የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዋናው ቢሮ ኃላፊዎችና አገልጋዮች በቂርቆስ ክፍለከተማ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዋናው ቢሮ ኃላፊዎችና አገልጋዮች በቂርቆስ ክፍለከተማ ፒኮክ መናፈሻ ግቢ ውስጥ በመገኘት ጉርጓዶችን በመቆፈር በቤተክርስቲያኒቱ የተገዙ ችግኞችን ተክለዋል።
በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉት የቤተክርስቲያኒቱ ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ገመቹ ደበሎ "ተፈጥሮን እንድንከባከብ እንድንጠብቅና እንድናበጅ ቃሉ ይናገራል" በማለት የገለጹ ሲሆን የቤተክርስቲያናችን መሪዎችና አገልጋዮችም ምዕመኑን በማስተባበር በዚህ ክረምት ችግኞችን በአካባቢያቸው እንዲተክሉ አበረታተዋል።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 01 የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገለታ መኸዲ በበኩላቸው "መሠረተ ክርስቶስ ሁልጊዜም ከጎናችን ነች" በማለት በሰባተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በመሳተፏ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በስፍራውም ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩት የመምሪያ ኃላፊዎችና የቢሮው ሰራተኞች በፕሮግራሙ ላይ መሳተፋቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።
መረጃው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው።
ቤተልሔም ደረጄ ፡ ኢቫንጀሊካል ቲቪ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ልማት ጽ/ቤት በሰላም ግንባታ ላይ ከተለያዩ እምነት ተቋማት ጋር ውይይት አካሄደ።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ ልማት ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ልማት ጽ/ቤት በሰላም ግንባታ ላይ የአንድ ቀን ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ ከወንጌላውያን አብያተ ክርሰትያን መሪዎች፣ከኦርቶዶክስ፥ከሙስሊም እና በካውንስሉ ሰር ከሚገኙ የተለያዩ ወንጌላውያን አብያተ ክርሰትያናት መሪዎች በውይይቱ ተሳትፈዋል። በዕለቱም ከሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ዶ/ር መሐመድ ስለ ሰላም ግንበታ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል ።ተሰታፊዎችም ያለችን ሀገር አንድ ናት በእምነት ሳንለያይ ሁላችንም በመተባበርና በመተጋገዝ ለሀገር ሰላም ግንበታ ትልቅ ስራ ለመስራት ቃል ገብተዋል ።
በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሸነር አቶ እምሩ ሙላቱ ፥የልማት ኮምሽኑ የሰላም ግንባታ ዲፓርተመንት አስተባበሪ አቶ ስለሺ ጋሩማ ፥የአዲስ አባባ ቅርንጫፍ ልማት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ገዛሐኝ ዘውዱና ሌሎች የቅርንጫፍ ልማት ጽ/ቤቱ የስራ ሐላፊዎች ተገኝተዉ ውጤታማ ውይይት እንዲደረግ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ ማድራገቸው ተገልጿል።
በመጨረሻም ተሳታፊዎች በሙሉ ይህንን ሀገራዊ አጀንዳ ያዘጋጀችዉን የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ልማት ኮሚሸንን አመስግነዉ የእለቱ ውይይቱ ተጠናቋል።
መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነው።

❤2
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አከባቢው ክልል በጫንጮ ሙሉ ወንጌል የስነመለኮት ተማሪዎች ምርቃት ተካሄደ።
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አካባቢው ክልል በጫንጮ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያን የማምለኪያ አዳራሽ ተሰርቶ ለምርቃት በቅቷል።
ከዛም ባለፈ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ሴምንየሪ ስር በድፕሎማ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ በጫንጮ ሙሉ ወንጌል ስነ መለኮት የተማሩ 17 ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል።
በዕለቱም በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባና አከባቢው ክልል ፕሬዚዳንት መጋቢ ሰለሞን በንቲ ፣ መጋቢ ቀና ከሴምንየሪ እና መጋቢ ሽመልስ ጠጂ ከወጣቶች እና ልጆች ክፍል የተገኙ ሲሆን መጋቢ ሰለሞን በንቲ የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።
መጋቢ ሽመልስ ጠጂ ጸሎት በማድረግ ህንፃዉ ለእግዚአብሔር ክብር እንዲውል አሰልፈዋል ሰጥተዋል።
የተማሪዎችን ምርቃት ስርዓት የመሩት ደግሞ መጋቢ ቀና መሆናቸው ከቤተ ክርስቲያኒቱ ማህበራዊ ሚድያ ገጽ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አማኑኤል ዴቢሶ ፤ ኢቫንጀሊካል ቲቪ

❤1