የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዋናው ቢሮ ኃላፊዎችና አገልጋዮች በቂርቆስ ክፍለከተማ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዋናው ቢሮ ኃላፊዎችና አገልጋዮች በቂርቆስ ክፍለከተማ ፒኮክ መናፈሻ ግቢ ውስጥ በመገኘት ጉርጓዶችን በመቆፈር በቤተክርስቲያኒቱ የተገዙ ችግኞችን ተክለዋል።
በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉት የቤተክርስቲያኒቱ ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ገመቹ ደበሎ "ተፈጥሮን እንድንከባከብ እንድንጠብቅና እንድናበጅ ቃሉ ይናገራል" በማለት የገለጹ ሲሆን የቤተክርስቲያናችን መሪዎችና አገልጋዮችም ምዕመኑን በማስተባበር በዚህ ክረምት ችግኞችን በአካባቢያቸው እንዲተክሉ አበረታተዋል።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 01 የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገለታ መኸዲ በበኩላቸው "መሠረተ ክርስቶስ ሁልጊዜም ከጎናችን ነች" በማለት በሰባተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በመሳተፏ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በስፍራውም ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩት የመምሪያ ኃላፊዎችና የቢሮው ሰራተኞች በፕሮግራሙ ላይ መሳተፋቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።
መረጃው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።
ቤተልሔም ደረጄ ፡ ኢቫንጀሊካል ቲቪ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ልማት ጽ/ቤት በሰላም ግንባታ ላይ ከተለያዩ እምነት ተቋማት ጋር ውይይት አካሄደ።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ ልማት ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ልማት ጽ/ቤት በሰላም ግንባታ ላይ የአንድ ቀን ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ ከወንጌላውያን አብያተ ክርሰትያን መሪዎች፣ከኦርቶዶክስ፥ከሙስሊም እና በካውንስሉ ሰር ከሚገኙ የተለያዩ ወንጌላውያን አብያተ ክርሰትያናት መሪዎች በውይይቱ ተሳትፈዋል። በዕለቱም ከሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ዶ/ር መሐመድ ስለ ሰላም ግንበታ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል ።ተሰታፊዎችም ያለችን ሀገር አንድ ናት በእምነት ሳንለያይ ሁላችንም በመተባበርና በመተጋገዝ ለሀገር ሰላም ግንበታ ትልቅ ስራ ለመስራት ቃል ገብተዋል ።
በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሸነር አቶ እምሩ ሙላቱ ፥የልማት ኮምሽኑ የሰላም ግንባታ ዲፓርተመንት አስተባበሪ አቶ ስለሺ ጋሩማ ፥የአዲስ አባባ ቅርንጫፍ ልማት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ገዛሐኝ ዘውዱና ሌሎች የቅርንጫፍ ልማት ጽ/ቤቱ የስራ ሐላፊዎች ተገኝተዉ ውጤታማ ውይይት እንዲደረግ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ ማድራገቸው ተገልጿል።
በመጨረሻም ተሳታፊዎች በሙሉ ይህንን ሀገራዊ አጀንዳ ያዘጋጀችዉን የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ልማት ኮሚሸንን አመስግነዉ የእለቱ ውይይቱ ተጠናቋል።
መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነው።

❤2
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አከባቢው ክልል በጫንጮ ሙሉ ወንጌል የስነመለኮት ተማሪዎች ምርቃት ተካሄደ።
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል በጫንጮ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያን የማምለኪያ አዳራሽ ተሰርቶ ለምርቃት በቅቷል።
ከዛም ባለፈ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ሴምንየሪ ስር በድፕሎማ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ በጫንጮ ሙሉ ወንጌል ስነ መለኮት የተማሩ 17 ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል።
በዕለቱም በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አከባቢው ክልል ፕሬዚዳንት መጋቢ ሰለሞን በንቲ ፣ መጋቢ ቀና ከሴምንየሪ እና መጋቢ ሽመልስ ጠጂ ከወጣቶች እና ልጆች ክፍል የተገኙ ሲሆን መጋቢ ሰለሞን በንቲ የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።
መጋቢ ሽመልስ ጠጂ ጸሎት በማድረግ ህንፃዉ ለእግዚአብሔር ክብር እንዲውል አሰልፈዋል ሰጥተዋል።
የተማሪዎችን ምርቃት ስርዓት የመሩት ደግሞ መጋቢ ቀና መሆናቸው ከቤተ ክርስቲያኒቱ ማህበራዊ ሚድያ ገጽ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አማኑኤል ዴቢሶ ፤ ኢቫንጀሊካል ቲቪ

❤1
ስመጥሩ አገልጋይ እና መምህር ጆን ማካርተር በ86 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
መሰረታቸውን በካሊፎርኒያ ያደረጉት አገልጋይ እና መጋቢ ጆን ማካርተር ለየት ባሉ ስነመለኮታዊ አቋሞቻቸው እና በኮቭድ 19 ጊዜ የነበረውን የመንግስት እንቅስቃሴ በመቃወማቸው ስማቸው ይነሳል። ግሬስ ቱ ዩ የተሰኘው የትምህርት አገልግሎታቸውም ሰኞ ቀን በኒሞኒያ መያዛቸው ተረጋግጦ ወደ ሆስፒታል ከገቡ ብዙም ሳይቆዩ ሕይወታቸው እንዳለፈ በኤክስ ማህበራዊ ሚድያ ላይ አሳውቋል።
“ልባችን ላይ ቢከብድም ፤ የምንወደው መጋቢያችን እና መምህራችን ጆን ማክ አርተር ወደ አዳኙ መገኘት የመግባቱን ዜና ስናጋራ ደስተኞች ነን። በዛሬው ቀን እምነቱን ማየት ችሏል።” የሚል መልዕክት ነበር በማህበራዊ ሚድያ ላይ በአገልግሎቱ የተጋራው።
አገልጋይ ማክ አርተር ፓትሪሺያ ከተሰኙ ባለቤታቸው ጋር ለ60 አመታት በትዳር የቆዩ ሲሆን 4 ልጆች ፣ 15 የልጅ ልጆች፣ እና 9 የልጅ ልጅ ልጆችን ማየት ችለዋል።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1939 በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ የተወለዱት ጆን ማካርተር በጊዜው ሎስ አንጀለስ ፓሲፊክ ኮሌጅ ከተሰኘው ኮሌጅ የሳይንስ ዲግሪያቸውን የያዙ ሲሆን ከቢዮላ ዩኒቨርሲቲ ታልቦት ቲዮሎጂካል ሲሚናሪ የዲቪኒቲ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።
በፈረንጆቹ 1969 ማለትም በነገረ መለኮት ከተመረቁ ከሶስት አመታት በኋላ በካሊቮርኒያ ሰን ቫሊ ግሬስ ኮሚውኒቲ ቤተ ክርስቲያን መጋቢ በመሆን ለ50 አመታት አገልግለዋል።
እርሳቸው ቤተ ክርስቲያኒቱን በሚመሩበት ጊዜም ቤተ ክርስቲያኒቱ 2 የማለዳ ፕሮግራሞችን ታካሄድ የነገረ ሲሆን በፕሮግራሞቹ ላይም 3000 ሰዎችን መያዝ የሚችለው አዳራሽ በሰዎች ይሞላ እንደነበር በእርሳቸው የሚመራው ዘ ማስተርስ ሴሚናሪ ያወሳል።በጽህፍ ስራቸው እና በስብከታቸው የሚታወቁት ማክ አርተር ከ3,300 ግዜ በላይ መስበካቸው ይገመታል። ከ400 በላይ መጽሐፍቶችን እና የመጽሀፍ ቅዱስ ማጥኛዎችንም ለአንባቢያን አበርክተዋል።
ከዚህም ባለፈ ለረዥም ጊዜያት ለሕዝብ ሲደርሱ የቆዩ የሬድዮ ፕሮግራሞችን እና የቴሌቪዥን አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል። ማካርተር የዘ ማስተርስ ዩኒቨርሲቲ መስራች ሲሆኑ እስከ 2018 ድረስም ተቋሙን በፕሬዚደንት ሲመሩ ቆይተዋል።
በኮሮና ጊዜ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትን ለማቆም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እና የሴቶችን የስብከት አገልግሎት በመቃወማቸው ከተለያዩ አካላት ተቃውሞን ሲያስተናግዱ የቆዩት መጋቢ ማክ አርተር በፈረንጆቹ 2023 ነበር በደረሰባቸው የልብ ሕመም አማካኝነት ወደ ሆስፒታል ያመሩት። ከጥቂት ጊዜያት በኋላም ጤናቸው እንደተመለሰ የተናገሩት ማክ አርተር ከዛን ጊዜ አንስቶ የጤና እክል ሳያጋጥማቸው ያለፈበት ጊዜ አልነበረም። በመድረክ አገልግሎት ብቅ ማለታቸውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እይቀነሰ መጥቶ ነበር።
በዚህ አመት መጀመሪያ ላይም የመጋቢዎች ኮንፍረንስ ላይ ባልስተላለፉት የተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት የመጨረሻው ዙር ላይ ነኝ በማለት በሕይወት ብዙ እንደማይቆዩ ተናግረው ነበር።
ዜና እረፍታቸውን ተከትሎም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በአገልግሎታቸው የሚያውቋቸው የተሰማቸው ሃዘን እያንጸባረቁ ይገኛሉ።
መረጃውን ከክርስቲያን ፖስት አገኘነው።
አማኑኤል ዴቢሶ ፡ ኢቫንጀሊካል ቲቪ

❤8😢6
ፕሮጄክት ዜሮ የተሰኘ የወንጌል ተልእኮ እቅድ በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በይፋ ተከፈተ
ኢትዮጵያን እስከ መጪው 2030 ድረስ በወንጌል ያልተደረሱ ህዝቦችን በሙሉ ለመድረስ እቅዱን ከመላው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያናት በመጡ መሪዎች በተገኙበት በይፋ አስጀምሯል፡፡
በእለቱ በቀረበው መረጃ መሰረት በአለም ላይ 3.43 ቢሊዮን በኢትዮጵያ ደግሞ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በላይ ጨርሶ ወንጌል ያልሰማ ህዝብ እንዳለ ተነግሯል፡፡ በመሆኑም ይህንን ህዝብ ሚሽነሪዎችን በማሰማራት እስከ መጪው 2030 ድረስ ማለትም በአምስት አመታት ጊዜ በወንጌል እንዲደረሱ ለማድረግ ዝርዝር እቅዱን አቅርቧል፡፡
ፕሮጄክት ዜሮ የሚለውን ስያሜ ለምን እንደተጠቀሙ በተሰጠው ማብራሪያ በተጠቀሰው አመት ወንጌል ያልሰማ ሰው ቁጥር 0 እንዲሆን አስበን ተነስተናል በማለት የፕሮጄክቱ ዋና አስተባባሪ ፓስተር ሽመልስ ደጀኔ ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡
በጉባኤው መክፈቻበዝማሬ ወንድም ረታ ጳውሎስ ዝማሬ ያገለገለ ሲሆን፣ በመቀጠል በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በምክትል ጠቅላይ ጸሐፊ ማእረግ የመንፈሳዊ እና የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ፓስተር ይልማ ዋቄ የእግዚአብሔርን ቃል በወንጌል ተልእኮ ላይ አተኩረው አቅርበዋል፡፡
በመቀጠል የሆርን ኦፍ አፍሪካ ሚሽነሪ ተቋም እህት ወለላ እቅዱ ሁለት ምእራፍ እንዳለው አስረድተው በሚቀጥሉት አምስት ወራት ከጉባኤው በሚቋቋም የቴክኒክ ቡድን ጥናት እና የሚሽነሪዎችን ስልጠና እንደሚደረግ ጠቅሰው ጥናቱ የሚያመጣውን ውጤት ተከትሎ በሁለተኛው ምእራፍ ደግሞ ጥናቱ በሚያመላክታቸው ቦታዎች የሚገኙ ቤተ እምነቶችን በመጠቀም የወንጌል ተልእኮውን በተግባር ለማዋል እንደታቀደ ተናግረዋል፡፡
ወንድም በቀለ ቀጥለው እንደተናገሩት በተለይ በዚህ ስራ ላይ ሰፊ አቅሙን እየተጠቀመ ያለውን ሆርን ኦፍ አፍሪካ ሚሽነሪ ተቋምን አድናቆት ሰጥተው በወንጌል ያልተደረሱትን አስቦና አቅዶ መስራት ለቤተክርስቲያን ዋነኛ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ከእቅዱ በኋላ ተሳታፊዎቹ በቡድን በመሆን ጥልቅ ውይይት በማድረግ በየግላቸው የደረሱበትን ድምዳሜ እንደ ግብአት ለእቅዱ አስረክበዋል፡፡
ለኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን
ተስፋዬ ካሳሁን
ከኢንተር ሌግዠሪ አዲስ

❤5