በአርጀንቲና የሚገኙ የወንጌል አማኞች ከመንግስት ሙሉ እውቅና ማግኘታቸው ተገለጸ።
በአርጀንቲና የሚገኙ የወንጌል አማኞች ከመንግስት እንደ ሀይማኖት ተቋም የመቆጠር ሕጋዊ ሰውነት አግኝተዋል።
በዚህ ታሪካዊ እርምጃ የአርጀንቲና ብሔራዊ የሕግ አስፈጻሚ ዘርፍ የወንጌል አማኞችን ቤተ ክርስቲያን እንደ ሕጋዊ የሃይማኖት ተቋማት የመዘገበ ሲሆን በመላው ሀገሪቱ ላይም ሙሉ የሆነ ሕጋዊ መብት እንዲኖረው ፈቃድ ሰጥቷል።
በፕሬዚደንት ጃቪር ሚሌ ፊርማ የጸደቀው አዋጅ በሀገሪቱ የሀይማኖት ምዝገባ የተመዘገቡ ቤተ ክርስቲያኖች እንደ ሲቪል ማህበራት ሳይቆጠሩ በነጻነት እምነታቸውን ማራመድ እንደሚችሉ ይናገራል።
ወንጌል አማኝ ቤተ ክርስቲያኖችም ይህንን ሕጋዊ ሰውነት ማግኘታቸው በራሳቸው ስም የባንክ አካውንት እንዲከፍቱ ከማስቻል ጀምሮ የአስተዳደር ስራዎቻቸውን ለመፈጸም የሚሄዱበትን ርቀት ያሳጥርላቸዋል። የአርጀንቲና ሪፐብሊክ የወንጌል አማኞች ህብረት (The Christian Allicance of Evangelical Churches of the Republic of Argentina) የተወሰነውን ውሳኔ አስመልክቶ የተሰማውን ደስታ የገለጸ ሲሆን ፤ ውሳኔው የሃይማኖት ነጻነት እና በሕግ ፊት እኩል መሆን የተከበረበት እና ከ30 አመታት በላይ የቆየ የጸሎት፣ ጽናት እና ጥረት ውጤት ሲል አስታውቋል።
የአርጀንቲና የወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን በመንግስት ዘንድ እውቅና ማግኘቷ በሀገሪቱ ላይ ወንጌል አማኞች ያላቸውን ተሳትፎ እንደሚጨምረው የሚጠበቅ ሲሆን ፤ ወንጌል አማኞች በነጻነት በአገልግሎት፣ በወንጌል ስርጭት እና በማህበራዊ አገልግሎት እንዲበረቱ በማድረግ በአርጀንቲና መንፈሳዊ ምህዳር ላይም ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል።
የሀገሪቱ አውራጃዎች አዋጁን ተከትሎ አሰራራቸውን ማሻሻል ይጠበቅባቸዋል። የአርጀንቲና ወንጌል አማኞችም የተወሰነው ውሳኔ ሕጋዊ ግልጽነትን ከማምጣት ባለፈ ወንጌል አማኞች በሀገሪቱ ላይ ወደፊት ላይ ያላቸውን ድርሻ የሚያመላክት ነው በማለት ደስታቸውን እያጋሩ ይገኛሉ።
መረጃውን ከወርልድ ኢቫንጀሊካል አሊያንስ ድረገጽ አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

❤4
ሚሽን ኦፍ ሆፕ ኢንተርናሽናል ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስቸለውን ስምምነት ተፈራረመ።
መሰረቱን በናይሮቢ ኬንያ ያደረገው ሚሽን ኦፍ ሆፕ ኢንተርናሽናል በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሁለንተናዊ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቅ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም ከአጸደ ሕጻናት ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ተማሪዎችን ለማስተማር እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል።
እናም በዚህ ረገድ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በካውንስሉ ጽህፈት ቤት ተፈራርሟል።
ስምምነቱ ላይም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስልን በመወከል የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሓፊ የሆኑት ቄስ ደረጄ ጀምበሩ ፊርማቸውን ያኖሩ ሲሆን ሚሽን ኦፍ ሆፕ ኢንተርናሽናልን በመወከል ደግሞ የአገልግሎቱ መስራች አባል እና ስራ አስኪያጅ ሜሪ ዋቹካ ካማሁ ፊርማቸውን አኑረዋል።
በቆሬ አከባቢ ትምህርት ቤቶችን ለመጀመር ያቀደው አገልግሎቱ የሚገነባቸው ትምህርት ቤቶች ጥራት ካለው የትምህርት አሰጣጥ ባለፈ የምገባ እና የሕክምና ክትትል አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።
ሚሽን ኦፍ ሆፕ ኢንተርናሽናል ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በጋራ ለመስራት ያቀዳቸው ስራዎች በተለያዩ የሀገራችን ክፍል ያሉ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

❤8👍5
የጽዮን ከተማ ሰራዊት ቤተ ክርስቲያን ለ30 ቀናት ለማካሄድ ያቀደቸው የማህበራዊ ሚዳያ የቀጥታ ስርጭት የወንጌል ስርጭት ፕሮግራም መክፈቻ ፕሮራግራም በቤተ ክርስቲያኒቱ አዳራሽ ነሐሴ 1 ቀን በይፋ ተጀመሯል፡፡
ፌስቡክ፣ ቲክቶክ፣ ዩቱዩብ፣ ኢንስታግራም ፣ ዋትሳፕ እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም የሚደረገው ይሄ የወንጌል ስርጭት ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ለመድረስ ያቀደ ሲሆን ብዙዎችንም በወንጌል እንደሚደርስ ይጠበቃል።

❤6👍1