የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.7K subscribers
9.47K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
ኢንተርናሽናል ባይብል ቲኦሎጂ ኮሌጅ በድግሪ መርሃ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ ።

ሐምሌ 6 /2017 ዓ.ም ኢንተርናሽናል ባይብል ቲዮሎጂ ኮሌጅ በዲግሪ መርሃ ግብር ያሰተማራቸውን 15 ተማሪዎችን በህያው ድምጽ ቤ/ክ የ 14ኛ ዙር የምረቃ ሥነ-ሥርአት አካሄዷል ።

መርሃ ግብሩን የቤተ ክርስቲያኒቱ መጋቢ የሆኑት መጋቢ አሊ ከማል ፀሎት በማድረግ ያስጀመሩ ሲሆን ቃለ እግዚአብሔርንም በቤተ ክርስቲያኒቱ መጋቢ በኩል ዘመኑ አጭር ነው በሚል ርዕስ ያካፈሉ ሲሆን የቤተ ክርስቲያኒቱ ዘማሪያን በአምልኮ አገልግለዋል ።

የምረቃት ስነ-ስርዓቱም የኮሌጁ ዲን በሆኑት በወንድም ገነት ቲርካሶ የተጀመረ ሲሆን ለጉባኤው እና ለተመራቂዎች የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት አስተላልፈው የኮሌጁን ሪፖርት አቅርበዋል ። በንግግራቸውም ላይ ኢንተርናሽናል ባይብል ቲኦሎጂ ኮሌጅ በ2005 ዓ.ም በወንጌላዊ ተረፈ ጫኪሶ ባለራዕይነት እንደተጀመረ ያነሱ ሲሆን እስካሁን ድረስ በተለያዩ ከተሞች ቅርጫፎችን ከፍቶ በርካታ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል ብለዋል ።


በምረቃ ሥነ -ሥራዓቱ ላይ የተማሪዎች ተወካይ የሆኑት ወንድም ጥበቡ ተሾመ ለዚህም ያበቃን ለክብሩም ያበቃን እግዚአብሔር ይመስገን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል እንዲሁም ኮሌጁንና ቤተ ክርስቲያኒቱን አመስግነዋል።

በመቀጠልም ለተመራቂ ተማሪዎች ሰርተፊኬት የመስጠት ሥነ-ሥርዓት የተደረገ ሲሆን ከፍተኛ ውጤት ለስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቷል ።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፤ ቤተልሔም ደረጄ
በክርስቲያን ሴሚናሪ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት መድረሱን ተከትሎ በናይጄሪያ የሚገኙ ጳጳስ መንግስት እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቀረቡ።
በናይጄርያ የሚገኙ ጳጳስ የሚመሩት ሴሚናሪ ላይ በ10 ወራት ውስጥ ሁለት ጊዜ ጥቃት ለመድረሱ የመንግስት ጠንካራ እርምጃ አለመውስድ አስተጽዖ አድርጓል በማለት ተናግረዋል። ታጣቂዎች ለሁለተኛ ጊዜ ባደረሱት ጥቃት የሴሚናሪው ጥበቃ የተገደለ ሲሆን 3 አዳጊ ወጣት የሆኑ ተማሪዎች ደግሞ ታግተው ተወስደዋል።
ጥቃቱም የተፈጸመው በባለፈው ሳምንት በማዕከላዊ ናይጄሪያ እዶ ግዛት ፤ ኢማኩላቴ ኮንሴፕሽን ማይነር ሴሚናሪ ነበር። ጳጳስ ገብሬል ዱኒያ ለቸርች ኢን ኒድ (Church in need) እንደተናገሩት ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች ወደ ሴሚናሪው የመጡ ሲሆን የሴሚናሪው ጥበቃዎችም እነርሱን ለመከላከል አልቻሉም።
በጊዜውም ከሲቪል ጥበቃ ድርጅት ለሴሚናሪው የተመደበው ክርስቶፈር የተሰኘ ጥበቃ መገደሉን ተናግረዋል።
ከዛም ባለፈ እድሚያቸው ከ14 እስከ 17 የሆኑ ሶስት ተማሪዎች መታገታቸውን ጳጳሱ አስታወቀዋል።”የመንግስት አካላት ጥበቃ እንዲያደርጉ ያሳወቅን ቢሆንም ምንም አይነት ጠንከር ያለ እርምጃ እስከ አሁን አላስተዋንም።” ያሉት ጳጳሱ “ችግሩ ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ሁሉም ሰው እንደያግዘን እና እንዲጸልይልን እናሳስባለን።” በማለት ተናግረዋል።
ከአጋቾቹ ጋር በመካከለኛ ሰዎች አማካኝነት ንግግር የተደረገ ቢሆንም ማገቱ እንዳይቀጥል ለታገቱ ሰዎች ክፍያ ከፍሎ ማስለቀቅ ተግባራዊ እንዳይደረግ የሴሚናሪው ፖሊሲ ይከለከላል።

ጳጳሱም እንደዚህ አይነት ጥቃቶች የሴሚናሪውን ቦታ ለመንጠቅ እና ክርስቲያኖችን ከዚያ ቦታ ለማስለቀቅ ያለሙ ሊሆን ይቻላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል።

መረጃውን ከፕሪሚየር ክርስቲያን ኒውስ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፤ አማኑኤል ዴቢሶ
4
ሐምሌ 26 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ “ለኢየሱስ” በሚል ርዕስ ሊዘጋጅ የታሰበውን የአምልኮ ድግስ አስመልክቶ ሐምሌ 11 2017 ዓ.ም በሳሮማሪያ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ።


መጋቢ ትዝታው ሳሙኤል በጸሎት ባስጀመሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የአሮማ ቤተ ክርስቲያን መሪ የሆኑት መጋቢ በጋሻው ደሳለኝ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
በመክፈቻው ንግግራቸው ከዚህ በፊት መጋቢ ትዝታው ሳሙኤል የመዝሙር ግጥሞችን በማበርከት ሲያገለግሉ እንደቆዩ ተናግረዋል።
"መጋቢ ትዝታው ሳሙኤል ከዚህ ቀደም 'ሊነጋ ሲል ይጨልማል' ፣ 'መላክዕክቱ በፊቱ ይቆማሉ'፣ 'ስመሰክር' ፣ 'ማን ቀረ ከሜዳ' እና 'በማንም የማልቀይርህ' በሚሉት መዝሙሮቹ ይታወቃል። በአሁኑም ጊዜ ከ13 ዓመታት በኋላ በኢትዮጵያ ተገኝቶ ለኢየሱስ በሚል የመዝሙር ኮንሰርት አዘጋጅቷል። " ሲሉ ተደምጠዋል።


ዘማሪ ትዝታው ይሄ ጊዜ ለረዥም ጊዜ ሲጠብቁት የቆየ እንደሆነ ተናግረዋል።
በአምልኮ ድግሱ ላይም በሁሉም ስፍራ ያሉ ሰዎች መጥተው እንዲካፈሉ ጥሪ የተደረገ ሲሆን በጌታ ያመኑ ሰዎች የትንሳኤ ልጆች መሆናቸውን አስመልክቶ ነጭ ልብስ ለብሰው እንዲገኙ ጥሪ ተደርጓል።
ከዚህም ባለፈ ሐምሌ 26 2017 ዓ.ም በሚዘጋጀው የመዝሙር ኮንሰርት የጸሎት ፕሮግራሞች የሕይወት ምስክርነት የዝማሬ እና የአምልኮ ጊዜ ፣ የወንጌል አገልግሎት፣ የነፍሳት ጥሪ እንዲሁም ለምድራችን ጸሎት ይደረጋል ሲሉ አገራዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


በስፍራው የተገኘችው ዘማሪ ዘርፌ ከበደ ወንጌል የሕይወታችን ክፍል ስለሆነ ለትውልድ እንዲደርስ በጽድቅ የተሞላ አገልግሎታችን ያስፈልጋል ስትል ገልጻለች።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፤ ቃልኪዳን እንዳለ
7👍1🔥1