መሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በለገጣፎ ላሉ እና ለተቸገሩ 1200 ወገኖች የአይነት ድጋፍ አደረገች።
የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚደንት የሆኑት መጋቢ ደሳለኝ አበበ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ በለገጣፎ አከባቢ የተደረገው ድጋፍ ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ የጻፉ ሲሆን ለ1200 ወገኖች የተደረገው እርዳታ ምግብን፣ ብርድልብሶችን እና የመማሪያ ቁሳቁሶችን ያካተተ እንደሆነ አሳውቀዋል።
የተደረገው እርዳታ ብዙ ገንዘብ ወጪ የተደረገበት እንደሆነ ያነሱት መጋቢው ለተቸገሩ ወገኖች ተስፋን እና ፍቅርን ለማሳየት የተበረከተ ነው ሲሉ ስለ እርዳታው በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።
ድጋፉም እውን መሆን የቻለው በመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የልማት ኮሚሽን እና በኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ትብብር ነው።
መጋቢ ደሳለኝ አበበም የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር በተግባር ሲገለጽ ማየት አበረታች እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን ይህም የተደረገው አዲስ የትምህርት አመት እየተቃረበ ባለበት ግዜ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው አስፍረዋል።
መረጃውን ከፕሬዚደንቱ የፌስቡክ ገጽ ላይ አገኘነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቭ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

❤2
የሰሜን ምስራቅ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በደሴ ከተማ ሲካሄድ ቆይቶ ፍፃሜውን ማግኘቱ ተገለጸ ።
ጉባኤው ከአንፆኪያ እና ኬሚሴ ጀምሮ እስከ ከአላማጣ እስከ ኮረም ድረስ ከሚገኙ 25 ከተሞች የመጡ ተማሪዎች የተሣተፉበት ጉባኤ ሲሆን ዋና ትኩረቱ የዘፍጥረት መጽሐፍን አሳታፊ በሆነ መንገድ ማጥናት መሆኑ ተገልጾዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ ፌሎሽፕ መመስረት እና ማጠናከር ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
የጉባኤው ተሣታፊ ተማሪዎች፣ የቤተሰብ ቡድን አገልግሎት ስልት እና አገልጋይ መሪነት በሚሉ አርእስቶች ላይ ጠቃሚ ሴሚናር ወስደዋል።
ተማሪዎች የመጡባቸው ከተሞች በወንጌል ያልተደረሱ ሲሆኑ በአንድኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 1 ክርስቲያን ተማሪ ብቻ ያለባቸው ከተሞች ጭምር እንደሚገኙ በመድረኩ ተጠቅሷል። ተሣታፊዎች አካባቢያዊ ሁኔታቸውን ያገናዘበ ወዳጃዊ ወንጌልን የመመስከር መንገድ ማለትም የመፀለይ የመንከባከብ የማካፈል እና አለም አቀፍ የእግዚአብሔር ራዕይ የሚሉ ስልጠናዎችንም ወስደዋል።
በአራት ቀን ቆይታችው፣ ከወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች እና ከቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር አሶሼት ተሳታፊዎች ጋር የውይይትና የአብሮነት ጊዜ አሳልፈዋል።
የሰሜን ምስራቅ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልል ብዙ ፀሎት የሚያስፈልገው እንደሆነ እና አማኞች እንዲበረቱ ፤ በአካባቢው እያገለገሉ ለሚገኙ ቅዱሳን የወንጌል እሣት በተማሪዎች መካከል እንዲቀጣጠል እንዲጸለይ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የክርስቲያን ዜና ነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ

❤1