የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.54K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ ክልል የባሌ ጎባ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን 50ኛ የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።

"ዘመን ተሻጋሪ የወንጌል የማዳን ሃይል” በሚል መሪ ቃል የቤተክርስቲያኒቱ ምስረታ 50ኛ የወርቅ ኢዩቤልዩ ሲከበር የቤተ እምነቱ ም/"ፕሬዝዳንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው፣ ከአዲስ አበባ፣ ከአዳማ፣ ከሀዋሳ ከአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የመጡ ቀደምት የቤተክርስቲያኒቱ አባላትና አገልጋዮች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው በበኩላቸው የጎባ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ከራሷ አልፋ በሀገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አገልጋዮችን አፍርታ ሰጥታናለች በማለት ካመሰገኑ በኋላ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

በበዓሉ ላይም በ1966 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጌልን የሰበኩትና የአሁኑ የኢ/ወ/አ/ክ/ህ ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ ጻዲቁ አብዶ የእግዚአብሔርን ቃል ሰብከዋል፡፡ እንዲሁም ከመጋቢ ጻዲቁ ጋር ከጅማሬው ጀምሮ አብሮ ወንጌልን የሰበኩትና አሁን የአይ ኤል አይ መስራችና መሪ የሆነት ፕሮፌሰር ባደግ በቀለ የእግዚአብሔርን ቃል በማካፈል አገልግለዋል፡፡

የጎባ ሙሉ ወንጌል "ሀ" መዘምራን የመዝሙር አልበማቸዉን ከማስመረቅ በተጨማሪ በበዓሉ ላይ በዝማሬ አገልግለዋል፡፡ በዓል ላይ የጎባ ክ/ከተማ ም/አስተዳዳሪ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።በመጨረሻም የቤ/ክ የመሪዎች ጉባዔ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሀይሉ ንባቢ በተለያየ መንገድ ለበዓሉ መሳካት አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሁሉ አመስግነው በዓሉ ለታላቅ ደስታና መጽናናት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፤ ቤተልሔም ደረጄ
በዓለም አቀፍ የሚሽን ጉባኤ ላይ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በፕሬዚደንቷ መወከሏን አስታወቀች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ጨመሮ የተለያዩ አለም አቀፍ አብያተክርስቲያናት በመስራች አባልነት በሚመሩት አለም አቀፍ የሚሽን ጉባኤ (International Mission Association/#IMA) አዘጋጅነት በማዕከላዊ አሜሪካ ሁንዱራስ ዋና ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ስብሰባ ላይ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በፕሬዚዳንቷ ተወክላለች።


በያዝነው ሳምንት በጀመረውና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተወጣጡ የቤተክርስቲያን መሪዎች በወንጌል አገልግሎት ዙሪያ እየመከሩ በሚገኙበት ስብሰባ ላይ የታደሙት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ በጉባኤው የቤተክርስቲያኒቱን የወንጌል እንቅስቃሴ ልምድ ከማካፈል በተጨማሪ በሌሎች አለማት ያለውን የወንጌል ተልዕኮ አካሄድ ከስብሰባው ተሳታፊዎች ጋር የሚለዋወጡ ይሆናል።


ይህ ጉባኤ ለቤተክርስቲያኒቱ ልምድ ከመለዋወጥ ባሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚኖራት የወንጌል ተጽዕኖ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይታስባል።
መረጃውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ የማህበራዊ ሚድያ ገጽ ላይ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
5👍3