በቼክ ሪፐብሊክ ዋና ከተማ ፕራግ “ለኢየሱስ እራመዳለሁ።” የተሰኘው የጎዳና ላይ ዝግጅት መካሄዱ ተገለጸ።
በየዓመቱ የሚካሄደው እና በዚህኛው አመት ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደው የአደባባይ ዝግጅት አምልኮ እና ጸሎት የተደረገበት እንዲሁም የእግዚአብሄር ቃል የተሰበከበት ነበር። ምንም እንኳን በየመሃሉ ዝናብ እያስቸገረ የቆየ ቢሆንም ከመላው ሀገሪቱ የመጡ አማኞች በከተማዋ አደባባይ በመገኘት የኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነት እና አዳኝነት አውጀዋል።
በሳልቬሽን ክሩ እና በሪች ዘ ወርልድ አገልግሎት አስተናባሪነት የተዘጋጀው ፕሮግራም በኮሎምቢያ እና በቪንዝዌላ ከተካሄዱት ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ጋር የሚስማማ ይዘት የያዘ ነበር። በቼክ ሪፐብሊክ በአገልግሎቱ የሚታወቀው ዘማሪ ጃን ክሪስቶፍ ጉባኤውን በአምልኮ የመራ ሲሆን መጋቢ ፒተር ኩባ እና ጃል ቮቶካ እና ህብረት ላይ መጠንከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
መረጃውን ከክርስቲያን ዴይሊ ኢንተርናሽናል አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

👍4❤2