“መጽሐፍ ቅዱሳዊ አመራር” “Biblical Leadership” በሚል ስያሜ 3ኛ ዙር የሥልጠና መርሐ ግብር ተጀመረ
በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር እና በእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ትብብር ተግባራዊ እየተደረገ ባለው ፕሮጀክት የተዘጋጀው ሦስተኛው ዙር የሥልጠና መርሐ ግብር ተጀመረ።
በስልጠናው ላይ ቁጥራቸው ከ50 በላይ የሆኑ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፥ ከሕግ ባለሙያዎች፥ ከከፍተኛ ትምህር ተቋማት፥ ከህክምና ሙያ ዘርፍ፥ ከምህንድስና ሙያ ዘርፍ እና ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ መሪዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
እኤአ 2023 ዓ.ም ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ተዋቅሮ እየተሰጠ ያለው ይህ ስልጠና “Catalyzing Leaders” በሚል ርዕስ የሚካሄድ ሲሆን ዓላማውም በተለያየ ደረጃ እና ሙያ ላይ የሚገኙ መሪዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ እሴቶችን በመጠቀም ለተሻለና ውጤታማ መሪ እንዲሆኑ መደገፍ ለዚህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እሴቶችን በግብአትነት እንዲጠቀሙ ማበረታታት መሆኑ ተግልጾዋል።
በስልጠናው ላይ ዓለም አቀፍ እውቅና ያለቸው መምህራንና የምርምር ባለሙያዎች በአሰልጣኝነት እየተሳተፉ ይገኛል።
መረጃው የኢትዮጵያ መጽሃፍ ቅዱስ ማህበር ነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፤ ቤተልሔም ደረጄ

❤12🙏3🔥2
የኢትዯጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከኦርጋኒክ ቸርች ፕላንቲንግ ሚኒስትሪ (Organic Church Planting Ministry) ጋር በመተባበር ለ53 አገልጋይ ሴቶች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ።
" መንፈሳዊ ጉዞን መገምገምና ወደ ክርስቶስ ማደግ፣ደቀመዛሙርትንም ማፍራት በሚል ርዕስ" ሐምሌ 17 2017 ዓ.ም. በጉዲና ቱምሳ ማሰልጠኛ ተቋም ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን መንፈሳዊ ህይወትን ለመመዘን መሰረታዊ የሆኑ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆዎችን መረዳት፣ ክርስቶስን ማእከል ያደረገ ህይወት የመኖር አስፈላጊነት እንዲሁም የታላቁ ተልዕኮን ሀላፊነት መወጣትና ደቀመዛሙርትን ማፍራት የአገልግሎት መርህ በስልጠናው የተዳሰሱ ሀሳቦች ነበሩ።
ስልጠናውን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የሴቶች አገልግሎት ኮሚቴ ያስተባበረ ሲሆን የኮሚቴው ሰብሳቢ ቄስ ፀጋነሽ አየለና ምክትል ሰብሳቢ መምህር ቀለሟ ተፈራ ስልጠናውን ሰጥተዋል። ዶ/ር ገዙ ሞሲሳ የኦርጋኒክ ቸርች ፕላንቲንግ ሚኒስትሪ ዳይሬክተር የእግዚአብሔርን ቃል በማካፈል የሚኒስትሪውን አላማ ያስረዱ ሲሆን መጋቢ ሮማን ሳሙኤል በዝማሬ አገልግለዋል።
የስልጠናው ተሳታፊ አገልጋይ ሴቶች ከቤተሰብ ጀምሮ ባሉበት ቤተእምነትና ማህበረሰብ ክርስቶስን በሚያሳይ የተለወጠ ማንነት እንዲኖሩ እንዲሁም ወንጌልን በመስበክና ደቀመዛሙርትን በማፍራት ጥሪያቸውን እንዲፈጽሙ ከሌሎች አገልጋይ ሴቶች ልምድን እንዲቀስሙ ያደረገ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም ይህንን በመተግበር ለሌሎች መልካም ምሳሌ በመሆን እንደሚተጉ ተናግረው፤ ይህን መሰል የልምድ ልውውጥና የስልጠና መርሃ ግብር በካውንስሉ የሴቶች አገልግሎት ኮሚቴ በመዘጋጀቱ አመስግነዋል።
መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል መንፈሳዊ ዘርፍ አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ