የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.4K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አማኑኤል ብርሃንና ህይወት ቤ/ክ ከተለያዩ አጥቢያዎች ለተወጣጡ አገልጋዮች ስልጠና ሰጠች።

ከተመሰረተች 26 ዓመታትን ያስቆጠረችው ቤተክርስቲያንኗ ባለፉት 10 ቀናትም በአራቱ ቀጠናዎቿ ማለትም በዶኒ ፣በአለምጤና ፣ በአርቤጎና እና በሻሸመኔ ቀጠና ዙሪያ ላሉ የአጥቢያ አገልጋዮች ስልጠናውን ስትሰጥ ቆይታለች።

በአሁኑ ሰዓትም የኢትዮጵያ አማኑኤል ብርሃንና ህይወት ቤ/ክ በአራቱም አቅጣጫ ሰባት ቀጠናዎችና 48 አጥቢያዎች እንዳሉዋት ተገልጿል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይም ሐምሌ 25 እና 26 በሻሸመኔ አጥቢያ የወንጌል ስርጭት ጊዜ የተደረገ ሲሆን በተናጠል በተደረገ የወንጌል ስርጭትም 408 ሰዎች ወንጌልን የሰሙ ሲሆን ከነዚህም መካከል 12ቱ ጌታን ሲቀበሉ 14ቱ ደግሞ በንሰሀ መመለሳቸው ተነግሯል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም በጀማ ስብከት 2500 የሚጠጉ የከተማው ነዋሪዎች ወንጌልን ሲሰሙ 17 አዳዲስ ሰዎች ደግሞ የውሀ ጥምቀት መውሰዳቸውንም ከቤተክርስቲያኗ የደረሰን መረጃ ያሳያል ።

መረጃውን ከማህበራዊ ትስስር አገኘነው

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2
እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ እንጸልይ" ዶ/ር ብርሃኑ ታምሬ ከደቡብ አፍሪካ ።

የደቡብ አፍሪካ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል አስቸኳይ የጾም እና ጸሎት ጥሪ አቅርቧል።

የወንጌል አብሳሪዎች አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን በጁሃንስበርግ መሪ እና የካውንስሉ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ታምሬ እንደገለጹት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች በተለያዩ ቡድኖች ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልጸው ነገሮች እንዲስተካከሉ እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ እንጸልይ ብለዋል።

ዶ/ር ብርሃኑ በመልዕክታቸው በአሁኑ ሰዓት ዱዱላ የተባለ ቡድን ስደተኞችን የማይገቡ ዶክመንቶችን በመጠየቅ እያሰቸገረ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም እዛው የተወለዱ እና ያደጉ ልጆች ሲማሩም ይሁን ትምህርት ተምረውም ከጨረሱ በኋላ ስራ ለማግኘት በመቸገር ከፍተኛ ስንለቦናዊ ጫና እያደረባቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

እግዚአብሔርን አምነን ፊታችንን ወደ እርሱ በማድረግ ያለውን ችግር በእርሱ ፊት እንቅረብ በማለት በፈረንጆቹ ኦገስት 5-7 / 2025 ወይም ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 01/2017 ዓ.ም ድረስ በጾም እና ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ጸሎት እንዲቀርብ ጥሪ አቅርበዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
🔥2
በቬንዝዌላ በተከሰተው ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ውድቀት እና ሰብዓዊ ቀውስ መሃል የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ከፍተኛ የሆነ እገዛ እያደረጉ እንደሆነ ተነገረ።

ቪንዝዌላ በኢኮኖሚ ውድቀት እና በሰብዓዊ ቀውስ እየተናጠች ባለችበት በዚህ ጊዜ የወንጌል አማኝ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ከተቸገሩ ወገኖቻቸው ጎን እንደቆሙ እየተነገረላቸው ይገኛል። የመንግስት ተቋማት ሀገሪቱ እያለፈችበት ላለው የዋጋ ግሽበት መፍትሔ ለመስጠት ባልቻሉበት በዚህ ጊዜ መጋቢዎች ከመስበክ ባለፈ ሀገራቸውን ለመደገፍ በብዙ መስኮች እላይ ታች እያሉ ይገኛሉ።

መጋቢዎች ለችግር ለተጋለጡ ሰዎች ምግብ ከማቅረብ ባለፈ የማማከር እና ተስፋ የመስጠት ስራቸውን በመቀጠል ላይ ናቸው። ብዙ ቤተ ክርስቲያኖች በአሁኑ ሰዓት እንደ እርዳታ ማዕከሎች እያገለግሉም ይገኛሉ።

የተሰጡ አቅርቦቶችን ማከፋፈል እና የእርዳታ ህብረቶችን ማጠናከር ደግሞ ዋነኛ ስራቸው ነው። ምንም እንኳን ያለው አቅርቦት በሕዝቡ ዘንድ ካለው ፍላጎት አንጻር ጥቂት ቢሆንም ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚያመሩ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው። ይህም የሆነው ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ማንም ሰው የጽናት እና በእግዚአብሔር አቅርቦት ላይ የመደገፍን ተስፋ ስለሚካፈል ነው ሲል ኤፒ ኒውስ አስነብቧል።

ይህም ክስተት ወንጌል አማኞች በርህራሄ እና በእውነት መስራታቸው ሀገር በከፍተኛ ደረጃ በምጥ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ ለብዙዎች መጽናት እና መጽናናት ምክንያት እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ።

መረጃውን ከኤፒ ኒውስ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
5🔥3👍1
የቢሾፍቱ ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ አቀረበ።

ከሰሞኑ በቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ዝናብ በተለያዩ የከተማዋ ስፍራዎች ቤት ውስጥ ጎርፍ በመግባት የንብረቶች መበላሽት እና ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።

ሁኔታውን አስመልክቶ የቢሾፍቱ ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ አቅርቧል።

ጥሪዉን ያቀረቡት የሕብረቱ ዋና ሰብሳቢ መጋቢ ብሩክ ከበደ “በከተማዋ በጣለው ንፈስ እና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች ላይ እና በህብረታችን በታቀፋ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ላይ በደረሰው የንብረት ውድመት የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን እገልፃለሁ።” ብለዋል።

መጋቢ ብሩክ አክለዉ ቅዱሳን የወንድምና የእህቶችን መኖርያ ቤቶች እንዲሁም የአጥቢያ ቤተክርስቲያናትን መሰብሰቢያ አዳራሾች መልሶ ለመስራት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ሁሉ በማድረግ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ እርስ በእርስ በመተጋገዝ አብረን እንቁም የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው አራተኛው አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በድምቀት ተጠናቀቀ፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሐረሪ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ለሁለት ቀናት በሐረሪ ክልል፣ ሐረር ከተማ ላይ ሲያካሂደው የነበረው አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በድምቀት ተጠናቋል፡፡

በሰላም ኮንፍረንሱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ባስተላለፉት የሰላም መልዕክት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን ለመፍታት የሚረዱ በርካታ የውይይት መድረኮች በማዘጋጀት፣ ችግሮች የሚፈቱበትን የጋራ የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ አለመግባባቶች እንዲፈቱ እያደረገ ያለው ጥረት ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ጸኃፊው አክለውም የእርስ በእርስ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ በተለይም መከባበርን፣ ሰላምን፣ አብሮነትን እና ይቅርታን የሚያጎለብቱ በረካታ ተግባራት መከናወናቸውን በመግለጽ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይቻል ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሰላምን ከመገንባት አንፃር ኃላፊነታቸውን ከምን ጊዜውም በላይ እንዲወጡ አደራ ብለዋል፡፡

በተያያዘም የሀገራችን ሰላም እንዲጸና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች በግጭት ውስጥ ለሚገኙ አካላት በሰላም በመነጋገር ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ የሰላም ጥሪ በአክብሮት ያቀርባል በማለት በድጋሚ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሰላም ኮንፍረንስ መድረክ ላይ በክብር እንግዳነት የተገኙት የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ክብርት ወ/ሮ ሮዛ ኡመር እንደተናገሩት ሀረር ከአንድ ሺህ ዓመት በፊት ጀምሮ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የተለያዩ የሃይማኖቶች ተቋማት እና ተከታዬቻቸው ተቻችለው እና ተከባብረው በፍቅር የሚኖርባት የሰላም፣ የመቻቻል እና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነች ድንቅ ከተማ መሆኗን አስታውሰዋል።

ክብርት ም/ርዕሰ መስተዳድርዋ አክለውም የሃይማኖት ተቋማት ለሰላም ግንባታ እያበረከቱት ያለው አስተዋፅኦ እጅግ የላቀ መሆኑን በመጠቆም የሃይማኖት ተቋማት በሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላምን ይበልጥ ለማስረፅ እና ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።


የኢፌድሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ክቡር ዶክተር ካይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በበኩላቸው የሃይማኖት ተቋማት በሀገር ደረጃ ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት የሚያደርጉት ጥረት እና አስተዋጽዎ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም ይህን የጀመሩትን ታላቅ የሰላም ግንባታ ሥራ በመቀናጀት አጠናክረው እንዲቀጥሉ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል የሃይማኖት ተቋማቱን በማስተባበር እና በማቀናጀት ሰላምን ለማጽናት የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው በቀጣይም የሃይማኖት ተቋማቱን ትብብር ይበልጥ በማጎልበት የጀመራቸውን የሰላም ግንባታ ሥራዎች እንዲያስቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሐረሪ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው አራተኛው አገር አቀፍ ሕዝባዊ የሰላም ኮንፍረንስ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አምስተኛውን አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ እንዲያዘጋጅ መመረጡ በይፋ የተበሰረ ሲሆን የሐረሪ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤም ለአምስተኛው አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረስ አዘጋጀ ሆኖ ለተመረጠው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሰላም ዋንጫውን በክብር አስረክቧል፡፡

መረጃውን ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ