የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.36K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኖርዌይ ቤተ ክርስቲያን የእርዳታ ድርጅት ጋር በመተባበር በበጀት ዓመቱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በዋናነትም ያለድሜ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛትን ከመከላከል አንፃር የተሰሩ ሥራዎችን የሚገመግም የምክክር መድረክ በጽሕፈት ቤቱ አካሄደ፡፡

ሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ/ም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሴቶች ወጣቶች እና ሕፃናት መመሪያ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ጥሩወርቅ የዕቅድ አፈፃጸም የምክክር መድረክ ዓላማ አስመልክተው ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በገባው ስምምነት መሰረት እንዲሁም ካለበት ሃገራዊ እና ሃይማኖታዊ ኃላፊነት አንፃር ከሰላም ግንባታ ሥራው ጎን ለጎን የሴት ልጅ ግርዛት እና ያለዕድሜ ጋብቻ ከመከላከል አንፃር የተሰሩትን ዋና ዋና ሥራዎችን፣ የተገኙ ውጤቶችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመድረኩ ተሳታፊዎች አካፍለዋል፡፡

በመቀጠልም የአባል የሃይማኖት ተቋማት ርዕሰ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሴቶች፣ ወጣቶች እና ሕፃናት መመሪያ ኃላፊ በበጀት ዓመቱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ከመከላከል አንፃር የሰሯቸውን ሥራዎች በዝርዝር በማቅረብ አንዳቸው ከአንዳቸው ልምድ እና የእርስ በእርስ ትምህርት መውሰድ የሚያስችላቸውን እድል መፍጠር መቻሉ ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት የሥራ አፈፃጸም ሪፖርቶች ላይ ሰፊ ምክክር ከተደረገ እና አስተያየት ከተሰጠ በኋላ በቀጣይ ከዚህ የተሻለ የተቀናጀ ሥራ በመሥራት የተሻለ ወጤት ማስመዝገብ እንደሚያስፈልግ በመግባባት የዕለቱ መድረክ የዕቅድ አፈፃጸም የምክክር መድረክ በታቀደው ዕቅድ መሰረት በስኬት መፈጸሙ ተገልጿል፡፡

መረጃው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ነው፡፡

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
1
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ በጋምቤላ ክልል ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች::

የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዝዳንት ፓስተር ላኮ በዳሶ በስፍራው በመገኘት ቤተ እምነቱን በመወከል በጋምቤላ ክልል ፑኮንግ ቀበሌ ውስጥ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖችው ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙትን ምግብ ነክ የሆኑ እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርገዋል።::

የቤተ እምነቱ ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት ቤተ እምነቱ ከመንፈሳዊ አገልግሎት ጎን ለጎን በተለያዪ አከባቢዎች ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመደገፍ በተለያዩ ሰብዓዊ አገልግሎቶች ላይ በንቃት እየተሳተፈች መሆንዋን ገልጸዋል።

“ አቅመ ደካሞችንና በተለያዩ ችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በመርዳትና በመንከባከብ ሰብዓዊ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል።” ሲሉም ተናግረዋል።

በተሰጠው የድጋፍ እቃዎች ውስጥ የእርሻ መሳሪያዎች ይገኙበታል። በአከባቢው ያለውን ለም መሬት እና የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም ከተረጅነት መላቀቅ እንደሚያስፈልግ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ይህንን ታሳቢ በማድረግ የእርሻ መሳሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ከድህነት ለመላቀቅ ብቸኛ አማራጭ ያለንን የተፈጥሮ ሀብት ተጠቅመን ማልማት ስንችል ነው" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለተግባራዊነቱ ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በጋምቤላ ቁጥር 3 ሙሉ ወንጌል አጥቢያ መጋቢ የሆኑት ፓስተር ወንድወሰን መሀመድ ስለተደረገው ድጋፍ እና ቤተክርስቲያኗ በተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎች ላይ በመሳተፍ የበኩሏን ድርሻ ስለተወጣች አመስግነዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
1
ዳይናሚክ ቸርች ፕላንቲንግ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በመተባበር ለ22 አገልጋዮች ሁለተኛ ዙር ስልጠና ሰጠ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የቤተ ክርስቲያን ተከላ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ዳይናሚክ ቸርች ፕላንቲንግ ኢንተንራሽናል ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ በመሆን ስልጠና ሲያዘጋጅ ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።

ከዚህ በፊት በመጀመሪያ ዙር በነበረው ስልጠና በሁለት ጊዜያት 22 አገልጋዮችን የቤተ ክርስቲያን ተከላን አስመልክቶ ስልጠና ሰጥቶ ነበር።
በሁለተኛ ዙር ላይ ባዘጋጀው ስልጠና ላይም ከዚህ በፊት የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና የወሰዱ 22 አገልጋዮች የተገኙ ሲሆን የአሁኑ ስልጠናም ትኩረቱን ያደረገው ደቀመዛሙርትን ማበራከት ላይ እንደሆነ ተጠቅሷል።

በዙም የተካሄደውን ስልጠና የሰጡትም የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና የሰጡት የዳይናሚክ ቸርች ፖላንቲንግ ኢንተርናሽናል መስራች አል ሚደልተን እና የአገልግሎቱ ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ሜሪሌይ ነበሩ።

ከማለዳው 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ 12 ሰዓት በሳሮማሪያ ሆቴል ሐምሌ 16 የተካሄደው ስልጠና ደቀመዛሙርትን ከማፍራት ጋር በተያያዘ ጠቃሚ ሀሳቦች የተነሱበት እንደሆነ ተገልጿል።

ዳይናሚክ ቸርች ፖላንቲንግ ኢንተርናሽናል ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ በመሆን ሁለት ዙር ስልጠናዎችን የሰጠ ሲሆን ከዚህም በኋላ ከአመራር ጋር በተያያዘ ሶስተኛ ዙር ስልጠና እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የውጪ ግንኙነት ዘርፍ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
2