የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.61K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ቤዛ_ኢንተርናሽናል_ቸርች_የ2017_ዓ_ም_የአፍሪካ_ተነሺ_ኮንፍረንስ_ተጀመረ

የቤዛ ኢንተርናሽናል ቸርች ከ16 ዓመታት ቆይታ በኋላ አዲስ የአምልኮ አዳራሽ ወይም የአፍሪካ አምልኮ ማዕከል በይፋ ተጀምሮዋል።

የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ቤተ መንግስቱ ይህ የአካባቢ ለውጥ ብቻ አይደለም የእግዚአብሔር ታማኝነት ሙላት እና ለቤተ ክርስቲያናችን አዲስ ወቅት ነው።ወደዚህ አዲስ ጅምር ስንገባ፣ ከየት እንደመጣን እናስታውሳለን ጉዞው በትንሽ የቤት ውስጥ መሰባሰብ የጀመረው እና አሁን ወደዚህ አስደናቂ ጊዜ መርቶናል። በነገር ሁሉ የረዳንን እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ታሪካችን የእምነት፣ የመለወጥ እና የማይካድ የእግዚአብሔር በህይወታችን የመገኘት ማስረጃ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሐፊ ቄስ ደረጀ በመገኘት በዚህ ሁሉ አመታት ውስጥ በነገር ሁሉ የረዳቸውን እግዚአብሔርን በማመስገንና “ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”ሐጌ 2፥9 የለውን የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብ ጸሎት አደርገዋል።

በተገነባው የአምልኮ አደራሽ ውስጥ ከየካቲት 2/2017 ዓ.ም የተጀመረው ተነሺ አፍሪካ እስከ የካቲት 6/2017 ዓ.ም የሚቀጥል እንደሆነና የአብያተክርስቲያናት መሪዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች እና አብረዉ በስራ ሲደክሙ የነበሩ የቤተክርስቲያን አባላት በተገኙበት የአምልኮ አዳራሽ በድምቀት ይመረቃል።
👍5🙏43
#የኢትዮጵያ_ቃለ_ሕይወት_ቤተ_ክርስቲያን_ም_ፕሬዝዳንትና_የልማት_ኮሚሽኑ_ቦርድ_ሰብሳቢ_የሆኑት_ዶ_ር_ስሞዖን_ሔሊሶ_የተመራ_ቡድን_በኦሮሚያ_ክልል_ምስራቅ_ሐረርጌ_ሚደጋቶላ_ወረዳ_የሚሰሩ_የፕሮጀክት_ስራዎችን_ጉብኘት_አደረገ
በጉብኝታቸው በአካባቢው እየሰራ ያለውን የፕሮጀክት አፈጻጸም አድንቀው በአከባቢው በተከሰተ ድርቅ አደጋ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የፍየል፣ የምርጥ ዘር፣ የራስ አገዝ ማደራጀት፣ ጥብቅ ግብርና እና የተሰሩ የውሃ ስራዎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ እንዳለ በጉብኝታቸው ወቅት መመልከት ችለዋል፡፡

ልማት ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ የሚስተዋለውን የውሃ እጥረት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የ350 ሜትር ጥልቀት ያለው የውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጧል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ለአካባቢው ህዝብ ዘላቂ እና ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል ሲሆን ለማስቆፈርም ከ27 ሚሊየን ብር በላይ መመደቡ ተገልጿል፡፡

ዶ/ር ስሞዖን ሔሊሶ “ይህ ከምንሰራቸው በርካታ የሰብዓዊ እርዳታ እና ልማት ስራዎች መካከል አንዱ ነው በዓመት እስከ 2 ቢሊዮን ብር በመበጀት የተለያዮ ስራዎችን በሁሉ የአገርቱ ክፍሎች እየሰራን እንደሆነ ተናግረዋል።

“እንደ ወረዳችን በጣም ከፍተኛ ችግር የሆነውን የውሃ ችግር ለመቅርፍ ልማት ኮሚሽኑ ስራ ስለ ጀመረ ከልብ እናመሰግናለን የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሰበአዊ እርዳታ እና ልማት ኮሚሽን በድርቅ ለተጎዱ ህብረተሰቦች የአስቾኮይ ጊዜ እርዳታን በመስጠት ለ644 አባወራዎች በመድረሱ እና በርካታ ስራዎችን እየሰራ ስለሚገኝ ዘመን የማይሽረውን ታሪክ ሰርታችዏል ያሉት ደግሞ የሚዳጋቶላ ወረዳ ዋና አስተዳደር አብዲ ኢብራሂም ናቸው።
11👍5