የኢት./ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ በልጆችና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ አዘጋጅነት ወጣቶችን ለመሪነት የማሳደግ ስልጠና በጉዲና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና ማዕከል ተካሄደ።
የኢት./ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ በልጆችና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ አዘጋጅነት ወጣቶችን ለመሪነት የማሳደግ ስልጠና በጉዲና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና ማዕከል ተካሂዷል፡፡
በስልጠናውም ከቤተክርስቲያኒቱ ሲኖዶሶች የተወጣጡ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተሮች እና አስተባባሪዎች እንዲሁም ከየሲኖዶሶች የተወከሉ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት በጎፈቃድ አምባሳደሮች ተሳትፈዋል።
የቤተክርስቲያኒቱ ፕረዝዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ በፕሮግራሙ በመገኘት በልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ተቀርጾ እየተሰራበት ያለውን ፓኬጅ ልጆች እና ወጣቶችን በሁለንተናዊ መልኩ ቀርጾ ለማሳደግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት : ለስኬቱ የአገልግሎቱ መሪዎች እና አስተባባሪዎች እንዲሁም የአገልግሎቱ አምባሳደሮች በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ምክር ለግሰዋል።
የቤተ ክርስቲያኒቱ የልጆችና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ በተለያየ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር መምራት የሚችሉ ተተኪ ወጣት መሪዎችን ማፍራት የስልጠና አላማ እንዳሆነ ገልጸዋል።
በፕሮግራሙም እየተሰራበት ባለው ሁለንተናዊ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት ፓኬጅ ዙርያ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ; በተለያዩ ርዕሶች ዙርያም በተለያዩ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ትምህርቶች ተሰጥተዋል።
በመጨረሻም የምክክር ጊዜ ከተካሄደ በኃላ ፡ በስልጠና ለተሳተፉ አምባሳደሮች የምስክር ወረቀት እና የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን በመስጠት ተጠናቋል።
መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የመጋቢ አመራር ሥልጠና በሚዛን አማን ከተማ ተሰጠ።
በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በደቡብ ምዕራብ ቤቴል ሲኖዶስ ለሚገኙ ቁጥራቸው 600 ለሚሆኑ ቄሶችና ወንጌላውያን ለሁለት ተከታታይ ቀናት በመጋቢ አመራር ስልጠና ላይ ተሰጥቷል።
ሥልጠናውም አንድ መሪ "ሚስዩን ተኮር" በመሆን እንዴት ለውጥን መምራት እንደሚችል" በሚያስገነዝብ መልኩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽንሰ ሀሳቦችን ዳሷል።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የሚስዩንና ቲዮሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል እና በቤተ ክርስቲያኒቱ የካምፖስ አገልግሎትና የከተማ የወንጌል ማዳረስ ዋና ክፍል አስተባባሪ የሆኑት ቄስ ወርቁ ኤባ ሥልጠናውን ሰጥተዋል።
መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በደቡብ ምዕራብ ቤቴል ሲኖዶስ ለሚገኙ ቁጥራቸው 600 ለሚሆኑ ቄሶችና ወንጌላውያን ለሁለት ተከታታይ ቀናት በመጋቢ አመራር ስልጠና ላይ ተሰጥቷል።
ሥልጠናውም አንድ መሪ "ሚስዩን ተኮር" በመሆን እንዴት ለውጥን መምራት እንደሚችል" በሚያስገነዝብ መልኩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽንሰ ሀሳቦችን ዳሷል።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የሚስዩንና ቲዮሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል እና በቤተ ክርስቲያኒቱ የካምፖስ አገልግሎትና የከተማ የወንጌል ማዳረስ ዋና ክፍል አስተባባሪ የሆኑት ቄስ ወርቁ ኤባ ሥልጠናውን ሰጥተዋል።
መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
❤1
በቬንዙዌላ የሚገኙ ወንጌል አማኞች ለኢየሱስ እራመዳለሁ በሚል ርዕስ በአውራ ጎዳናዎች ላይ መታየታቸው ተገለጸ።
በቬንዙዌላ ወንጌል አማኞች የተዘጋጀው ሰልፍ በሀገሪቱ ፕሬዚደንታዊ አዋጅ አማካኝነት ብሔራዊ ለኢየሱስ የመራመድ ቀን ላይ ነበር የተካሄደው። ከ23ቱም የሀገሪቱ ግዛቶች አማኞች ወደ ሀገሪቱ ዋና ከተማ በማቅናት ሰልፉን ያደረጉ ሲሆን መሪ ቃላቸውም ‘ኢየሱስ ይህች ሀገር ያንተ ናት።”የሚል ነበር። ሰልፍ የወጡት ክርስቲያኖችም ሰንደቆችን እና ባንዲራዎችን ይዘው የምስጋና መዝሙር ሲዘምሩ ተስተውለዋል።
በካርካስ ሁለት ዋና ሰልፎች በሊበርታዶር ጎዳና በአንድ ላይ በመገናኘት በጋራ የአምልኮ እና የጸሎት ፕሮግራም ተካሂዷል። ተመሳሳይ የሆኑ ፕሮግራሞችም በተለያዩ ከተማዎች እና የገጠር መንደሮች ውስጥ ተካሂደዋል።
መርሃግብሩ በብዙዎች ዘንድ ደስታን የፈጠረ ሲሆን መንፈሳዊ አንድነትን ለማምጣት ለተሰራው ስራ ቤተ ክርስቲያናት፣ ሚኒስትሪዎች እና በጎ ፈቃደኞች ከፍተኛ የሆነ ርብርብ አድርገዋል።
በቪንዝዌላ የወንጌል አማኞች ካውንስል መሪ የሆኑት መጋቢ ጆሴ ፒኔሮ ሰልፉ የተካሄደበት አላማ ኢየሱስን ማዕከል ያደረገ እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን ምንም አይነት የፖለቲካ አቋም እንደሌለበት አበክረው ተናግረዋል።
“ይህንን እያደረግነው ያለው ለአንዱ ለኢየሱስ ነው።” በማለትም ፕሮግራሙ መንፈሳዊ አላማ እና አካታች ተፈጥሮ ወንጌልን ብቻ ያማከለ እንደሆነ ተናግረዋል።
የሀገሪቱ ፕሬዚደንት የተሰራውን ስራ ያደነቁ ሲሆን ይሄም የአንድነት እና የእምነት መገለጫ እንደሆነ ገልጸዋል። ፕሬዚደንቱ ለተደረገው ሰልፍ ትብብር ያደረጉት ፖለቲካዊ ጥቅማቸውን በማሰብ ነው በማለት የሚተቹ ቢሆንም የሰልፉ ተሳታፊዎች ሰልፉ የትልቅ ተሀድሶ እና መነቃቃት ምክንያት እንደሆነላቸው ገልጸዋል።
መረጃውን ከክርስቲያን ዴይሊ ኢንተርናሽናል አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ