የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዋናው ቢሮ አገልጋዮችና ሰራተኞች ቤተክርስቲያኒቱ ከነሃሴ 1-11/2017 ዓ.ም ያወጀችውን ሀገር አቀፍ ጾምና ጸሎት ተከትሎ በዋናው ቢሮ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ ጀምረዋል።

በምድራችን ኢትዮጵያ ሰላም ላይ ትኩረቱን ባደረገው በዚህ ጾምና ጸሎት ጉባኤው በንስሀ እና ምልጃ ልምናውን ለእግዚአብሔር አቅርቧል።

"በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈግሉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።" 2ኛ ዜና 7÷14

መረጃውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ የፌስቡክ ገጽ ላይ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
10
የኢት./ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ በልጆችና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ አዘጋጅነት ወጣቶችን ለመሪነት የማሳደግ ስልጠና በጉዲና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና ማዕከል ተካሄደ።
የኢት./ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ በልጆችና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ አዘጋጅነት ወጣቶችን ለመሪነት የማሳደግ ስልጠና በጉዲና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና ማዕከል ተካሂዷል፡፡

በስልጠናውም ከቤተክርስቲያኒቱ ሲኖዶሶች የተወጣጡ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተሮች እና አስተባባሪዎች እንዲሁም ከየሲኖዶሶች የተወከሉ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት በጎፈቃድ አምባሳደሮች ተሳትፈዋል።

የቤተክርስቲያኒቱ ፕረዝዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ በፕሮግራሙ በመገኘት በልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ተቀርጾ እየተሰራበት ያለውን ፓኬጅ ልጆች እና ወጣቶችን በሁለንተናዊ መልኩ ቀርጾ ለማሳደግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት : ለስኬቱ የአገልግሎቱ መሪዎች እና አስተባባሪዎች እንዲሁም የአገልግሎቱ አምባሳደሮች በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ምክር ለግሰዋል።

የቤተ ክርስቲያኒቱ የልጆችና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ በተለያየ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር መምራት የሚችሉ ተተኪ ወጣት መሪዎችን ማፍራት የስልጠና አላማ እንዳሆነ ገልጸዋል።

በፕሮግራሙም እየተሰራበት ባለው ሁለንተናዊ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት ፓኬጅ ዙርያ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ; በተለያዩ ርዕሶች ዙርያም በተለያዩ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ትምህርቶች ተሰጥተዋል።

በመጨረሻም የምክክር ጊዜ ከተካሄደ በኃላ ፡ በስልጠና ለተሳተፉ አምባሳደሮች የምስክር ወረቀት እና የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን በመስጠት ተጠናቋል።

መረጃውን ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ