የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.51K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ክልሎች አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአሁን ሰዓት በመላው ሀገሪቱ 60 ክልሎች ያሏት ሲሆን እነዚህ ክልሎች በየአመቱ በስራቸው የሚገኙ አጥቢያ መሪዎችና አገልጋዮች የሚሳተፉበት ጉባኤ ያሰናዳሉ። በእነዚህ ጉባኤዎች ከመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዋናው ቢሮ በተወከሉ ኃላፊዎች ትምህርቶች ሲሰጡ የክልሉ አመታዊ ሪፖርት ይደመጣል።

በዚህም መሠረት ባሳለፍነው ሳምንት የሻምቡ፣ ጃርቴ፣ ዶዮገና፣ ሆሳዕና፣ ሺንሺቾ፣ አርሲና ባሌ፣ አድአ ሊበን፣ አድአ በርጋ፣ ቡራዩ ወልመራ፣ የሜታ ሸኖ እና ወሌንሾ ቡታጅራ ክልሎች የክልል ጠቅላላ ጉባኤያቸውን አካሂደዋል።

በጉባኤያቸው በተለይ አዲስ በተሻሻለው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጠ ደንብ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር ተከናውኗል።

መረጃው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
4
ኪንግደም ፓሽን ሴሚናሪ የስነ መለኮት ትምህርት ቤት በነቀምትና መቱ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ሐምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም የኪንግደም ፓሽን ሴሚናሪ በወለጋና በኢሉ አባቦር በማስተርስ ፣ በዲግሪና በዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በነቀምቴ ሁለገብ አደራሽ አስመርቋል። በዚሁ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይም የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የምዕራብ ሪጅን ቦርድ ሰብሳቢ ቄስ ገመቹ አብዲሳ እና የነቀምቴ ከተማ ምክትል ከንቲባ ተመስገን ሚሬሳን ጨምሮ ፣ ተጋባዥ አገልጋዮች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ሴሚናሪው ለ8ኛ ዙር ብቁ ናቸው ብሎ ያሰባቸውን 96 ተማሪዎችን በይፋ ያስመረቀም ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በማስተርስ 27 ተማሪዎችን እንዲሁም በዲግሪ 69 ተማሪዎችን ኮሌጁ አስመርቋል።

የኪንግደም ፓሽን ሴሚናሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ፕሬዘዳንት በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ዶክተር ዘካሪያስ አዱኛ እንደተናገሩትም ሴሚናሪው ከዚህ ቀደም በእንግሊዝኛ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች ብዙ ተማሪዎችን እያሰለጠነ ያፈራ እና እያፈራ እንደሚገኝ በመጥቀስ ብቁ የሆኑ አገልጋዮችን ለቤተክርስቲያንና ለእግዚአብሔር መንግስት እያበረከተ ያለ የስነ መለኮት ተቋም መሆኑንም አንስተው ለወደፊት ካምፓሶቹን በሁሉም ክልሎች እንደሚከፍትም ጠቅሰዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይም የሴሚናሪው ፕርሪንሲፓል ዶክተር ጋዲሳ መንገሻ የእግዚአብሔርን ቃል ያካፈሉ ሲሆን በምርቃቱ ወቅትም የኪንግደም ፓሽን ሴሚናሪ ለቤተክርስቲያን አገልጋዮችን በማፍራት እየተጋ ያለ ተቋም መሆኑንም በማንሳት ከዲፕሎማ እስ ፒ ኤች ዲ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠኑ መሆናቸውንም ጠቅሷል።

በምረቃው መርሐግብሩ ላይ የተገኙት የክቡር እንግዶችም በነበረው መርሐግብሮች ደስተኛ እንደሆኑና ሴሚናሪው እየሰራ ያለ ስራዎችን በማድነቅ አበረታቷል። በዕለቱም የማዕረግ እና የፒኤችዲ ተመራቂ ተማሪዎችም በሴሚናሪው የነበራቸውን ቆይታ አስመልክቶም ደስተኞች እንደነበሩና ለወደፊቱም ከሴሚናሪው ጎን መሆናቸውን ተናግሯል።

በወንጌል ተልዕኮና ዓቃቤ እምነት ትምህርትቤትነት የሚታወቀው ኪንግደም ፓሽን ሴሚናሪ በአሁን ሰዓትም በሀገር ውስጥ ያሉትን 80 ካንፓሶች ጨምሮ ፣በምስራቅ አፍሪካ በ11 ካንፓሶች እና በኦለይን በመካከለኛው ምስራቅም ጭምር ተማሪዎችን እያሰለጠነ እንደሚገኝ ተነግሯል። ሴሚናሪው ከከተማ ወጣ ያሉ ቦታዎችን በመድረስና አብያተክርስትያንን ለታላቁ ተልዕኮና ለእቀበተ እምነት ስራም በማስታጠቅ እየሰራም ይገኛል።

በተጨማሪም ኪንግደም ፓሽን ሰሚናሪ በወንጌል አገልግሎት እድሜያቸውን ለጨረሱትና ለወንጌል ስራ ብዙ መስዋዕትነት በመክፈል ለወንጌል መስፋፋት ምክንያት ለሆኑት ለሶስት አባቶች ለመጋቢ ተፈራ ጎንፋ ከመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን፣ ለመጋቢ ኩመራ ሊካሳ ከሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያንና ፣ለቄስ ታደሰ ከነቀምቴ መካነ ኢየሱስ እውቅና ሰጥቷል።



መረጃውን ኪንግደም ፓሽን ሰሚናሪ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፤ ቤተልሔም ደረጄ
👍1