የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.54K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
ኪንግደም ፓሽን ስሚናሪ ከ396 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

ሐምሌ 5፣ 2017 ዓ.ም ኪንግደም ፓሽን ስሚናሪ ለ7ተኛ ዙር በዲፕሎማ፣ በዲግሪ፣ በማስተርስ እና ፕ ኤች ዲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሀፍ መጋቢ ታምራት አበጋዝ፣ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ የሴሚናሪው ሴኔት፣ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ፣ ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የተመራቂ ቤተስቦች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።

የኪንግደም ፓሽን ስሚናሪ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዘካሪያስ አዱኛ የእንኳን ደህና መጣችሁና የእንኳን ደስ አለቸው ንግግር አድርገዋል። በንግግራችውም ኪንግደም ፓሽን ስሚናሪ ከተቋቋመ10 አመታትን ያስቆጠረ መሆኑን አንስተው በኢትዮጵያ ከ80 በላይ ካንፓሶሶች እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ወደ 11 የሚጠጉ ካምፓሶች በመክፈት እያስተማረ የሚገኝና እንዲሁም በኦላይን ፕላት ፎርም በተለያዩ መርሀግብሮች እያስተማረ መሆኑን ጠቅሷል።

የሴሚናሪው የቦርድ ፕሬዝዳንት ፓስትር ሰለሞን ባናቲ በበኩላቸው ሴሚናሪው ለቤተክርስቲያን ብቁ የሆኑ አገልጋዮችን እያፈራ እንደሆነ በማንሳት ተመራቂ ተማሪዎች በታማኝነት እና በትጋት እንዲሰሩና ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ምክትል ፕሬዚደንት መጋቢ ሰንበቶ በሼም በበኩላቸው ይህ ታሪካዊ ቀን ነው እግዚአብሔር ስለሰጠን ቀን እናመሰግናለን በማለት፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንደ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ እንደ ሀገር የተማረ ሀይል እንደሚያስፈልግ እና ለዚህም ተመራቂዎቹ ትልቅ ሀይል መሆናቸው ተናግረው ማሳሰቢያንም አክለውበታል።

የእለቱ የክብር እንግደ ሆነው የተሰየሙት የአዲስ አበባ ሐይማኖት ተቋም ጉባኤ ዋና ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ “የእንኳን ደስያላችሁ ንግግር አቅርበዋል። በንግግራቸውም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብዙ መሪዎች፣ ብዙ አገልጋዮች፣ ብዙ አስተማሪዎች፣ ብዙ ሚሽነሪዎች ያስፈልጉናል፤ እናንተ ደግሞ ለዚህ ተሰጥታችሁናልና እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ትጋታችሁ በነገር ሁሉ ይቀጥል ሲሉ በእግዚአብሔር ቃል መክረዋል።

የኪንግደም ፓሽን ስሚናሪ ሴኔትም በትምህርታቸውና በጥናትና ምርምር ሥራ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫ እና ሜዳልያ ሽልማት አበርክቷል።
4
በኢትዮጲያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የልማት ኮሚሽን የማህበረሰብ ልማት ስልጠና ተሰጠ።

ሐምሌ 3/2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የአንድ ቀን የማህበረሰብ ልማት ስልጠና ላይ ከአዳማ ከተማ የእድር ማህበራት ፤ ከተለያዩ እምነቶች የመጡ የእምነት አባቶች፤ ከ7 ቀበሌ የተወጣጡ የማህበረሰብ መሪዎች እና መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል። ስልጠናውን የሰጡትም የቤተ እምነቱ ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ እምሩ ሙላቱ ነበሩ።

በስልጠናው ላይም በተለያዩ የማህበረሰብ ልማት ዘርፎች ማለትም የኢኮኖሚ አቅም መጎልበት፣ ማህበራዊ ደህንነት፣ የማህበረሰብ ልማት አቀራረብ፣ ትራንስፎርሜሽን፣ ለውጥን ጨምሮ ውይይት የተደረገ ሲሆን ምክትል ኮሚሽነሩም በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት እና የልማት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ሁለንተናዊ አገልግሎት ማካሄድ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት በመስጠት አስገንዝበዋል።

የስልጠናው አላማ ተሳታፊዎች ማህበረሰባቸውን ለማገልገል፣ ልማት ለማምጣት እና ትብብር እና ፈጠራን ለማጎልበት ማህበረሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ አስፈላጊውን እውቀትና ክህሎት ማስታጠቅ እና የማህበረሰብ ልማት የግለሰቦችን እና የህብረተሰቡን አጠቃላይ ህይወት ለማሻሻል ያለውን ጠቀሜታ ማስገንዘብ መሆኑን አቶ ኢዮብ ውብሸት ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል ስትል የኢትዮጲያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን በማህበራዊ ትስስር ገጿ ላይ አስፍራለች።
ቤተልሔም ደረጄ ፡ ኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን
3