የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.47K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የሃይማኖት አባቶች የተሳተፉበት 7ኛዉ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ከዚህ ቀደም በነበሩት መረሃ ግብሮች 6 ሚሊዮን ችግኞች መትከላቸውን አንስተው ተክሎ ከመሄድ በዘለለ በመንከባከብ ለሚፈለገው ግብ ማድረስ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ከተማችን አዲስ አበባ እንደስሟ ውብ ለማድረግ ሰላም በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን በአረንጓዴ አሻራም ለማስዋብ ትልቁን አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቁመው አሁንም የከተማችን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ተግተን እንሰራለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ለሀገር ሰላም በጋራ የሚተጉ የሰላም አለኝታ የሆኑ የፀጥታ ኃይሎች አዲስ አበባን ውብና ጽዱ ለማድረግና አሻራቸውን ለማሳረፍ በስፍራው በመገኘታቸው ምስጋናቸው ያቀረቡት በመርሃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ግርማ ሰይፍ ናቸው።

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባለፉት 6 ዓመታት በነበሩት የአርንጓዴ አሻራ የማኖር መረሃ ግብር አባል ቤተዕምነቶችን በማስተባበር በመዲናችን አዲስ አበባ ከ3 ሚሊዮን በላይ ችግኞች እንዲተከሉ ያደረገ ሲሆን በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በተዘጋጀው ሀገራዊ ንቅናቄ ሁሉም አባላት አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ አቅርቧል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ መጋቢ አሸብር ከተማ፣የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊን መጋቢ ታምራት አበጋዝን ጨምሮ የጉባኤው አባል ቤተዕምነት መሪዎች እና ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጠ/መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውን ሌሎች የጸጥታ እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

መረጃው የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ
1👍1

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለፌደራል መንግስት እና ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰላም ጥሪ አስተላለፈች።

ቤተ ክርስቲያኗ ለፌደራል መንግስት እና ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ነው የሰላም ጥሪዋን ያስተላለለፈቸው።
ቤተ ክርስቲያኒቱ ባወጣችው ባለ አራት ነጥብ መግለጫ ለሰላም ይሆናል ብላ ያሰበቻቸውን መፍትሔዎች አስቀምጣለች።

የመጀመሪያው ነጥብ የፌደራል መንግስትም ሆነ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጦርነት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ ንግግሮችን አልያም ድርጊቶችን እንዳያደርጉ የሚያሳስብ ሲሆን ሰላማዊ የሆነ ንግግር እንዲደረግ ፣ ለንጹሃን ጥንቃቄ እንዲደረግ ከዚህም ባለፈ ለመላው ሀገሩ ደህንነት እና ሰላም መልካም የሆነ መንገድ እንዲቀየስ ጥሪ ያቀርባል።

ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉዳዩን በቅርበት እንዲከታተለው እና የፕሪቶሪያው ስምምነት ተግብራዊ መደረጉን እንዲያረጋግጥ ከዛም ባለፈ ስምምነቱን የሚጥስ ማንኛውም አካል ላይ ግልጽ የሆኑ ምላሾች እንዲሰጥ የሚጠይቅ ነው።

ሶስተኛው ነጥብ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ያሉ ሚዳያዎች ጥላቻን የሚዘሩ አልያም ጦርነትን የሚያጎሉ ሀሳቦችን ከማንጸባረቅ እንዲቆጠቡ ከዚህ ይልቅም ለእውነት ፣ ለሀገራዊ አንድነት እና የሰላም ግንባታ የሙያውን ስነ ምግባር በማክበር እንዲሰሩ የሚያሳስብ ነው።

በመጨረሻው ነጥብም ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሰላም ግንባታ እና ለእርቅ በትጋት እንደምትሰራ ተቀምጧል።
በመግለጫው ማብቂያ ላይም ሁሉ ሰው ለክፍፍል ሳይሆን በትህትና ለተሞላ ውይይት እና ለሰላም እንዲቆም ቤተ ክርስቲያኒቱ ጥሪዋን አቅርባለች።

መረጃውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
3