ባርሄ ሚኒስትሪ ከሀርቫስት ኢንተርኮንቲነንታል ሚኒስትሪ ጋር በጋራ በመሆን ለሁለት ቀን የሚቆይ የወንጌል ስርጭት አዘጋጁ ።
በወንጌል ስርጭቱ መጀመሪያ ባለራዕይ ገረመው ጎሳዬ የመክፈቻ ንግግራቸውን ያደረጉ ሲሆን ከፕሮፌሰር ሚኒስትር ፓትሪሺያ አይካ ጋር ከዚህ ቀደም በተለያዩ የወንጌል ስራዎች ላይ በጋራ መሳተፋቸውን ተናግረዋል።
ሚኒስትር ፓቲሪሺያ አይካ በበኩላቸው በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በአካል ተገኝተው ይህንን የወንጌል ተልዕኮ ለሌሎች ለማድረስ በጋራ ለመስራት እንደመጡ እና ለሁለት ቀናት በዘነበ ወርቅ በአየር ጤና እና በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ የንግድ ማዕከል በሆነው በመርካቶ ላይ ወንጌል ለመስራት መገኘታቸውን ገልጸዋል።
እንዲሁም ሚኒስትር ፓትሪሺያ "እግዚአብሔር ከዚህ ቀደም ከባርሄ ሚኒስትሪ ጋር በጋራ ስሰራ የነበረው የወንጌል አገልግሎትን ይበልጥ መጥቼ እንድሰራ ስላደረገኝ እና በኢትዮጵያ ተገኝቼ ለሁለት ቀናት የወንጌል ስርጭት ለማድረግ እንዲሁም ስልጠና ለመስጠት ስለቻልኩ አመሰግነዋለሁ።” በማለት ተናግረዋል።
ሚኒስትር ፓትሪሺያ አይካ ከ2009 እስከ 2012 እ.አ.አ በኢትዮጵያ ተገኝተው ለፋርማሲ ተማሪዎች ወንጌልን መስራታቸው እንዲሁም ከ12 አመታት በላይ ከሚኒስትር ካሌብ ጋር ብርቱ የሆነ የወንጌል አገልግሎት ሲሰሩ መቆየታቸውን በዚህም ደቀመዝሙርን ማፍራታቸውን በስብሰባው ገልጸዋል።
ሚኒስትር ፓትሪሺያ አይካ ከ450 በላይ ቤተክርስቲያናትን በተለያዩ ሀገራት ስለመመስረታቸው እንዲሁም ትልቅ ራዕይም እንዳላቸው ተናግረዋል። ቤተ ክርስቲያኒቷ ተልዕኮዋ የጠፉትን ነፍሳት ለማዳን ዋጋ ከፍሎ ደቀመዝሙር ማድረግ ላይ መሰረት አድርጋ እንደምትሰራ ገልጸዋል።
እንዲሁም “አማኞች የእግዚአብሔርን ሃይል እና መንፈስ ተቀብለናል እና ለሌሎች ነፍሳት ይህንን የተካፈልነውን ወንጌል በማድረስ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ልንጠራ ይገባል።” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በንግግራቸውም መጽሐፍ ቅዱስን ከዘፍጥረት እስከ ዩሐንስ ራዕይ ማወቅ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ እና ለሌሎች ይህንን ወንጌል ማድረስ እንዳለብን አስታውቀዋል።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቃልኪዳን እንዳለ

❤1
በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የቤተ ክርስቲያ አንድነት ሥነ-መለኮት (The Theology of Church Unity) በሚል ርዕስ ሥልጠና በአዶላ ከተማ ተሰጠ።
በአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ ከበርካታ ሰበካዎችና ማኀበረ ምዕማናንን ለተወጣጡ ቁጥራቸው ከ1,300 በላይ ለሚሆኑ ወንጌላዊያን፣ ቄሶችና የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ሥልጠናው ተሰጥቷል። ሥልጠናውን የቤተ ክርስቲያኒቱ የወንጌልና ቲዮሎጂ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል ሰጥተውታል።
የቤተ ክርስቲያኒቱም ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ሥልጠናው ላይ ተገኝተው ለአገልጋዮቹ ጠቃሚ መልክዕቶችን አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙና የቤተ ክርስቲያኒቱ የወንጌልና ቲዮሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል በአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ እየተገነባ የሚገኘውን የአንደኛ ጀረጃ ትምህርት ቤት የህንፃ ግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል።
የህንፃ ግንባታ ሂደቱም ከዚህ በፊት ከመጡበት ወቅት አንፃር ከፍተኛ ልዩነት እንዳለውና በፍጥነት በመገንባት ላይ መሆኑ እንዳስደሰታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ገልጸዋል። አሁን እየተካሄደ ባለበት መልኩ ጥራቱን ጠብቆ መገንባቱ እንዲቀጥል አበረታተዋል።
የሲኖዶሱም ፕሬዚዳንት ቄስ ጌሎ ጎሎልቻ የትምህርት ቤቱ ሙሉ ወጪ ከምዕመናን በሚሰበሰብ አስተዋጽኦ እየተገነባ መሆኑን ገልፀው ቤተ ክርስቲያን በራሷ አቅም ፕሮጀክቶችን ሰርታ ማጠናቀቅ እንደምትችል ማሳያ እንደሚሆን ገልጸዋል።
የትምህርት ቤቱ መደበኛ የትምህርት መስጫ ብሎኮች ሲጠናቀቁ ደረጃውን የጠበቀ ከ1ኛ-8ኛ ክፍል የሚያስተምር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የሲኖዶሱ ፕሬዚዳንቱ ጨምረው ገልፀዋል።
መረጃው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ

ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አመራሮች እና በስሩ የሚገኙ ሕብረቶች መሪዎች በጋራ በመሆን በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
መግለጫን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚደንት ዶክተር ጣሰው ገብሬ ሲሆኑ ከትንቢተ ኢርሚያስ 29 ፡7 ላይ “በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።” የሚለውን ክፍል አንስተው ምንም እንኳን ምርኮኞች ባንሆንም ስለሀገራችን ኢትዮጵያ መጸለይ አለብን በማለት ተናገረዋል።
በመቀጠልም ዝርዝር መግለጫው የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ የሆኑት ቄስ ደረጄ ጀንበሩ በጽሁፍ አቅርበዋል።
በጽሁፍ የቀረበው መግለጫም በቅድሚያ እስከ ዛሬ ድረስ የረዳንን እግዚአብሔርን የሚያመሰግን ሲሆን ከዛም በመቀጠል ለሀገራችን ሰላም የተለያዩ አካላት ማድረግ የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ የሚያቀርብ ነው።
በመግለጫውም ፡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች በሙሉ ግጭትን ለማስወገድ ፈቃደኛ እንዲሆኑ ፣ በማንኛውም ምክንያት ተለያይተው የቆዩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ይቅርታ በማድረግ እና ይቅርታን በመቀበል አዲሱን አመት እንዲቀላቀሉ ፣ በማህበራዊ ሚድያ የሚሰሩ አካላት አስታራቂ እና የፍቅር ቃል በማስተላለፍ እንዲተጉ ፣ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ተጠቃሚ የሚሆኑ ወጣቶች ከጎጂ እንቅስቃሴ በመራቅ ለሀገራቸው አስተማማኝ ሰላም እና ለነገው ብሩሕ ተስፋ ሲሉ በትጋት እንዲሰሩ እና የሀገራቸውን ደህንነት እንዲጠብቁ እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች በጋራ በመሆን ጉዳይ የሚመለከታቸውን በሙሉ በመምከር እና በማበረታታት ለሀገራችን ሰላም እንዲተጉ ጥሪ ቀርቧል።
ከዚህም በተጨማሪ ከሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚገኙ የወንጌል አማኝ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሐምሌ 30 - ነሀሴ 2 ፤ 2017 ዓ.ም ስለ ሀገራችን ዘላቂ ሰላም እና ስለ ሕዝባችን አንድነት በጾም እና በጸሎት በእግዚአብሔር ፊት እንዲሆኑ ካውስንሉ ጾም እና ጸሎት አውጇል።
በወንጌል አማኞች ልማድ በሆነው የጳጉሜ ጸሎት ላይም የወንጌል አማኞች ሀገራቸውን በእግዚአብሔር ፊት በጾም እና በጸሎት ይዘው እንዲቀርቡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

❤6