የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በቀጣና ሁለት ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን “የተዘጋጀ ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በሊደርሺፕ ትራንስፎሜሽን ሚኒስትሪ ከተለያዩ ቤተ ክርስቲያን ለተወጣጡ ወጣት መሪዎች ሴሚናሪ ተካሄደ።

በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን “አንድ የተዘጋጀ ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በሊደርሺፕ ትራንስፎርሜሽን ሚኒስትሪ ከተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት ለተወጣጡ ወጣት መሪዎች ሴሚናሪ ተካሂዷል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት መጋቢ ዳንኤል ሲሆኑ እንዲሁም በእለቱ ወጣትነት እግዚአብሔር ለሀገር እና ለቤተ ክርስቲያን ለለውጥ እና ለተሃድሶ ጠቃሚ እንደሆነ ተናግረው የወጣትነት ጊዜ በምን አይነት መንገድ መያዝ እንዳለበት አስተምረዋል።

መጋቢ ዳንኤል ወጣትነት በሰዎች እድሜ ውስጥ ወርቃማ የእድሜ ክልል እንደመሆኑ ወጣትነትን በሚገባ ለመጠቀም እና የእግዚአብሔርን ቃል ለማወቅ መትጋት ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

ቄስ ትዕግስቱ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 1 ላይ ከሚገኘው ክፍል ላይ በመነሳት ወጣቶች እንዴት ራሳቸውን ከሀጥያት ማራቅ እንዳለባቸው አስተምረዋል።

በከሰዓቱ ፕሮግራምም ላይ ወንድም ለማ ደገፋ ጥሪ ፣ ብቃት ፣ ስብዕና እና ተግባራት በተሰኙ በተለያዩ ርዕሶች ላይ ትምርህትን ሰጥተዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቃልኪዳን እንዳለ
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባ እና አካባቢው ክልል የወንጌል መስካሪዎች የአንድነት ፕሮግራም ተካሄደ።

ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም በሴሚሲ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ በተካሄደው የወንጌላውያን እና የወንጌል መስካሪ አገልጋዮች የአንድነት ፕሮግራም ላይ 118 አገልጋዮች ተገኝተዋል። በዘማሪ አላምረው ኢያሱ ዝማሬ ቀርቦ ጉባኤው እግዚአብሔርን አምልኳል።

በመቀጠል በክልሉ የወጣቶች ቤተሰብ አገልግሎት ፣ የወንጌል ስርጭት አገልግሎት ሃላፊ በሆኑት በመጋቢ ኤልያስ አየለ "መቼ እንደ ሐዋርያቶችሁ" በሚል ርዕስ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት አቅርበዋል።

የፕሮግራሙ አላማ አመቱን ሙሉ ወንጌልን ሲሰብኩ የቆዩትን አገልጋዮች ጌታ ስለረዳቸው ለማመስገን እና ለማበረታታት መሆኑን ታውቋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
3
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ለሲኖዶሶች የመንፈሳዊ መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገ።


የኢ/ወ/ቤ/መ/ኢ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ለመማር ማስተማር ሂደት እና ለአገልጋዮች የሚረዱ የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ለቤጊ ግዳሚ ሲኖዶስ (ቤጊ): ለቦረናና አካባቢው ሲኖዶስ (ያቤሎ): ለአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ (አዶላ ወዩ) በድጋፍ መልክ አበርክቷል። መጽሐፍቶቹም በየሲኖዶሶቹ ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት እና ምዕመናን አገልግሎት የሚውሉ መሆኑ ተገልጿል።

የመምሪያው ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ለቤተክርስቲያኒቱ ድጋፍ ያደረጉትን ተቋማትን ማለትም ራፊኪ ፋውንዴሽን (Rafiki Foundation) ፣ ሉተራን ሄሪቴጅ(Lutheran Heritage Foundation) እና ሌሎችንም በማመስገን ፣ መጽሐፍቶቹን ለቤተክርስቲያኒቱ ሴሚናሪዎች ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆች እና ት/ቤቶች ፣ እና ማ/ምዕመናን ጥቅም እንደሚውል እና ከተባባሪ ድርጅቶች ጋር በመሆን ድጋፍ የማድረጉ ስራ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
የደቡብ ኮሪያ የፕሮቴስታንት ሚሽን 140ኛ አመት ክብረበዓል ተከትሎ የኮሪያ ክርስቲያኖች ታሪክ እና ባህል ማዕከል በሀገሪቱ ዋና ከተማ ሴዎል ተከፈተ።

140ኛ አመት የደቡብ ኮሪያ የፕሮቴስታንት ሚሽን ክብረ በዓልን ተከትሎ የኮሪያ ክርስቲያን ታሪክ እና ባህል ማዕከል ነሐሴ 4 ቀን በሲዮል ኢዩንፒዮንግ አውራጃ ተከፍቷል። በብሔራዊ እና በከተማው ምንጮች ድጋፍ የተከፈተው ማዕከሉ 10 ቢሊዮን የደቡብ ኮሪያ ዎን አልያም 7.3 ሚሊዮን ዶላር የወጣበት እንደሆነ ተገልጿል።

ማዕከሉ ቋሚ እና ልዩ የኤግዚቢሽን አዳራሾች፣ መዝገብ ቤቶች እና የመማሪያ ቦታዎችን ያካተተ ነው። እና በማዕከሉ ውስጥ ለሕዝብ እይታ ከቀረቡት አርቴፋክቶች መካከል እ.አ.አ በ1906 ጥቃም ላይ የዋሉ የሚሽነሪ ፖስት ካርዶች፣ ቀደምት ካርታዎች እና የአዲስ ኪዳን ትርጉሞች ይገኙበታል።

ኤግዚቢሽኑም ከኮሪያ የክርስትና እምነት የእድገት ታሪክ በተጨማሪ ሀገሪቱን ዴሞክርሲያዊ ለማድረግ ፣ ማህበራዊ አገልግሎት ለመስጠት እና እና ባህልን ለማሳደግ ክርስትና የተጫወተውን ሚናም የሚያሳይ ነው።


የሲዮል ከተማ ከንቲባ የሆኑት ኦ ሴ ሁን በበኩላቸው ክርስትና ለኮሪያ ጤና አገልግሎት እና አጠቃላይ እድገትና ደህንነት መሰረት በመጣል ስላደረገው አስተዋጽዖ አመስግነዋል።

የማዕከሉ ዳይሬክተር የሆኑት ጃይ ሰንግ በበኩላቸው የማዕከሉ አላማ ለክርስቲያኖችም ክርስቲያን ላልሆኑ ሰዎችም ቤተ ክርስቲያን በማህበረሰብ ላይ ያሳደረቸውን መልካም ተጽዕኖ ማሳየት እንደሆነ ተናግረዋል።

መርሃ ግብሩም ሪቫን በመቁረጥ እና ማዕከሉ የእምነት እና የታሪክ አሻራ ሕያው ማሳያ መሆኑን ለማመላከት የ ችግኝ በመትከል ተጠናቋል።

መረጃውን ከክርስቲያን ዴይሊ ኢንተርናሽናል ድረ ገጽ አገኘነው

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ