Dn Abel Kassahun Mekuria
15.3K subscribers
538 photos
48 videos
1 file
845 links
ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው።

ይወዳጁን

ለፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL

ለyoutube
https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_

ለInstagram
https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW
Download Telegram
+++ "ለዚህ መች ጸለይን?" +++

በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቤተሰባዊ የሆኑ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲረዳ የተቋቋመ የካህናት (የቀሳውስት) ጉባኤ ነበረ። የቀድሞው የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ሺኖዳም ይህን ስብስብ እንዲቀላቀሉ ለአባ ሚካኤል ባቀረቡላቸው ጥሪ መሠረት የዚህ ጉባኤ አባል ሆኑ። ታዲያ አንድ ቀን አባ ሚካኤልን ጨምሮ የጉባኤው የበላይ ኃላፊ የሆኑት ጳጳስና ሌሎችም ካህናት የተጣሉ ባልና ሚስትን ሊያስታርቁ ተሰበሰቡ። ይሁን እንጂ የባልና የሚስትየው ጠብ እንዲህ በቀላሉ ሊበርድ የሚችል አልነበረምና ጳጳሱም ሆኑ ቀሳውስቱም ሁለቱን ለማስማማት ብዙ ቢጥሩም ግን አልተሳካላቸውም።

በስተመጨረሻም ጳጳሱ ወደ አባ ሚካኤል እየጠቆሙ "አባ ሚካኤል ለምን ዝም ብለው ተቀመጡ? እስኪ እርሶ ይሻላል ብለው የሚያስቡትን ይንገሩን?" አሏቸው። አባ ሚካኤልም "ብፁዕነትዎ፣ እንጸልይበት!" አሉ። ጳጳሱም "ይህን ጉባኤ ከመጀመራችን በፊት እኮ ጸልየናል" ቢሏቸው አባ ሚካኤል "አዎን አባታችን፤ ለዚህ ችግር ግን አልጸለይንም" አሉ። ከዚያ ሁሉም ለጸሎት ተነሡ። በጳጳሱ ፈቃድ በአቡነ ሚካኤል መሪነት ጸሎት አደረጉ። ጸሎቱ እንዳለቀም እነዚያ የተጣሉት ባልና ሚስት ክርክራቸውን ሁሉ ትተው በጉባኤው ፊት በፍቅር ተቃቀፉ። ሰላም አወረዱ። ይህን ጊዜ ከቀሳውስቱ አንዱ "አባታችን ከመጀመሪያ እንዲህ ቢሉን ምን ነበር?! አሳረፉን እኮ" ብለው ጉባኤውን ፈገግ አሰኙት።

እኛስ ያልጸለይንባቸው ስንት ችሮች አሉብን?

ብዙ ቋጠሮ የሚፈታው ግን በብዙዎች የሚረሳው ትልቁ መፍትሔ፣ ጸሎት!!!

(አባ ሚካኤል ኢብራሂም (1899-1975) የግብጽ ቤተ ክርስቲያንን ለበርካታ ዓመታት በትጋት ያገለገሉና እጅግ የሚያስቀና የጸሎት ሕይወት የነበራቸው አባት ናቸው።)


ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
አዲስ አበባ
240👍31🙏24🥰9🔥2
ሰላም እንዴት ቆያችሁ፣

ያለፈው ሳምንት የመግቢያ ትምህርታችን እንዴት ነበር? እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ቀጣይ ሁለተኛውን ክፍል ነገ አርብ የካቲት 28 ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ እንማራለን።

ትምህርቱ የሚተላለፍበትን ይህን የTelegram Channel link ለብዙዎች በማጋራት የቃለ እግዚአብሔሩ ተሳታፊ ያድርጉ።

“ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ” መዝ 119:162


https://tttttt.me/Dnabel
84👍23🙏9
"ስላንቺም የተነገረው ፍጹም ምስጋና ሁሉ በምስጋናሽ ባሕር ጥልቅነት ዘንድ እንደ ጠብታ ነው።... የምስጋና ዘውድ በራስሽ ላይ ነው። የጽድቅ ጋሻም አንቺን ይከባል።... ሳላቋርጥ አመሰግንሽ ዘንድ የኪሩቤልን አፍ፣ የሱራፌልን ልሳን ብቀበል፤...የሰሎሞንን ጥበብ ብነሣ፣ የልቡናዬም አጽቅ ቢሰፋ እስከ ባሕር ቢዘረጋም፣ የቃሌም ቡቃያ እስከ ቀላይ ድረስ ቢጠልቅ በዚህ ውዳሴሽን ለመፈጸም አልችልም"

የፍቅሯ ኃይል ያረፈበት፣ የስሟም አጠራር ከአፉ ከማይጠፋ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገኘ የምስጋና ቃል

https://tttttt.me/Dnabel
223👍16🙏14🥰4
ክፍል ሁለት ትምህርታችንን ዛሬ ልክ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ በዚህ https://tttttt.me/Dnabel የቴሌግራም ቻናል በlive stream ትምህርቱ ይሰጣል።

እንደ አማራጭ ይህን ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ደግሞ በzoom ልትቀላቀሉን ትችላላችሁ።

https://us05web.zoom.us/j/84709079682?pwd=obn6Rc8YrJjSTaAAeRwKmNbMC2kY8n.1
👍4336🙏3
Live stream scheduled for
ትምህርቱን ከመጀመራችን በፊት ለክለሳ የሚረዳ መመዘኛ ተዘጋጅቷል። መልሳችሁን በcomment section ላይ 1 2 እያላችሁ በአጭሩ አስቀምጡ። (ሙሉውን ያገኘ ይሸለማል)

1 በሐዋርያት ሥራ የቅዱስ ጳውሎስ ታሪክ የሚጀምረው ከስተኛው ምዕራፍ ነው ?

2 ሳውል ክርስቲያኖችን ያሳድ የነበረው ከጥላቻ የተነሣ ነው?

3 ሳውል በደማስቆ እንዴት ሊያምን ቻለ ?

4 ሳውልን ያጠመቀው ካህን ማን ይባላል ?

5 የቅዱስ ጳውሎስ ሮማዊነት ምን ጠቀመው?

6 በአሳዳጅነት ተጀምሮ በተሳዳጅነት የሚፈጸመው የጳውሎስ ታሪክ ለእኛ ምን መልእክት አለው?
🙏43👍146
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
“ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል፡ አለች። በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፥ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። እነሆ፥ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ፥ ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ”

ኢሳ 49:14-16
231👍15🙏11🤔3
ሰላም እንዴት ቆያችሁ፣

“ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ” ዕብ 1:1


እስኪ ማን ነው ይህን ጥቅስ በቃሉ በማጥናት ለነገ ትምህርት እየተዘጋጀ ያለው? አርብ መጋቢት 5፣ ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እንደ አምላክ ፈቃድ እንገናኛለን።

ትምህርቱ የሚተላለፍበትን ይህን የTelegram Channel link ለብዙዎች በማጋራት የቃለ እግዚአብሔሩ ተሳታፊ ያድርጉ።

“ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ” መዝ 119:162


https://tttttt.me/Dnabel
🙏6549👍22🥰6
Live stream scheduled for
ክፍል ሦስት ትምህርታችንን ዛሬ ልክ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ በዚህ https://tttttt.me/Dnabel የቴሌግራም ቻናል በlive stream ትምህርቱ ይሰጣል።

እንደ አማራጭ ይህን ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ደግሞ በzoom ልትቀላቀሉን ትችላላችሁ።

https://us05web.zoom.us/j/84709079682?pwd=obn6Rc8YrJjSTaAAeRwKmNbMC2kY8n.1
🙏17👍1312
ትምህርቱን ከመጀመራችን በፊት ለክለሳ የሚረዱ መመዘኛ ጥያቄዎች። እንደ ተለመደው መልስዎን group chat ላይ ያስቀምጡ። (ባለፈው ሳምንት የነበራችሁ ተሳትፎ እጅግ በጣም አስደሳች ነበር)


1 ስለ ቅዱስ ጳውሎስ መልእክት መጻፍ የተናገረው ሐዋርያ ማን ይባላል?
2 ቅዱስ ጳውሎስ የዕብራውያን መልእክት ላይ ለምን በሰላምታ አልጀመረም? ስሙንስ እንደ ሌሎች መልእክታቱ ለምን አልጠቀሰም?
3 የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ቅዱስ ጳውሎስ ለመሆኑ ምን ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል?
4 የዕብራውያን መልእክትን ወደ ኢየሩሳሌም ያደረሰላቸው ማን ነው?
5 ቅዱስ ጳውሎስ ይህን የዕብራውያን መልእክት ለምን ወይም በምን ዓላማ ጻፈው?
🥰55👍2521
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
384🙏40👍21🥰21❤‍🔥9😇6👏3🔥2
“ላልፈለጉኝ ተገኘሁ፥ ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ”
ሮሜ 10:20
187🙏33👍1
ክቡራን፣

ክፍል አራት ትምህርታችንን ዛሬ ልክ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ላይ በዚህ https://tttttt.me/Dnabel የቴሌግራም ቻናል በlive stream ትምህርቱ ይሰጣል።

እንደ አማራጭ ይህን ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ደግሞ በzoom ልትቀላቀሉን ትችላላችሁ።

https://us05web.zoom.us/j/84709079682?pwd=obn6Rc8YrJjSTaAAeRwKmNbMC2kY8n.1


ባለፉት ሁለት ክፍሎች ተፈጥሮ የነበረውን Network መቆራረጥ ለመፍታት የምንችለውን ጥረት እናደርጋለን። ቸር ያገናኘን!
👍6431🙏8