በአሜሪካ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸው እምነት እየጨመረ እንደመጣ ተገለጸ።
በቅርቡ በጋልአፕ ፖል የተደረገ ጥናት በአሜሪካ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ የነበራቸው እምነት ካለፉት አስርት አመታት በተለየ እየጨመረ መምጣቱን አመላክቷል።
በፈረጆቹ 2024 36 በመቶ የሚሆኑት አሜሪካውያን በቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ የሆነ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል። ይህም በ2022 ከነበረው 31 በመቶ የአምስት በመቶ እድገት ያሳየ ሆኖ ተገኝቷል።
ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ የተስተዋለው የመጀመሪያው እድገት ሲሆን ሴቶች፣ አፍላ ወጣቶች ፣ እና አነስተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ለቤተ ክርስቲያን ድጋፍ እያሳዩ ካሉ አሜሪካውያን መካከል ይጠቀሳሉ።
በሃገሪቱ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ጥናቱ ሲያሳይ ለሪፐብሊካኖች ያለው ድጋፍ ከ49 በመቶ ወደ 64 በመቶ ያደገ ሲሆን በዴሞክራቶች ላይ አሜሪካውያን ያላቸው እምነት ደግሞ ከነበረበት ቀንሷል ፡ ለዚህም ዴሞክራቶች የሃይማኖት ተቋማትን በተመለከተ ያላቸው ጽንፍ የረገጠ አመለካከት እንደምክንያት ይነሳል።
በቤተ ክርስቲያን ላይ ያለው እምነት እየጨመረ መምጣቱ እንዳለ ሆኖም በሀገሪቱ ቤተ ክርስቲያን ካላት ተዓማኒነት በላይ ትንንሽ ቢዝነሶች እና ወታደራዊ ተቋማት የበለጠ ተዓማኒነት አላቸው። ይህም በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን በግዜ ሂደት ያጣችውን ተዓማኒነት በማግኘት ላይ እንደሆነች ጥናቱ ያመላከተ ሲሆን ይህም በጊዜ ሂደት ውስጥ ማህበረሰብን የማነጽ ድርሻዋን ሊያሰፋው እንደሚችል ተነግሯል።
መረጃውን ከክርስቲያን ፖስት አገኘነው
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ

❤3
አራይዝ ሊደርሺፕ ሰሚት 2025 በኢንዶኔዢያ በይፋ ተጀመረ።
በአራይዝ ሊደርሺፕ ሰሚት ከ22 ሀገራት 300 ተሳታፊዎች ለአራት ቀናት በአምልኮ እና በትምህርት የአንድነት ጊዜ አሳልፈዋል። በአራይዝ ኤሲያ የተዘጋጀው ሰሚት ወጣቶችን በወንጌል ያልተደረሱ ቦታዎችን ለመድረስ ማነሳሳት ያለመ ሲሆን መሪ ቃሉም “በአከባቢው ስር የሰደደ ፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተገናኘ እና ወንጌል ወደ ሌለበት ቦታ የሚሄድ” የሚል ነው።
የመሪዎች ሰሚቱ የመክፈቻ ፕሮግራምም የተለያዩ ባህሎችን የሚያንጸባርቁ መርሃ ግብሮች የተካሄዱበት እንዲሁም የሀገራቱ ባንዲራዎች የታዩበት ነበር። በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ሪቨረንድ ዶክተር ዴቪድም ኤሲያ ሚሽነሪዎች ተቀባይ ከመሆን ሚሽነሪዎችን የምትልክ አህጉር መሆን አለባት በማለት ተናግረዋል።
ሬቨረንድ ሮ የዘመኑ ወጣቶች ትጉሆች አይደሉም በሚል የሚቀርብባቸውን ዘለፋ እንደማይቀበሉ የተናገሩ ሲሆን ምክንያታዊ እና ለመንፈሳዊ ነገር ልባቸው ክፍት የሆነ ትውልድ ናቸው በማለት ተናግረዋል።
አክለውም ቤተ ክርስቲያኖች ወጣቶቻቸውን ለዓለም ዓቀፍ የሚሽን አገልግሎት ማነሳሳት እንዳለባቸው ተናግረው ከዚህም ባለፈ ወጣቶች በአመራር እና በታማኝነት ብቁ ለማድረግ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
የተካሄደው ሰሚቱም የአራይዝ ኤስያን ራዕይ ለማጎልበት የሚደረግ ሲሆን ዓላማውም ከኤሲያ ወንጌል ወዳልደረሰባቸው ሌሎች ሀገራት ወንጌልን ይዘው የሚሄዱ ወጣቶች ለማብቃት ነው። ዶክተር ሮ እንደተናገሩትም መርሃግብሩ ከአንድ ጊዜ ክስተት ያለፈ እና እግዜአብሔር ለዓለም ሕዝብ ሁሉ መፍትሔ እንድትሆን በኤሲያ ቤተ ክርስቲያን እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ነው።
መረጃውን ከክርስቲያን ዴይሊ አገኘነው።

❤11
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 4ተኛውን ሀገር ዓቀፍ የሰላም ጉባኤን በተመለከተ መግለጫ ሰጠ።
የፊታችን ሐምሌ 28 እና 29 በሀረር ከተማ የሚደረገውን 4ተኛ ሀገር ዓቀፍ የሰላም ጉባኤን በተመለከተ ሐምሌ 23 የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሃፊ ክቡር ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ መግለጫ ሰጥተዋል።
4ተኛው ሀገር ዓቀፈ የሰላም ጉባኤ በሀረር ከተማ ለ4ተኛ ጊዜ የሚደረግ ሲሆን ከዚህ በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ በድሬዳዋ ቀጥሎ በጅማ ለ3ኛ ጊዜ ደግሞ በባህር ዳር መካሄዱ ይታወሳል።
ጠቅላይ ጸሐፊ አክለውም የሰላም ጉባኤ በየ2 ወሩ እንደሚከናወን አንስተው ጉባኤው ከሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጅ ጠቁመዋል።
ጉባኤው ከያዛቸው ዓላማቸው ውስጥም አለመግባባቶችን ማስቆም እና ሰላም ማስፈን ፣ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህልን ማዳበር ፣ በዘርፉ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎቻቸውን አቅርበው የሚወያዩበትን መድረክ መፍጠር ፣ ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ከሀገር እና ከፈጣሪ የተጣለባቸው አንደራ እንዲወጡ ማስቻል እና ህብረተሰቡን አስተባብሮ ሀገሩን እንዲጠብቅ ማስቻል ይገኙበታል።
ከዚህ በፊት የተደረጉ ጉባኤዎች ሕብረተሰቡ በሀገር ጉዳይ የባለቤትነት ስሜት እንዲያደርበት ከማድረግ ፣ የሃይማኖት ተቋማት እንዲቀራረቡ ከማድረግ እና ሌሎች የግል እና የመንግስት ተቋማት ጋር የመስራት ልምድን ከመፍጠር አንጻር ውጤቶች የታዩበት እንደሆነም ተናግረዋል።
ስለጉባኤው በዝርዝር ያነሱት ቀሲስ ታጋይ ታደለ በመጀመሪያ ሐምሌ 26 እና 27 ሁሉም ተሳታፊዎች ወደ ሀረር ከተማ እንደሚገቡ አሳወቀዋል።
በስፍራው በሚኖረው ጉባኤም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና ከሀረማያ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፍ እንደሚያቀርቡ እና ከዛ በኋላ መከናወን ባለባቸው ነገሮች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተነስቷል።
በስፍራው ታዋቂ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች እና የመንግስት አካላት አረንጓዴ አሻራቸውን የሚያስቀምጡ ሲሆን መሪዎች እን የሀገር ሽማግሌዎች ግጭትን አስቀድሞ መከላከል ላይ እንዲሰሩ የማሳሳብ ስራ እንደሚሰራም በመግለጫው ተጠቅሷል።
ሐምሌ 28 የሚደረገው የፓናል ውይይት እንደተጠናቀቀ ሐምሌ 29 በኢማን አህምድ ስታዲየም ነዋሪዎች በተሳተፉበት ሕዝባዊ የሰላም ኮንፍረንስ የሚካሄድ ይሆናል።
በስታዲየሙ በሚደረገው ፕሮግራም ላይም በዛ የሚገኙ አካላት ሁሉ ለሀገራችን የሰላም ጥሪ የሚያቀርቡ ሲሆን በሰላም ጉዳይ አስተዋጾ ላደረጉ የምስጋና እና የእውቅና ስጦታ እንዲሁም የሰላም ዋንጫ የሚበረከት ይሆናል።
በእለቱም ቀጣዩ የሰላም ጉባኤ የት እንደሚካሄድ ይፋ እንደሚደረግ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ በመግለጫቸው ገልጸዋል።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ተስፋኢየሱስ ፍቃዱ

❤1
ባርሄ ሚኒስትሪ ከሀርቫስት ኢንተርኮንቲነንታል ሚኒስትሪ ጋር በጋራ በመሆን ለሁለት ቀን የሚቆይ የወንጌል ስርጭት አዘጋጁ ።
በወንጌል ስርጭቱ መጀመሪያ ባለራዕይ ገረመው ጎሳዬ የመክፈቻ ንግግራቸውን ያደረጉ ሲሆን ከፕሮፌሰር ሚኒስትር ፓትሪሺያ አይካ ጋር ከዚህ ቀደም በተለያዩ የወንጌል ስራዎች ላይ በጋራ መሳተፋቸውን ተናግረዋል።
ሚኒስትር ፓቲሪሺያ አይካ በበኩላቸው በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በአካል ተገኝተው ይህንን የወንጌል ተልዕኮ ለሌሎች ለማድረስ በጋራ ለመስራት እንደመጡ እና ለሁለት ቀናት በዘነበ ወርቅ በአየር ጤና እና በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ የንግድ ማዕከል በሆነው በመርካቶ ላይ ወንጌል ለመስራት መገኘታቸውን ገልጸዋል።
እንዲሁም ሚኒስትር ፓትሪሺያ "እግዚአብሔር ከዚህ ቀደም ከባርሄ ሚኒስትሪ ጋር በጋራ ስሰራ የነበረው የወንጌል አገልግሎትን ይበልጥ መጥቼ እንድሰራ ስላደረገኝ እና በኢትዮጵያ ተገኝቼ ለሁለት ቀናት የወንጌል ስርጭት ለማድረግ እንዲሁም ስልጠና ለመስጠት ስለቻልኩ አመሰግነዋለሁ።” በማለት ተናግረዋል።
ሚኒስትር ፓትሪሺያ አይካ ከ2009 እስከ 2012 እ.አ.አ በኢትዮጵያ ተገኝተው ለፋርማሲ ተማሪዎች ወንጌልን መስራታቸው እንዲሁም ከ12 አመታት በላይ ከሚኒስትር ካሌብ ጋር ብርቱ የሆነ የወንጌል አገልግሎት ሲሰሩ መቆየታቸውን በዚህም ደቀመዝሙርን ማፍራታቸውን በስብሰባው ገልጸዋል።
ሚኒስትር ፓትሪሺያ አይካ ከ450 በላይ ቤተክርስቲያናትን በተለያዩ ሀገራት ስለመመስረታቸው እንዲሁም ትልቅ ራዕይም እንዳላቸው ተናግረዋል። ቤተ ክርስቲያኒቷ ተልዕኮዋ የጠፉትን ነፍሳት ለማዳን ዋጋ ከፍሎ ደቀመዝሙር ማድረግ ላይ መሰረት አድርጋ እንደምትሰራ ገልጸዋል።
እንዲሁም “አማኞች የእግዚአብሔርን ሃይል እና መንፈስ ተቀብለናል እና ለሌሎች ነፍሳት ይህንን የተካፈልነውን ወንጌል በማድረስ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ልንጠራ ይገባል።” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በንግግራቸውም መጽሐፍ ቅዱስን ከዘፍጥረት እስከ ዩሐንስ ራዕይ ማወቅ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ እና ለሌሎች ይህንን ወንጌል ማድረስ እንዳለብን አስታውቀዋል።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቃልኪዳን እንዳለ

በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የቤተ ክርስቲያ አንድነት ሥነ-መለኮት (The Theology of Church Unity) በሚል ርዕስ ሥልጠና በአዶላ ከተማ ተሰጠ።
በአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ ከበርካታ ሰበካዎችና ማኀበረ ምዕማናንን ለተወጣጡ ቁጥራቸው ከ1,300 በላይ ለሚሆኑ ወንጌላዊያን፣ ቄሶችና የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ሥልጠናው ተሰጥቷል። ሥልጠናውን የቤተ ክርስቲያኒቱ የወንጌልና ቲዮሎጂ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል ሰጥተውታል።
የቤተ ክርስቲያኒቱም ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ሥልጠናው ላይ ተገኝተው ለአገልጋዮቹ ጠቃሚ መልክዕቶችን አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙና የቤተ ክርስቲያኒቱ የወንጌልና ቲዮሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል በአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ እየተገነባ የሚገኘውን የአንደኛ ጀረጃ ትምህርት ቤት የህንፃ ግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል።
የህንፃ ግንባታ ሂደቱም ከዚህ በፊት ከመጡበት ወቅት አንፃር ከፍተኛ ልዩነት እንዳለውና በፍጥነት በመገንባት ላይ መሆኑ እንዳስደሰታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ገልጸዋል። አሁን እየተካሄደ ባለበት መልኩ ጥራቱን ጠብቆ መገንባቱ እንዲቀጥል አበረታተዋል።
የሲኖዶሱም ፕሬዚዳንት ቄስ ጌሎ ጎሎልቻ የትምህርት ቤቱ ሙሉ ወጪ ከምዕመናን በሚሰበሰብ አስተዋጽኦ እየተገነባ መሆኑን ገልፀው ቤተ ክርስቲያን በራሷ አቅም ፕሮጀክቶችን ሰርታ ማጠናቀቅ እንደምትችል ማሳያ እንደሚሆን ገልጸዋል።
የትምህርት ቤቱ መደበኛ የትምህርት መስጫ ብሎኮች ሲጠናቀቁ ደረጃውን የጠበቀ ከ1ኛ-8ኛ ክፍል የሚያስተምር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የሲኖዶሱ ፕሬዚዳንቱ ጨምረው ገልፀዋል።
መረጃው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ነው።
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ ቤተልሔም ደረጄ