Dn Abel Kassahun Mekuria
15.3K subscribers
538 photos
48 videos
1 file
844 links
ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው።

ይወዳጁን

ለፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL

ለyoutube
https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_

ለInstagram
https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW
Download Telegram
Live stream scheduled for
የክለሳ ጥያቄዎች
(አደራ ተሳተፉ)

1 ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በምን ዓይነት መንገዶች ለአባቶቻችን ተናገረ?


2 በኦሪት በነቢያት አድሮ ይናገር የነበረው እግዚአብሔር ቢሆንም ሐዲስ ኪዳን ከመጣ በኋላ ግን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ተሽረዋል? እውነት ወይስ ሐሰት? ማብራሪያ ያክሉበት።


3 ቅዱስ ጳውሎስ ለምን “ቀድሞ በነቢያት በዚህ ዘመን መጨረሻ ግን በልጁ ተናገረን” ሲል ለመጀመር ፈለገ? ንግግሩስ ምንን ያሳያል?
36👍12
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
193🙏34😢21👍13👌2
ክቡራን፣

ክፍል አምስት ትምህርታችንን ዛሬ ልክ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ በዚህ https://tttttt.me/Dnabel የቴሌግራም ቻናል በlive stream ትምህርቱ ይሰጣል።

እንደ አማራጭ ይህን ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ደግሞ በzoom ልትቀላቀሉን ትችላላችሁ።

https://us05web.zoom.us/j/84709079682?pwd=obn6Rc8YrJjSTaAAeRwKmNbMC2kY8n.1
31👍12
ሰላም፣
ዛሬ ጉባኤውን ማድረግ የማንችልበት ምክንያት ስለ ገጠመን የዚህ ሳምንት ትምህርታችን ወደ ቀጣይ ተሸጋግሯል። ያለፈው ሳምንት ክፍል ፬ ትምህርት ማታ YouTube ላይ ይለቀቃል።

የዕድሜ በረከቱን አይንሳን!
142🙏28👍19👏4
“ሕዝቅያስ ግን እንደ ተቀበለው ቸርነት መጠን አላደረገም”
2ኛ ዜና 32:25
137👍5🙏4
ክቡራን፣

ክፍል አምስት ትምህርታችንን ዛሬ አርብ መጋቢት 26 ልክ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ በዚህ https://tttttt.me/Dnabel የቴሌግራም ቻናል በlive stream ትምህርቱ ይሰጣል።

እንደ አማራጭ ይህን ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ደግሞ በzoom ልትቀላቀሉን ትችላላችሁ።

https://us05web.zoom.us/j/84709079682?pwd=obn6Rc8YrJjSTaAAeRwKmNbMC2kY8n.1
51👍13🙏6
የክፍል 4 ትምህርት የክለሳ ጥያቄዎች


1 ቅዱስ ጳውሎስ ወልድን “ሁሉን ወራሽ” ብሎ የጠራው ለምንድር ነው?


2 በአምላክ ሰው መሆን ትምህርት ውስጥ “ተዋሕዶ” ሲባል ምን ማለት ነው?


3 ሐዋርያው “ዓለማትን በፈጠረበት” ሲል ምን እያለን ነው? “ፈጠረበት” የሚለውን ቃል እንዴት ነው የምንረዳው?
👍236👏1👌1
Live stream scheduled for
Live stream started
Live stream finished (58 minutes)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“የተሰቀለው ክርስቶስን የሚያይ እና እምነቱንም በእርሱ ላይ የሚያኖር፣ ከኃጢአት ቁስሎቹ ሁሉ ይፈወሳል”

የሂፖው ሊቀ ጳጳስ አውግስጢኖስ

አቤቱ መድኃኔዓለም ሆይ፥ በስቅለት በመከራህ የተዘራሁ፣ በደምህም ላይ የበቀልኩ ፍሬ ነኝና ጠውልጌ እንድቀር አትተወኝ።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel

ስብከቱ፡ የክቡር ሊቅ አለቃ አታሌው ታምሩ
191🙏37👍13😢8🥰7
+++ ያለ እግዚአብሔር "እንደ እግዚአብሔር" +++

በእባብ ሥጋ ተሰውሮ ወደ ሔዋን የመጣው ሰይጣን ሴቲቱን ያታለለበት የሐሰት ቃል "ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው" የሚል ነበር።(ዘፍ 3፥5) ይገርማል! በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረ የሰው ልጅ እንደ እግዚአብሔር (እርሱን መስሎ) የመኖር ፍላጎት እንዳለው ሰይጣን ያውቃል። ይህ ውሳጣዊ ፍላጎቱ ላይ ለመድረስ በሃይማኖትና በበጎ ምግባር ከማደግ ይልቅ ባልተገባ መንገድ ፍለጋውን ያደርግ ዘንድ አዲስ ስብከት አመጣለት። ምን የሚል? "ያለ እግዚአብሔር 'እንደ እግዚአብሔር' ትሆናላችሁ" የሚል። በምን? በቅጠል።

ዛሬም ሰይጣን ያለ እግዚአብሔር "እንደ እግዚአብሔር" ትሆኑባችኋላችሁ ሲል የሚያሳየን እንደ ገንዘብ፣ ዕውቀት፣ ጉልበት ያሉ ብዙ ቅጠሎች አሉ። ነገር ግን እኛ ክርስቲያኖች እርሱን ወደ መምሰል የምናድግበት ብቸኛው መሰላላችን ረድኤተ እግዚአብሔርና የማይቋረጥ የእኛ ሩጫ ነው። እርሱ ሳይኖር እና ሳያካፍል እኛ በራሳችን የምንካፈለው ምንም አምላካዊ ምሳሌነት የለም።(2ኛ ጴጥ 1፥4)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
143👍17🙏8🥰1🫡1
በኢያሪኮ መንገድ ቆመው ይለምኑ የነበሩ ሁለት ዓይነ ስውሮች ክርስቶስ በዚያ እያለፈ መሆኑን ሲሰሙ "የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን" እያሉ ፈውስ ይማጸኑት ጀመር። ነገር ግን ከጌታችን ፊት ቀድመው ይሄዱ የነበሩ ሰዎች እኒህን ነዳያን "ዝም በሉ!" ብለው ገሰጿቸው።(ሉቃ 18፥39) ልብ በሉ፤ የገሰጿቸው ሰዎች ጌታን ከኋላ የሚከተሉ ወይም ከአጠገቡ አብረው የሚሄዱት አልነበሩም። ከፊት ከፊት የሚቀድሙት እንጂ። በእርግጥም ከጌታው ፊት ቀደም ቀደም የሚል ሰው ጠባይ ይህ ነው። ራሱን ከባለቤቱ በላይ ዐዋቂ ያደርጋል። ምስኪኖችን "ዝም በሉ" እያለ የሚያሳቅ፣ የጌታውን ቸርነት የሚሸፍን አጉል ጠበቃ ይሆናል። እስኪ አሁን "ማረን" ማለት ምን ነውር አለው? ቃሉስ የስድብ ያህል የሚያስቆጣና "ዝም በሉ" የሚያሰኝ ነው? እነዚህ ሁለቱ ዕውሮች የገጠሟቸው እንዲህ ያሉ "በባለቤቱ ያልተወከሉ ጠበቆች" ነበሩ። ግን አልተበገሩም "ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ ማረን" እያሉ ከቀድሞው ይልቅ አብዝተው ጮኹ። እርሱም ልመናቸውን ሰምቶ ወደዚህ አምጧቸው አለ፣ ፈወሳቸውም።

እነ እገሌ ፊት ነሱኝ፣ ተቆጡኝ፣ አመናጨቁኝ ብለህ ከቤተ ክርስቲያን አትቅር ጸሎትህንም አታቋርጥ። ጉዳይህን ከባለቤቱ ጋር ብቻ አድርግ። ያኔ የልመናህን ድምፅ ይሰማል። ሊፈውስህም ወደ እርሱ የሚያቀርቡ ወዳጆቹን ይልክልሃል።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://tttttt.me/Dnabel
233🙏23👍16