንግስት ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች የካዉንስሉ የክላስተር አመራሮች መምህራን እና ተማሪዎች በጉለሌ የህፅዋት ማእከል በመገኘት ነገን ዛሬ እንትከል በሚል መሪ ቃል አረንጓዴ አሻራቸዉን አኑረዋል።
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/5qQ3ixHS68c
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!