የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.51K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በሀዋሳ ከተማ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ስር የባለአደራ ትውልድ የታዳጊ ወጣቶች አገልግሎት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሄዱ።

3 ሺህ የሚሆኑ የ2017 ዓ.ም ስልጠና ተሳታፊዎች ከ25 አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የተውጣጡ የባለአደራ ትውልድ ሰልጣኝ ታዳጊ ወጣቶች በሀዋሳ ከተማ ጉዱማሌ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሄደዋል።

በሲዳማ ክልል የምትገኝው የአማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን በሀዋሳ ከተማ በጉዱማሌ ፓርክ በመገኝት ከ3000ሺ በላይ በሚሆኑ የባላደራ ትውልድ ሰልጣኝ ታዳጊ ወጣቶችና የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

ወጣቶቹ ለነገ የቤተክርስቲያንን ፣የራስን ፣የቤተሰብንና የሀገርን አደራን የሚቀበል ሀላፊነቱን የሚወጣ ትውልድን ለማፍራት ከሀምሌ 7 እስከ ሀምሌ 12 ለአምስት ተከታታይ ቀናት “የባለአደራ ትውልድ” በሚል የራዕይ ቃል በቤተክርስቲያኗ ስልጠናም ሲወስዱ ቆይተዋል።

በእለቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የፅዳትና የወንጌል ስብከት በከተማዋ እግር ጉዞም አካሂደዋል።

የባላደራ ትውልድ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ዋና አስተባባሪ መጋቢ ተክለአብ ማቴዎስ ስልጠናው 5ተኛ ዙር መሆኑን በመግለፅ በአመት ለሁለት ጊዜ እንደሚካሄድም ገልፀዋል።

የሀዋሳ አማኑኤል ህብረት መጋቢ የሆኑት መጋቢ ወንዶሰን ካሳ በእለቱ እንደተናገሩት “ስልጠናው እድሜያቸው ከ14 እስከ 18 ዕድሜ ክልል ያሉ ታዳጊዎች እንደሚሰጥ እና ቤተክርስቲያንም ሆነ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ስለሚያስፈልጋት ቤተክርስቲያንኗ ትውልድን የማዳን ፣የማብቃት፣የማፍራት ራዕይ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራንም ነው ።”ብለዋል።

መረጃውን አገልጋይ ፍፁም አዲሱ ከአማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ሀዋሳ አደረሰን

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአለም አቀፉ የሚሽን ማህበር ጉባኤ ላይ የእውቅና ሽልማት አገኘች።

በመካከለኛው አሜሪካ ሁንዱራስ እየተካሄደ በሚገኘውና ሁለተኛ ሳምንቱን በያዘው የአለም አቀፍ ሚሽን ማህበር (IMA) ጉባኤ እየተሳተፈች የምትገኘው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በመድረኩ በወንጌል ተልዕኮ እያከናወነች ላለው እንቅስቃሴና ከአሞር ቪንቪንቴ ቤተክርስቲያን ጋር ላላት አጋርነት የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላታል።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን በመወከል በስፍራው የሚገኙት የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ ሽልማቱን ሲቀበሉ "ይህ እውቅና ክርስቶስን ለመስበክ እና መንግስቱን በማህበረሰቦች መካከል ለመገንባት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ግሩም ማስታወሻ ነው።" ሲሉ ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ አክለውም አለም አቀፉ የሚሽን ማህበር ለወንጌል ስራ እንድንነቃቃ እያደረገ ስላለው አስተዋጽኦ አመሰግናለሁ ብለዋል።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በተለያየ አለም የሚገኙ አብያተክርስቲያናት በተካተቱበት አለም አቀፍ የሚሽን ማህበር (IMA) መስራች አባል መሆኗ ይታወቃል።
መረጃው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
3👍1