በኢንግላንድ የሚገኘው ‘የተመለሱ ጸሎቶች ማሰባሰቢያ የሆነው ኢተርናል ዋል ኦፍ አንሰርድ ፕሬየርስ (Eternal wall of answered prayers) ግንብ ከ100,000 በላይ የተመለሱ ጸሎቶች መመዝገቡ ተገለጸ።
በኢንግላንድ እየተሰራ ያለው እና ገና ተሰርቶ ያላለቀው የኢተርናል ዋል ኦፍ አንሰርድ ፕሬየርስ በዲጂታል መዝገብ ቤቱ ውስጥ ከ100,000 በላይ የተመለሱ ጸሎቶችን ማሰባሰብ መቻሉን አስታውቋል።
በኢንግላንድ ቢርሚንግሃም ውስጥ እየተሰራ የሚገኘው 51.5 ሜትር ርዝመት ያለው ግንብ 1 ሚሊየን ጡቦችን እንደሚጠቀም ይነገርለታል። እናም እያንዳንዱ ጡብ በዲጅታል መንገድ አንድ ለየት ያለ የጸሎት ምስክርነት እንዲይዝ ነው የታቀደው። እናም በጡቡ ውስጥ የተቀመጠውን የጸሎት ምስክርነት ሰዎች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው አማካኝነት ሊያደምጡት ይቻላሉ። ሰዎች በመጸለያቸው እግዚአብሔር የሰጣቸውን ድል በእንደዚህ አይነት መልኩ ለሌሎች ማድረሱ ብዙዎች በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት ከፍ እንደሚያደርገው ይጠበቃል።
በሪቻርድ ጋምብል አማካኝነት የተጀመረው ይህ ምስክርነቶች ማሰባሰቢያ ግንብ በይፋ ከመመረቁ በፊት 250,000 የጸሎት መልሶችን ለመያዝ አቅዷል። አስተባባሪዎችም መሰረቱን በያዝነው ዓመት ከጣሉ በኋላ ክርስቲያኖች ለሌሎች እምነት ይሆን ዘንድ የጸሎት መልሶቻቸውን እንዲያስገቡ ጥሪ በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡
በግንቡ ጡቦች ላይ ከሰፈሩት ምስክረነቶች መካከል አካላዊ ፈውስ፣ የፋይናንስ አቅርቦት ፣ የተፈወሱ ግንኙነቶች እና መንፈሳዊ ተሐድሶ ይጠቀሳሉ። ምናልባት በአጭር ጊዜ ምስክርነታቸውን ማስቀመጥ ያልቻሉ ሰዎች ቀደም ብለው ፎርም በመሙላት ተራ መያዝም ይችላሉ።
መረጃውን ከክርስቲያን ዲይሊ ኢንተርናሻናል አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

❤13👍5
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከዊክሊፍ ኢትዮጵያ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት ተፈራረመ።
ነሐሴ 7/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናትን ታሪክ በመጽሐፍ ሰንዶ ከማስቀመጥ አንጻር የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና ዊክሊፍ ኢትዮጵያ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ማህበር በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ ስምምነት አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ታሪክን መጻፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንደሆነ በማንሳት ታሪክን ጠብቆ በታማኝነትና በጥራት መጻፍ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩም የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት በሀገራችን ኢትዮጵያ ከአንድ መቶ አመታት በላይ እድሜ እንዳላቸው እና በወንጌልና በማህበራዊ አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳበረከቱ በመገለጽ "የሚጻፈው ታሪክ እግዚአብሔር በቤተክርስቲያኑ በኩል የሰራው ስራ ስለሆነ ታሪኩ የእርሱ ነው።” በማለት ተናግረዋል።
የዊክሊፍ የቦርድ ስብሳቢ ፓስተር ግሩም ሞላም “ የታሪክ ጀማሪ እግዚአብሔር ነው። ታሪክንም የሚሰጠው እግዚአብሔር ነው። ስለተሰጠን ታሪክ አግዚአብሔር ይመስገን። ከ30 ሚሊዮን በላይ የሆነው የወንጌል አማኞችን ታሪክ ጽሕፎና ሰንዶ ለማስቀመጥ ካውንስሉ ከእኛ ጋር ለመስራት በማቀዱ ደስ ብሎናል።” ብለዋል።
የካውንስሉ የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ መጋቢ አሸብር ከተማ የሚዘጋጀው መጽሐፍ ለምርምር፣ ለ ዩኒቨርስቲዎች ፣ ለኮሎጆች፣ ለሥነ መለኮት ተቋማት የሚያግዝና የሚጠቅም መሆኑን አንስተው መጽሐፉ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋ እንደሚጻፍ ገልጻዋል።
ዳይሬክተር ተፈራ እንዳለ የኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናትን ከአንድ መቶ አመት ያለፈ ታሪክ በተቀናጀ መልኩ ለትውልድ ፣ ለሀገር ፣ ለቤተክርስቲያን በሚመጥን መልኩ ለመዘጋጀት በዚህ ስራ ላይ ለመሳተፍ እድል በማግኘታቸው የተሠማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ

❤2👍2
11 የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የልማት ድርጅቶች ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የ713 ሚሊዮን ብር የሰብዓዊ እርዳታ ፕሮጀክት ይፈ አደረጉ።
በአማራ በኦሮሚያ እና በትግራይ ክልሎች ለተቸገሩ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ ለመስጠት 11 የሀገር በቀል ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት የልማት ድርጅቶች ከኮምፓሽን ኢንተርናሽሽናል ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የ713 ሚሊየን ብር ሰብዓዊ እርዳታ ፕሮጀክት መጀመራቸውን አሥታወቅዋል። ይህ ፕሮጀክት በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የምግብ እጥረት ላጋጠማቸው ከ200,000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ያቀርባል። ይህ አዲስ ፕሮጀክት ወሳኝ የሆኑ የምግብ ፣ የጤና ፣ የንጽሕና እና የመጠለያ ቁሳቁሶችን በማቅረብ የሕይወት አድን ድጋፍ ይሰጣል።
ፕሮጀክቱ በሶስቱ ክልሎች በሰብዓዊ እርዳታ ፣ በምግብ ስርጭት እና በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ማገገም ላይ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለማጠናከር ያለመ ነው። በዛሬው ዕለት በተካሄደው የፕሮጀክት ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት የመንግስት ተወካሆች ፣ የሲቪል ማህበርሰብ ድርጅቶች ፣ የሃይማኖት ተቋማት እና የሚድያ ባለ ድርሽ አካላት ተገኝተዋል።
የአብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ደሳለኝ በስፍራው በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን “ኮምፓሽን ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም ለብዙዎች ተስፋ መለምለም ምክንያት ሆኗል። የሃይማኖት የዘር እና የጸታ ልየታ ሳያደርግ በመስራት ተኪ የሌለው ተቋም ነው። የተጀመረው ስራ ስኬታማ እንዲሆን ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽዖ ማድረግ ይጠበቅብናል። ይህንን እርዳታ ለረጂዎች ስናስተላልፍ እኛም እናንተ ነን በሚል የፍቅር ስሜት መሆን አለበት።” በማለት ተናግረዋል።
በስፍራ ተገኝተው ስለኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ፤ ስለ እሴቶቹ ፤ ስለሰራቸው ስራዎች እና ዛሬ ይፋ ስለተደረገው ፕሮጀክት ማብራሪያ የሰጡት ደሞ የኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ጸሃይወጣ ታደሰ ናቸው።
በንግግራቸውም “ርህራሄ የእሴቶቻችን መሰረት እና የስራችን ዋና መርህ ነው። እናም ለተጎዱ እና ለተቸገሩ ወገኖች አቅም የፈቀደውን ሁሉ ማድረግ የርህራሄ መገለጫ ነው። በዛሬው ቀን ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት ለዘላቂ መፍትሔ ያላሰለሰ ጥረት መደረግ እንዳለበት የሚያሳስብ ነው።” በማለት ተናግረዋል።
አክለውም የኮምፓሽን ዋነኛ ትኩረት በዘላቂነት ላይ የተመሰረተ የልጆች ሁለንተናዊ እድገት ልማት እንደሆነ ያነሱ ሲሆን “የኮምፓሽን የልማት ስራ የተመሰረተው አጋር ተቋማትን አቅማቸውን በማጎልበት የአከባቢያቸውን ልዩ ፍላጎት እንዲረዱ እና ምላሽ እንዲሰጡ በማገዝ ላይ ነው። በድህነት ውስጥ የተወለዱም ሆነ ያደጉ ልጆች ልብ ውስጥ ድህነት እንዳይወለድ ማድረግ ይቻላል ይገባልም።” በማለት ተናግረዋል።
አጋር አካላት ለፕሮጀክቱ ስኬት ማድረግ የሚችሉትን በሙሉ እንዲያደርጉ ጥሪ ባቀረቡበት ንግግራቸውም የመንግስት አካላት እያደረጉት ያለው የላቀ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ተናግረዋል። ወንድም ታገል ማቴዎስ የ11ዱን የልማት ተቋማት እና የታሰበውን ፕሮጀክት አስመልክቶ አጠር ያለ ሪፖርት አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንን በመወከል የተገኙት አቶ ኢብራሂም ሰኢድ በበኩላችው ዘላቂ መፍትሔ ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበት አንስተዋል። ከገንዘብ ሚኒስቴር በስፍራው የተገኙት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ አስማረ “የእምነት ተቋማት ሀገርን ለመርዳት በዚህ መልኩ ሲሰሩ ማየት በጣም አስደሳች እና ልብ የሚነካ ነው።” በማለት ተናግረዋል።
ይህ ዝግጅት የፕሮጀክቱን ይፋዊ ጅማሬ ከማብሰሩ በተጨማሪ ተባባሪ አካላት በቀጣይ የትብብር ስራዎችን ላይ እንዲወያዩበት አስችሏል፡፡
በሲቪል ማህበርሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ስር በሕጋዊነት የተመዘገቡት 11 የሀገር በቀል ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት የልማት ድርጅቶች ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የተገኘውን የገንዘብ ድጋፍ በመጠቀም ፕሮጀክቱን በጋር የሚተገብሩ ሲሆን ይህም ለተቸገሩ ማህበረሰቦች ወሳኝ እፎይታ እንደሚሰጥ ተገልጿል። እነዚህ የልማት ድርጅቶች ከአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ በተጨማሪ በመላ አገሪቱ ለዓመታት ሁለንታዊ የልማት መርሃ ግብር በማከናወን ላይ ይገኛሉ።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ አማኑኤል ዴቢሶ
ስካይላይት ሆቴል ፡ አዲስ አበባ

👍1