የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.33K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በሐረር ከተማ የግብርና ጥበቃ እና የአየር ንብረት SMART የፕሮጀክት ዲዛይንና አተገባበር ላይ ስልጠና ሰጠ።

‎ከምስራቅ ሐረርጌ ግብርና ጽ/ቤት፣ ከማያ ከተማ ግብርና ጽ/ቤት፣ የባቢሌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ለተወጣጡ 80 መጋቢዎች ፣ለግብርና ባለሙያዎች እና ሞዴል አርሶ አደሮች የግብርና ጥበቃና የአየር ንብረት ስማርት (SMART) የፕሮጀክት ዲዛይንና አተገባበር በሚል ርዕስ ከሐሮማያ ዩንቨርሲቲ በተወከሉት በዶክተር ሚካኤል አበራ ለሁለት ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል ።

ፕሮጀክቱም ‎በኢትዮጵያ የገጠር ማህበረሰቦች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት በማህበረሰብ ልማት ተነሳሽነት የኢየሱስን ፍቅር መጋራትን ግብ ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።

‎ዘላቂ የሆነ የግብርና አሰራርን በማስተዋወቅ እና ለአካባቢው አርሶ አደሮች ስልጠና እና ግብአት በመስጠት የምግብ ዋስትናን ለማሻሻል፣ የሰብል ምርትን ለማሳደግ እና የአየር ንብረት ለውጥ በእርሻ ላይ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተጽኖ ለመቀነስ የሚረዳ ስልጠና እንደነበረ ተገልጾዋል።

‎ስልጠናው በዋናነት የአካባቢውን ማህበረሰቦች በዘላቂነት የግብርና ፕሮጀክቶችን በመንደፍና ትግበራ ላይ ማሳተፍ ያለውን ጠቀሜታ ግብ ያደረገ እንደሆነ ተነግሯል ።

‎ተሳታፊዎቹ ስለ ስልጠናው አድናቆታቸውን ገልፀው የተማሯቸውን ቴክኒኮችና ስትራቴጂዎች በየአካባቢያቸው ተግባራዊ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

‎መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2
በኢትዮጵያ አማኑኤል ህብረት የሥነ መለኮት ኮሌጅ የሐረር ቅርነጫፍ ከሶስት አመት በላይ በዲግሪ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 53 ተማሪዎችን አስመረቀ።

‎ኮሌጁ ሐምሌ 20/2017 ዓ/ም በመጽሐፍ ቅዱስ ስነ መለኮት ዘርፍ ተቀብሎ ያስተማራቸውን ተማሪዎች ለምረቃ ያበቃ ሲሆን ከአንድ ቤተ እምነት ቅጥር አልፎ በመውጣት በልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት እያገለግሉ ያሉ በርካታ አገልጋዮችንም ጭምር ተቀብሎ በማስተማር ላይ ያለ ኮሌጅ ነው ።

‎ከዚሁ ጋር ተያይዞም ኮሌጁ የአገልጋዮችን ህብረት በማጠናከር ረገድ በከተማ ውስጥ ላሉ ለአብያተ ክርስቲያናት በረከት የሆነ ኮሌጅ መሆኑም ተነግሯል።

‎በሐረር አማኑኤል ህብረት ቤተ ክርስቲያን በተካሄደው በዚህ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ እንደተገለፀውም ቤተክርስቲያኗ በዲግሪ መርሀግብር ተማሪዎችን ስታስመርቅ በምስራቁ ኢትዮጵያ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነም ተገልጾዋል።

‎በዕለቱም የሐረር አማኑኤል ዋና መጋቢ ሲሳይ ታፈሰ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለተመራቂዎች አስተላልፈዋል።

‎የአገር አቀፉ የስነመለኮት ኮሌጅ ዲን የሆኑት መጋቢ ተስፋዬ ሽብሩና የኢትዮጵያ አማኑኤል የቤተ እምነቱ ፕሬዘዳንት መጋቢ ጌታሁን ታደሰ በተገኙበት የምረቃው ስነ ስርአት የተከናወነ ሲሆን በመጋቢ ጌታሁን ታደሰ በኩል የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ተሰብኳል።

‎በተጨማሪም ተመራቂ ተማሪዎች የነበራቸውን የትምህርት አመታት የመፅሃፍ ቅዱስ እውቀትን የገበዩበት እና እርስ በእርስም ቤተሰባዊ ህብረት ያጠናከሩትበት እንደነበረም ገልፀዋል።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
2