የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ክልሎች ጠቅላላ ጉባኤያት በመካሄድ ላይ መሆናቸው ተገለጸ።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ክልሎች ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን በማካሄድ ላይ የሚገኙ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት ነሃሴ 2 እና 3/2017 ዓ.ም ጉባኤዎቹ በመካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ክልል፤ ሐዋሳ ክልል፤ ዲላና አካባቢው ክልል፤ በንሳ ዳዬ ጊዜያዊ ክልል፤ በሻኪሶ ጊዜያዊ ክልል እና ጅዳ ቆርኬ ጊዜያዊ ክልሎች ተካሂደዋል። በእነዚህ ጠቅላላ ጉባኤዎች በክልሎቹ ስር ከሚገኙ አጥቢያዎች የተወከሉ መሪዎችና አገልጋዮች ተገኝተዋል።

በጠቅላላ ጉባኤው የ2017 ዓ.ም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት እቅድ ሲቀርብ አዳዲስ የመሪዎች ምርጫና ሹመት እንዲሁም በታማኝነት መዋጮአቸውን ለሚከፍሉ አጥቢያዎች የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቷል።

በመጨረሻም በተጠናቀቀው የበጀት አመት እድገት ያሳዩ 18 ስርጭት ጣቢዎች ለጉባኤያቱ ቀርበው ወደ አጥቢያነት አንዲያድጉ መሪዎቹ አጽድቀዋል።

መረጃውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ የፌስቡክ ገጽ ላይ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
1🙏1