የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.54K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በአዲስ አበባ መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን መሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።

ክረምትን አስመልክቶ የተዘጋጀው መሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስልጠና በአዲስ አበባ (5ኪሎ) መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ተጀምሯል።

ከሃምሌ 5 እስከ ነሃሴ 25/2017 ዓ.ም ለተከታታይ 8 ሳምንታት የሚቆየው ስልጠና በዋናነት የጋዜጠኝነት መሰረታዊያን ፤ የዜና አጻጻፍ እና ሀሰተኛ የዜና ስርጭቶችን መቀነስ ፤ ስነጽሁፍ እና ዲጂታል ሚዲያን ጨምሮ ዘጋቢ ፊልምን በተግባር ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

በሚኖሩት ሳምንታት እራሳቸውን በስነምግባር ብቁ አድርገው ቤተክርስቲያንን በዲጅታል ሚዲያ በማገዝ እንዲሁም የሚሰሩትን ስራ በተግባር እንዲያሳድጉ ሊያደርግ የሚችል የስልጠና ጊዜ እንደሚኖር በነበረው የመክፈቻ መረሃ ግብር የፕሮግራሙ አስተባባሪ ወንድም ደመላሽ ዶላ ተናግረዋል።

ስልጠናው The Christian News - የክርስቲያን ዜና ከየደስ ደስ መልቲ ሚዲያ እና ቲኪቆስ ሚዲያ ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጁት ስልጠና ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት ከአዲስ አበባ ባሻገር በሃዋሳ እንደሚጀምር ታውቋል።

መረጃውን ከክርስቲያን ዜና አገኘነው
ቤተልሔም ደረጄ ፡ ኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን
1
የመጋቢ ዘማሪ አስፋው መለሰ "አንተን አልጣ እንጂ" 6ኛ የመዝሙር አልበም ተመረቀ።

ዘለግ ላሉ ጊዜያት በዝማሬዎቹ የሚታወቀው መጋቢ አስፋው መለሰ 6ኛውን የመዝሙር አልበም በይፋ አስመርቋል።

በማቴዎስ ወንጌል 6፥31 ላይ መሰረት አድርጎ የተዘጋጀው የአልበሙ የምርቃትና የመዝሙር ድግስ ስነ ስርዓትም በልደታ ጉባኤ እግዚአብሄር ቤተክርስትያን በደማቅ ሁኔታ ተካሄዷል።

"አንተን አልጣ እንጂ" የተሰኘውን ሙሉ አልበም ሰርቶ ለማጠናቀቅ ሁለት አመት እንደፈጀ የተገለጸ ሲሆን አልበሙ 11 መዝሙሮችን በውስጡ መያዙም ተነግሯል።

ዘማሪ አስፋው መለሰ ቀደም ሲልም ብዙ ዘመን ራራህልኝ ፣ በጅምር አይቀርም ፣ ትናንት ዛሬ አይደለም እና መሰል የአልበም ስራዎችንም ለወንጌል አማኙ ተደራሽ አድርጓል።

በፕሮግራም የቤተክርስቲያኗን አገልጋዩች ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የወንጌላውያን አማኞችም መታደማቸውን በማህበራዊ ሚድያ ላይ ይፋ የተደረጉ መረጃዎች አመላክተዋል።
ቤተልሔም ደረጄ ፡ ኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን
5
የዘማሪ አዲሱ ዋዪማ 6ኛ የመዝሙር አልበም ለምርቃት በቃ።

በተለያዩ ጊዜያት በዝማሬዎቹ የሚታወቀው ዘማሪ አዲሱ ዋዪማ በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ 6ኛውን የመዝሙር አልበም በይፋ አስመርቋል።

የዘማሪ አዲሱ ዋዪማ የአፋን ኦሮሞ አልበም “በራ በራኮ” የሚሰኝ ሲሆን አልበሙ 13 መዝሙሮችን በውስጡ መያዙም ተነግሯል።

ዘማሪ አዲሱ ዋዪማ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከ20 አመታት በላይ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በታማኝነት በማገልገሉ የሚታወቅ ሲሆን በፕሮግራሙም የኢት./ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ ፕረዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ጨምሮ የቤተክርስቲያን አገልጋዩች እና ጥሪ የተደረገላቸው የወንጌላውያን አማኞችም ታድመዋል።

ዘማሪ አዲሱ ዋዪማ ቀደም ሲልም “ኢኝ ዳሬ ጎትኒ፣ ኡቱ ባድኔ ካናን ዱራ፣ አታሚን ጋላኒ ና ኢቲሳ”በተሰኙ የመዝሙር አልበሞችን ለወንጌል አማኙ ተደራሽ አድርጓል።

ቤተልሔም ደረጄ ፡ ኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን
7