የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
ታቦር ኢቫንጄሊካል ኮሌጅ በሥነ-መለኮት የትምህርት ያሰለጠናቸውን 47 ተማሪዎች ተመረቁ።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አካል የሆነው ይህ ኮሌጅ በመደበኛ፣ በማታ እና በክረምት መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 21 ተማሪዎችን በሚስዮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም እና በመደበኛና በርቀት መርሃ ግብሮች በሚስዮሎጂ በዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን 26 ተማሪዎችን አስመርቋል። ሲል በማህበራዊ ገጹ ላይ አሳውቋል።
👍1
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ከቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሺፕ ጋር በመተባበር  በነቀምትና በሆሳዕና ከተማ ለመሪዎች ስልጠና ተሰጠ።

ሰኔ 7/2017 ዓ.ም በነቀምት በተደረገው ስልጠና 60 መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ሰኔ 14/2017 ዓ.ም በሆሳዕና ከተማ በተደረገው ስልጠና ላይ 35 መሪዎች ተሳትፈዋል ።

የካውንስሉ የልጆች አገልግሎት  ተወካዮች በሰልጠናው ላይ የተገኙ ሲሆን በቀጣይም በሁለት ወራት ውስጥ 120 ሺህ ልጆችን በወንጌል ለመድረስ  በተለያዩ ከተማ ዘመቻ እንደሚካሄድና ለዚህም ዘመቻ ከ2000 በላይ ልጆችን የማሠልጠን ስራ እንደምሰራ የቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ፌሎሺፕ አስተባባሪ ወንጌላዊት አልማዝ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም በጂማ ከተማ ተመሳሳይ ስልጠና የተሠጠ ሲሆን ትልቅ ወጤት በማስገኘቱ ከእነዚያም ወስጥ 12 መምህራን የስምንት ቀን የቻይልድ ኢቫንጀሊዝም ስልጠና እየወሰዱ እንደሆነ ተገልጿል:።

በሐምሌ ወረ በጂማ ከተማ ከአምሳ በላይ ለሆኑ ሕጻናት ለአምስት ቀን የሚቆይ ስልጠና እንደሚሰጥ እንድሁም  በአላባና በባህርዳር ከተማ ተመሳሳይ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጿል።
10👍9
የዘማሪ አስፋው መለስ ስድስተኛው አልበም በተመለከተ ጋዜጣዊ መገለጫ ተሰጠ።

ሰኔ 24/2017 ዓ.ም የዘማሪ መጋቢ አሰፋው መለሰ ስድስተኛውን "አንተን አልጣ እንጂ" በሚል ርዕሰ የተዘጋጀው ሐምሌ 6 ቀን የሚመረቀውን አልበም በተመለከተ በሳሮማሪያ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል ።


ይህ የመዝሙር አልበም በማቴዎስ ወንጌል 6፥31 ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ ነው። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይም “በ20 ዓመታት የአገልግሎት ጊዜዬ በማግኘትም በማጣትም ጌታን ብቻ አላጣውትም።” ሲል መጋቢ ዘማሪ አስፋው ተነግሯል።

የዘማሪ አስፋው መለሰ ስድስተኛ አልበም 2 አመታትን እንደፈጀ የተገለፀ ሲሆን በውስጡም 11 መዝሙሮችን መያዙ ተነግሯል።

ዘማሪ አስፋው "ብዙ ዘመን ራራህልኝ"፡ "በጅምር አይቀርም የኔ ነገር"፡ "ትላንት ዛሬ አይደለም"፡ "የሩቅ ህልሞቼ" እና "ይሁን" ከዚህ በፊት ለወንጌል አማኞች ያደረሳቸው የዝማሬ አልበሞች ናቸው።

አልበሙም ሐምሌ 6/2017 ዓ.ም በልደታ ጉባኤ አግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የወንጌል አማኞች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እንደሚመረቅ እና ዝማሬዎቹም ሐምሌ 6 በፓስተር አስፋው መለሰ ክራይስት ግሎሪ ዩቲዩብ ገጹ ላይ እንደሚለቀቅ ተገልጿል ።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
10🔥6
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አባል ቤተ እምነቶች ፤ ሚኒስቲሪዎች እና ሕብረቶች በሙሉ የ2017 ዓ.ም ሪፖርት እና የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የስራ እና የሂሳብ ዝርዝር ዕቅድ እንዲሁም ዓመታዊ ክፍያ ሐምሌ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ገቢ እንድታደርጉ ካውንስሉ ያሳስባል።
ሰኔ/2017
12
የጌጃ ቃለ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ለ 43ተኛ ጊዜ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ሰኔ 21/10/2017 ዓ.ም የጌጃ ቃለ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ የረጅም ዓመት ልምድ ያለውና በዘርፉም በርካታ ተማሪዎችን እያሰለጠነ የሚገኝ ተቋም ነው። በተካሄደው የምርቃት መርሀግብር ላይም የተመራቂ ቤተሰቦች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና አገልጋዮች ተገኝተዋል።

የጌጃ ቃለ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ በዲግሪ መርሀግብር የሰለጠኑ 24 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ካለፈው አመት ጀምሮ በተግባራዊ ስነ መለኮት የማስተርስ መርሀግብር የጀመረ መሆኑንና የአሁኖቹ ተመራቂዎች በስነ መለኮት እና ስነ አመራር መሰልጠናቸውም ተገልጿል።

የጌጃ ቃለ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ከተለያዩ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት የመጡ ተማሪዎችን በይፋ ባስመረቀበት ቀን የጌጃ ቃለ ሕይወት ሀ መዘምራን በዝማሬ አገልግለዋል።

የጌጃ ቃለ ሕይወት መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ አካዳሚክ ዲን የሆኑት መጋቢ መስፍን ካሳ በበኩላቸው በማስተርስ የተግባራዊ ስነ መለኮት እንዲሁም በዲግሪ መርሀ ግብር ደግሞ በስነ መለኮት እና በስነ አመራር ተማሪዎችን እያሰለጠነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

መረጃውን ከኮሚሽኑ የሚዲያ ክፍል አገኘነው

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
2🔥1
የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን 6 ኪሎ አጥቢያ ባገኘችው 2000 ካሬ መሬት ላይ ልትገነባ ያሰበችውን ግንባታ አስመልክቶ የምስጋና ፕሮግራም አደረገች።

የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን 6 ኪሎ አጥቢያ በቀጣይ ልትሰራ ያሰበችውን የቤተክርስቲያኒቷን የህንፃ ዲዛይን ይፋ ያደረገች ሲሆን ሁሉም አማኝ በዚህ ትውልድ ተሻጋሪ ስራ ርብርብ እንዲያደርግም ጥሪ ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን 6 ኪሎ አጥቢያ ዋና መጋቢ የሆኑት ሐዋሪያ መርጋ አብዲሳ ቤተክርስቲያኒቱ በመላ ሀገሪቱ ላሉ አጥቢያዎች መሰረት የጣለች እናት ቤተክርስቲያን መሆኗን ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የእግዚአብሔር መገኘት እንዳለና በእግዚአብሔር መገኘት በአጥቢያዋ ክርስቶስን እየተቀበሉ ያሉ ነፍሳት በርካታ እንደሆኑም በተደረገው የአንድነት ፣ የፀሎት እና የምስጋና ጊዜ በመድረኩ ተገልጿል።

በዕለቱም የእግዚያብሔር ቃል ትምህርት የቀረበ ሲሆን በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ማመስገን እንጂ ማጉረምረም ተገቢ አለመሆኑ የትምህርቱ ዋና ጭብጥ ነበር። ማገልገል እና ማመስገን ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጥሪ እንደሆነ እና ክርስቶስም እንዲሁ በነፃ የምንሰጠውን አምልኮ እንደሚፈልግም የጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት የሆኑት መጋቢ አያንሳ ኦፕሲ ባደረጉት ንግግር አንስተዋል። የቤተክርስቲያኒቱ ሕንጻ ተገንብቶ ሲጠናቀቅም 3ሺ የሚጠጉ ሰዎችን የመያዝ አቅም እንዳለው ተነግሯል።

በቤተክርስቲያኒቱ የግንባታ ፕሮጀክት ላይ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪ በቀረበበት ፕሮግራም ላይ በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስቲያኒቱ ለማስፋፊያ ስራ የተረከበችውን 2000 ካሬ መሬት አስመልክቶ መላው ምዕመናንና የቤተክርስቲያኒቱ ወዳጆች በተገኙበት የምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል።
10👍1