የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.36K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሰላም ኮንፍረንስ በሐረር ኢማም አህመድ ስታዲየም ተካሄደ።

ሐምሌ 29/2017 አራተኛው ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሰላም ኮንፍረንስ በሁለተኛ ቀን ውሎው በሐረር ኢማም አህመድ ስታዲየም ተካሂዷል።

በኮንፍረንሱ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና ተወካዮች፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር፣ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሓፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ታድመዋል።

እንዲሁም የየክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሃይማኖት ተቋማትና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ኮንፍረንሱ ህዝቡ ሰላሙን እንዲጠብቅና የሰላም ባለቤት ሆኖ እንዲሰራ፣ ሰላም በሀገሪቱ በዘላቂነት ፀንቶ እንዲቀጥል የሃይማኖት አባቶችና ምዕምናን ይበልጥ እንዲሰሩ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
እንዲሁም ኢትዮጵያ በሰላም በአንድነትና በአብሮነት ፀንታ እንድትቆም ህብረተሰቡን ለማነቃቃት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

በኮንፍረንሱ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂዎች የሰላም መልዕክትና ጥሪ አስተላልፈዋል።

የሰላም ኮንፍረንሱን የኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ተቋማት ጉባኤ ከሐረሪ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑ ተመልክቷል።

የሰላም ኮንፍረንሱ "ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነትና ለአብሮነት'' በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ሲሆን በሁለተኛ ቀን ውሎው በሐረር ከተማ ኢማም አህመድ ስታዲየም ተካሂዷል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2
በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የማዕከላዊ ክላስተር የ4ተኛው ዓመት የመጋቢነት አመራር ሥልጠና(4th Year Pastoral Leadership Training) በአዲስ አበባ ከተማ ማካሄድ መጀመሩ ተገለጸ።

የማዕከላዊ ክላስተር የ4ተኛው ዓመት የመጋቢነት አመራር ሥልጠና(4th Year Pastoral Leadership Training) በአዲስ አበባ ከተማ በመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪዮም በዶ/ር አማኑኤል ገ/ሥላሴ የስብሰባ አዳራሽ መሰጠት ተጀምሯል።

የመጋቢያንን የአመራር ክህሎትን ለማሳደግ በአራት ዓመታት ተከፋፍሎ በተቀረፀ ልዩ ሥርዓተ ትምህርት በመሰጠት ላይ የሚገኘው ይህ ሥልጠና በዚህኛው ዙር ማጠቃለያውን የሚያደርግ መሆኑ ተገልጾዋል። የዘንድሮው ስልጠና "ደቀመዛሙርትን እና ደቀ መዝሙር አድራጊዎችን ማብዛት!" በሚል መሪ ሐሳብ እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው ከአዲስ አበባ ሲኖዶስና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ የተወጣጡ የሲኖዶስና የሰበካ መሪዎች፤ የማኀበራነ ምዕመናን ቄሶች፣ ወንጌላውያን እና ሽማግሌዎች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በጋራ እየተካፈሉ እንደሚገኙ ተገልጿል ።

ባለፉት ወራት በቦረናና በዲላ ከተሞች በርካታ ሲኖዶሶችን ያሳተፈ ሥልጠና በተመሳሳይ ይዘት መሰጠታቸው የሚታወስ መሆኑ ተገልጾዋል ። የማዕከላዊ ክላስተርን ጨምሮ በቀጣይ በሌሎች ክላስተር የሚሰጠውን የ4ተኛ ዓመት የመጋቢነት አመራር ሥልጠና የቤተ ክርስቲያኒቱ የሚስዮንና ቲኦሎጂ መምሪያ ከፒ ኤል አይ ኢንተርናሽናል(PLI International) ጋር በትብብር ያዘጋጃቸው መሆኑን ከመምሪው ለመረዳት ተችሏል።


መረጃውን የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
🔥1