የኢትዮጵያ ወጣት ክርስቲያኖች ማህበር የተመሰረተበት 21ኛ አመት በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ አከበረ።
የኢትዮጵያ ወጣት ክርስቲያኖች ማህበር የተመሰረተበት 21ኛ አመት በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ አክብሯል።
በሀገራችን በሁለንተናዊ አገልግሎቱ የሚታወቀው የኢትዮጵያ ወጣት ክርስቲያኖች ማህበር በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ባደረገው የ21ኛ አመት ክብረ በዓል ላይ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ጨምሮ የተለያዩ ወጣት አገልጋዮች እና ዘማሪዎች በስፍራው ተገኝተዋል።
በማለዳ የተጀመረው መርሃግብሩ ልጆችን የማጫወት እንዲሁም ደም የመለገስ መርሃግብርን ያካተተ ነበር።
ከሰዓት የነበረው መርሃግብርም አምልኮ ፣ የእግዚአብሔር ቃል ፣ የማህበሩ ድጋፍ የማሰባሰቢያ የተካሄደበት ነበር።
አርቲስት ሀገረወይን አሰፋ መድረኩን በመምራት ያገለገለች ሲሆን የማህበሩ የክብር አምባሳደር የሆኑት አርቲስት ሸዋፈራሁ ደሳለኝ በስፍራው በመገኘት የሰው ልጆችን ለማዳን ስለሰራው ስራ እግዚአብሔርን አመስግነዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በሀገራችን በወንጌል የቀደሙ አባታቾ እና እንደ ኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና እንደ ኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ያሉ ተቋማት ወጣትቾን በሰፊ ልብ እንዲያግዟቸው ጥሪ አቅርበው አባቶች በወጣቶች ያዘኑበት ነገር ካለም ወጣቶችን በመወከል አባቶችን ይቅርታ ጠይቀዋል።
ከዚህም ባለፈ በስፍራው መነባነብ የቀረበ ሲሆን የምስራቅ መሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ወጣት መዘምራን ፣ ዘማሪ መስፍን ጉቱ እንዲሁም ፓስተር እንዳለ ወልደ ጊዮርጊስ እንዲሁም ሌሎች በስፍራው በመገኘት ጉባኤውን በዝማሬ አገልግለዋል።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

የጽዮን ከተማ ሰራዊት የእየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አገልግሎት ከኢትዮጵያ ወንጌልን አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካወንስል እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር "ነሐሴን ለወንጌል እንዋጀዋለን "በሚል መሪ ቃል የመክፈቻ መርሐግብር አካሄደ።
ነሐሴን ለወንጌል በሚል መሪ ቃል የአንድ ወር የዲጂታል የወንጌል ስርጭት ሊከናወን ነዉ።
የጽዮን ከተማ ሰራዊት የእየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አገልግሎት ከኢትዮጵያ ወንጌልን አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካወንስል እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር "ነሐሴን ለወንጌል እንዋጀዋለን "በሚል መሪ ቃል የመክፈቻ መርሐግብር አካሂዷል።
የጽዮን ከተማ ሰራዊት የእየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አገልግሎት ከኢትዮጵያ ወንጌልን አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካወንስል እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በነሐሴ ወር የ30 ቀን የዲጂታል የቀጥታ ወንጌል ተልእኮ ዘመቻን በተመለከተ የመክፈቻና የምክክር መርሐግብር ነው ያካሄደው።
የጽዮን ከተማ ሰራዊት የእየሱስ ኮርስቶስ ወንጌል አገልግሎት ከኢትዮጲያ ወንጌላዉያን አብያተ ክርስቲያናት ካዉንስል ጋር በመተባበር የተለያዮ ስራዋችን በመስራት ይታወቃል።
በዚህ በመጨረሻ እና በዲጂታል ዘመን የእየሱስ ክርስቶስን የመንግስቱን ወንጌል በተለያዮ የዲጂታል የሶሻል ሚዲያ ማሰራጫ መንገዶች ማለትም በ ፌስቡክ፣ በዮቲዮብ ፣ በኢንስታግራም፣በቲክቶክ ፣በኢሜል ፣በፖድካስቶች እና በሌሎች አማራጮች ሁሉ በቀጥታ ስርጭቶች መስመር ላይ ለ30 ቀን የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል።
ሐምሌ 19/20017 ዓ.ም የፅዮን ከተማ ሰራዊት የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አገልግሎት ቤ/ክ ከወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካዉንስል እና ከአባል ቤተዕምነቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ከነሐሴ 1 - 30 የሚኖረዉን የቀጥታ የዲጂታል ወንጌል ስርጭት ዘመቻ አስመልክቶ ከሚዲያ አካላት እና ከአብያተክርስቲያናት መሪዎች ጋር ራዕይ የማካፈልና የምክክር ፕሮግራም ተደርጓል ።
ለመረሃ ግብሩ በፀሎት ፣ በመዘምራን ፣ በክትትል እና በዲጂታል ቡድን የሚያገለግሉ ጨምሮ 7 ግብረሃይል የተዘጋጀ መሆኑን የቤተክርስቲያን መሪዎች በመድረኩ ጠቅሰዋል።
ምሽት ከ12:00 - 2:00 በሚኖረዉ የቀጥታ የወንጌል ስርጭት በአንድ ወር ዉስጥ ለ1 ሚሊዮን ሰዎች የምስራቹን ለመንገር እና 3ሺህ ነብሳት ጌታን እንደ ግል አዳኛቸዉ አድርገዉ እንዲቀበሉ ለመስራት እቅድ እንደተያዘ ተናግረዋል።
በአለም ዙሪያ ያሉ አንድ ሚሊዬን አዳዲስ ነፋሳት (ትዉልድን) በወንጌል በመድረስ ታላቁ ተልዕኳችንን ለመፈፀም የታለመ ራአይ መሆኑ ተነግሯል።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ

❤5