የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ዋና ፅ/ቤት ፣ የልማት ኮሚሽኑ ዋና መ/ቤት እና የሴሚናሪው ሰራተኞች በጋራ በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት ልዩ የአንድነትና የጸሎት መንፈሳዊ ፕሮግራም አካሄዱ።
ሐምሌ 28 እና 29 /2017 ዓ.ም በአዳማ በተካሄው የአንድነትና የጸሎት ፕሮግራም ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕረዚዳንት መጋቢ ላኮ በዳሶ ፣ም/ፕረዚዳንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው ፣የልማት ኮሚን ኮሚሽነር መጋቢ ብርሃኑ ታረቀኝ ፣የሴሚናሪው ፕረዚዳንት መምህር ሂሩህ አድማሱ እና ሁሉም ሰራተኞች ተገኝተዋል ።
ፕሮግራሙም ጾም ጸሎት፣ አምልኮ፣ የተሃድሶ እና የመነቃቃት ትምርህት እና የአንድነት ፕሮግራምን ያካተተ ነበር።
ለጉባኤው መንፈሳዊ ሰላምታ በማቅረብ ፕሮግራሙን በጸሎት ያስጀመሩት መጋቢ ብርሃን ታረቀኝ ሲሆኑ መጋቢ ላኮ በዳሶ " እምነት ተስፋ ፍቅርን እንያዝ" በሚል ርዕስ የእግዚአብሔርን ቃል መልዕክት ለጉባኤው አካፍለዋል። መጋቢ ለወየሁ ስንሻውም እግዚአብሔር ምድራችንን ኢትዮጵያ እንዲጎበኛት እና እንዲባርካት ጸሎት አድርገዋል።
የአንድነት እና የጸሎት ፕሮግራሙን የተዘጋጀበትን አላማ ሲያሳውቁ የልማት ኮሚሽኑ ኮሚሽነር የሆኑትን መጋቢ ብርሃኑ ታረቀኝ "ዋነኛ ያሰባሰበን የእግዚአብሔር መንግስት ጉዳይ እና በአንድነት ህበረታችንን እንዲጠናከር ነው።” በማለት ተናግረዋል።
አክለውም “በፊቱ ጸልየናል ፣ተመካክረናል ፣ እንዲሁም አመቱን በሙሉ የረዳንን ጌታን አመስግነናል። ራሳችንምም በማየት ለቀጣይ አዲስ አመት በታደሰ ሀይል አገልግሎታችን እንዲሰምር መንፈስ ቅዱስ ምሪትና ሀይል ሰጥቶናል። ከጠበቅነው በላይ ጌታ ረድቶናል።” ብለዋል።
በፕሮግራሙ የተሳተፉ ወገኖች ጌታ መልካም የአንድነት ጊዜ እንደሰጣቸው ገልጾዋል።
መረጃውን ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ