የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.51K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የሚስዮን እና ቲኦሎጂ መምሪያ ከፒ-ኤል-አይ ኢንተርናሽናል(PLI International) ጋር በትብብር የሚሰጠው የመጋቢነት አመራር ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የሚስዩን እና ቲኦሎጂ መምሪያ ከፒ-ኤል-አይ ኢንተርናሽናል(PLI International) ጋር በትብብር የሚሰጠው የመጋቢነት አመራር ሥልጠና የደቡብ ክላስተር፤ ዛሬ በደቡብ ሲኖዶስ አዘጋጅነት በዲላ ከተማ መሰጠት ተጀምሯል።

ሥልጠናውም ላለፉት ሶስት ዓመታት የቤተ ክርስቲያኒቱን መሪዎችና አገልጋዮች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በተለያዩ አርዕስት ሲያሰለጥን የቆየ ሲሆን የማጠቃለያ ዓመት በሆነው የአራተኛው ዓመት ስልጠና "ደቀመዛሙርትን፣ ደቀመዛሙርት አድራጊዎችን እና መሪዎችን ማባዛት" በሚል ዋና ዐርስት ላይ መሠረት በማድረግ በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ክላስተሮች ሥልጠናው በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በዚህም የክላስተር ሥልጠና በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኙ 14 ሲኖዶሶች የመጡ በሲኖዶስ፣ በሰበካ እና በማህበረ ምዕመናን የሚያገለግሉ መሪዎች እና አገልጋዮች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በመካፈል ላይ ይገኛሉ።

የቤተ ክርስቲያኒቱም የሚስዩንና ቲኦሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል፣ የአዲስ አበባ ሲኖዶስ ኘሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ጽጌ በረሃ እና የቤተክርስቲያኒቱ የካምፓስ አገልግሎትና ከተማ ወንጌል ማዳረስ የሥራ ክፍል አስተባባሪ የሆኑት ቄስ ወርቁ ኤባ ሥልጠናውን በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።


መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገኘነው
ቤተልሔም ደረጄ ፡ ኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን