+++"እንደ አባቶቻችን ከተመለስን ይምረናል"+++
ጥንት በአባቶቻችን ዘመን አስጨናቂ መከራ በተነሣ ጊዜ፣ ልመናን የሚያውቁ አባቶችና እናቶቻችን ራሳቸውን አዋርደው በፍጹም ንስሐ የፈጣሪያቸውን ምሕረት ደጅ ጠኑ። እርሱም ጩኸታቸውን ሰምቶ ዘንበል አለላቸው። መዓቱንም ከእነርሱ መልሶ በገጸ ምሕረቱ ጎበኛቸው። በቁጣው ቀን ተስፋ ያደረጉት ቸርነቱ አላሳፈራቸውም።
ዛሬስ? ዛሬም የእኛ ንስሐ እንደ አባቶቻችን እውነተኛ ከሆነ፣ በፈጣሪያችን ቸርነት ላይ ያለን መተማመን ከቀደሙት እናቶቻችን ካላነሰ፣ አምላካችን እኛን ይቅር ለማለት የታመነ ነው። መድኃኔዓለም መለወጥ እንደሚስማማው ደካማ የሰው ልጅ አይደለም። ልክ በፀሐይና በመሬት መካከል ባለ ዑደት (ዙረት) ምክንያት፣ አንዱ የመሬት ክፍል ከፀሐይ ብርሃን ተቀብሎ ሲያበራ በሌላኛው በኩል ያለው ደግሞ በግርዶሽ እንደሚጨልም እንዲሁ፣ የእግዚአብሔር ብርሃን (ቸርነት፣ ምሕረቱ) ለአንዱ አብርቶ ለሌላው የሚጋረድ አይደለም። ለብርሃኑ የተዘጋጀና በኃጢአት ጉድፍ ያልታወረ ዓይነ ልቡና እስካለን ድረስ የምሕረቱ ነጸብራቅ ለዘወትር በእኛ ላይ እንዳበራ ነው። ብቻ ንስሐችን እንደ ቀደሙት እናቶቻችን፣ መመለሳችንም በቃልና በተግባር እንደ ተመለሱት እውነተኞቹ አባቶቻችን ይሁን!።
"በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ"
ያዕ 1፥17
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg

የዋልያ መኖሪያ ከፍ ካለ ኮረብታ ላይ ነው። ታዲያ ይህ የበረሃ ፍየል ውኃን በተጠማ ጊዜ ምንጭ ያለው ከተራራው ግርጌ ስለሚሆን እርሱን ፍለጋ ወደታች ይወርዳል። ወርዶም ምንጩን ካገኘና ከጠጣ በኋላ፣ ወደ መጣበት ኮረብታ ሲመለስ ገና ከተራራው ወገብ ሳይደርስ አካሉ ይደክምና ውኃ ይጠማል። መልሶ ከምንጩ ወርዶ ይጠጣል። ወደ ተራራው ሲመለስ አሁንም ይጠማዋል። እንደ ገና ወደ ምንጩ ይመለሳል።(ስለ ዋልያ ውኃ መጠማት የሚሰጥ ሌላው ሐተታ እንደ ተጠበቀ ሆኖ)
ታዲያ ይህን ያየ ክቡር ዳዊት ዋልያ እንዲህ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፣ ነፍሴም ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ? ብሎ ዘመረ። (መዝ 41(42)፥1-2)
ይህም የቅዱስ ዳዊት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን ያወቀችና ፍቅሩን የቀመሰች፣ እርሱንም መዘከር የማትጠግብ ነፍስ ሁሉ የዘወትር መዝሙር ነው።
እኛስ የአምላካችንን ግሩም ፍቅሩን ቀምሰን እንደ ገና "ተጠማሁ" እያልን በመናፈቅ የምንዘምርበት ቀን መቼ ይሆን?
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
ታዲያ ይህን ያየ ክቡር ዳዊት ዋልያ እንዲህ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፣ ነፍሴም ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ? ብሎ ዘመረ። (መዝ 41(42)፥1-2)
ይህም የቅዱስ ዳዊት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን ያወቀችና ፍቅሩን የቀመሰች፣ እርሱንም መዘከር የማትጠግብ ነፍስ ሁሉ የዘወትር መዝሙር ነው።
እኛስ የአምላካችንን ግሩም ፍቅሩን ቀምሰን እንደ ገና "ተጠማሁ" እያልን በመናፈቅ የምንዘምርበት ቀን መቼ ይሆን?
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
የኃጢአተኞች ተስፋ የሆነው መድኃኒታችን በኢያሪኮ ገብቶ ሲያልፍ፣ የቀራጮች አለቃ ባለጠጋው ዘኬዎስ ሊያየው ወድዶ ነበር። ነገር ግን አልቻለም። ያለማየቱንም ምክንያት ጸሐፊው ቅዱስ ሉቃስ ሲነግረን "ቁመቱም አጭር ነበረና ስለ ሕዝቡ ብዛት አቃተው" ይለናል።(ሉቃ 19፥3) ዘኬዎስ ጌታን ማየት ያልቻለው በእርሱ የቁመት ማጠር ላይ የሕዝቡ ብዛት ተጨምሮበት ነው። ታዲያ ለዚህ ችግር ጥሩ መፍትሔ የሚሆነው "እስኪ ዘወር በሉ" እያለ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር መጣላት ሳይሆን፣ የራሱን ቁመት ማጠር የሚፈታበት ሌላ መንገድ መፈለግ ነው። ስለዚህም ከፊቱ ወዳለው የሾላ ዛፍ ሮጦ ወጣ። "ባለጠጋ ነኝ፤ በዚያ ላይ ትልቅ ሰው። ራሴን እንደ ትንሽ ልጅ እዚህ ዛፍ ላይ ሳንጠለጥል የሚያየኝስ ምን ይለኛል?" አላለም። ዘኬዎስ ስለ ክብሩና ስለ ሰው አስተያየት ቢጨነቅ ኖሮ "ሰው የሆነውን አምላክ" ማየትና በቤቱ ማስተናገድ ይቀርበት ነበር። ብዙዎቻችን እኛ ክርስቶስን ክርስቶስም እኛን ከሚያይበት የሾላ ዛፋችን "ንስሐ" የምንርቀው "ሰው ምን ይለኛል?" በሚል አጉል ጭንቀት ነው።
አሁን ዘኬዎስ ከሾላው ዛፍ ላይ ነው። የቁመቱን ማጠር ችግር ለመፍታት ባደረገው ጥረት ከአንድ ሰው ጋር ሳይጣላ ያለ ማንም ከልካይ የፈለገውን ክርስቶስ ለማየት በቃ። ጌታም ከበለሷ ተክል ፈልጎ ያጣውን ፍሬ አሁን ከሾላው ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ አገኘው።(ማቴ 21፥19) ይህም በሾላው ዛፍ ላይ የተገኘው ፍሬ "የዘኬዎስ ተነሳሒ ልብ" ነው።
አንዳንድ ጊዜ መንፈሳዊ ሕይወትህን፣ ዓላማህን እንዳታይ ከፊትህ ቆመው የሚጋርዱህ ውጫዊ ነገሮች ይኖራሉ። "ዘወር በሉልኝ!" እያልክ ከእነርሱ ጋር አትጋጭ። "ለምን ትከልሉኛላችሁ?!" በማለትም በብስጭት አታጉረምርም። እንደ ዘኬዎስ የራስህ ችግር ላይ አተኩር። የውጭውን ነገር ማማረር ትተህ እጥረትህን የሚቀርፍልህ የምትወጣበት ዛፍ ፈልግ። እዚያው ሆነህ ለመንጠራራት አትሞክር። ችግርህ ከመንጠራራት በላይ ነው። አትታክት፣ እስኪ መጋፋት ተውና መሬቱን ልቀቅ አድርግ። ያን ጊዜ ከማንም ሳትጣላ ከምትፈልገው እና ከናፈቅኸው ነገር ጋር ያለ ምንም ከልካይ በግልጽ ትተያያለህ። ብቻ የሕዝቡን ብዛት ትተህ የራስህ ማጠር ላይ አተኩር።

+++ የዘመኑ ፈተና... +++
የራስ ጸጉሩን በመጠኑ ለመስተካከል አንድ ሰው ወደ ጸጉር ቤት ያመራል፡፡ የጸጉር ውበት ባለሙያውም ያለመጠን ብቅ ብቅ ያሉ የጸጉር ዘለላዎቹን ከማረም ጋር ጥቂት ጨዋታ ቢጤ ይጀምራሉ፡፡
ጸጉር ቆራጭ- ወንድሜ በእግዚአብሔር መኖር ታምናለህን?
ተቆራጭ- እንዴታ?! ምን ጥርጥር አለው፡፡
ጸጉር ቆራጭ- እኔ ግን በእግዚአብሔር መኖር አላምንም፡፡ ያንተም እምነት ልክ እንደሆነ አላስብም፡፡ እስኪ አስተውል! ዓለምን እና በውስጧ የሚኖሩትን የፈጠረ በጎ ፣የፍጥረቱንም መጎዳት የማይሻ መልካም አምላክ ቢኖር ኖሮ ዓለም እንዲህ በጥፋት ባልታመሰች፡፡ አሁን ወደ ጎዳናው ብትወጣ አሳዳጊ አጥተው በደዌ ተይዘው በየሜዳው የተበተኑ ሕፃናትን፣ ጧሪ ያጡ አረጋውያንን ትመለከታለህ፡፡ ታዲያ ይህን ሁሉ ነገር እያየህ ፈጣሪ አለ ብለህ ታምናለህ?
በዚህ ጊዜ ጸጉሩን የሚስተካከለው ሰው በዝምታ ተዋጠ፡፡ የተነሡት ማስረጃዎች ሁሉ የማይካዱ የአደባባይ ሐቆች እንደሆኑ ሲያስብ መልስ አጥቶ ከራሱ ጋር ግብግብ ገጠመ፡፡ ፈጥኖ የእርሱን ሐሳብ መቀበልም አልፈለገም፡፡ የማይጨበጥ ምክንያት ይዞ በጉንጭ አልፋ ክርክር ሊሞግተውም አልወደደም፡፡ ብቻ የመረጠው ዝምታን ነበር፡፡ ዝም አለ!
እንዲህ ዝም እንዳለ ጸጉሩን ተስተካክሎ ጨርሶ ወጣ፡፡ የሚደንቀው ግን ወደ ወጣበት ጸጉር ቤት ድንገት ዘው ብሎ ገባ፡፡ ቀጥሎም ጸጉሩን ወዳስተካከለው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭ የለም!›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም በንግግሩ እየተገረመና በድንጋጤ እያየው ‹‹እንዴት? አንተ ራስህ የት ተቆርጠህ ነው እንዲህ የምትናገረው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ያም ደንበኛ ጸጉር ቆራጩን እጁን ይዞ ወደ ውጭ እያስወጣው፣ በጎዳናው ላይ የተንጨባረረ እና ያልጸዳ ጸጉር ወደ ነበረው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭማ የለም፡፡ ጸጉር ቆራጭ ቢኖር ኖሮ ይህ ምስኪን በተቆረጠ ነበር›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም እርማት ለመስጠት እየቸኮለ ‹‹ቆይ ቆይ ወንድሜ አትሳሳት፡፡ ጸጉር አስተካካይማ እኔ አለሁ፡፡ ይህ ሰው ጸጉሩ የተንጨባረረው እኔ ባለመኖሬ ሳይሆን እርሱ ወደ እኔ ስላልመጣ ነው›› እያለ መኖሩን ሊያሳምነው ሞከረ፡፡
ያም ጸጉር ተስተካካይ እንዲህ አለው ‹‹አዎ፤ የዚህ ሰው ጸጉር ያለ ልክ አድጎ የተንጨባረረውና አዳፋ የሆነው አንተ ባለሙያው ስለሌለህ ሳይሆን እርሱ ወደ አንተ ስላልመጣ ነው፡፡ ልክ እንደዚህ ደግሞ ዓለም ችግር ውስጥ የምትወድቀውና ክፉ ነገር የሚያጋጥማት ፍጹም በጎ የሆነ አምላክ ሰለሌለ ወይም የሚጠብቃት ቸር እረኛ ስላጣች ሳይሆን ዓለም ወደ ፈጣሪዋ ስላልመጣች፣ በንስሓም ወደ እርሱ ስላልቀረበች ነው።››
‹እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል›
2ኛ ዜና 15፡2
ወደ አምላካችን እንቅረብ!!!

ሥጋዊ ኃይልና ጉልበት በሕመም ይደክማል። ጽኑዕ ደዌ ብርቱ ክንድን ልምሾ ያደርጋል። የታጠከው የጉብዝና ኃይል በእድሜህ አመሻሽ ይፈታል። ደዌ የማያደክመው እድሜ የማያጠፋው ጉልበት "ኃይለ እግዚአብሔር" ነው። ብዙ ድንቅ ያደረጉና የዓለምን አስፈሪ ነገሮች የታገሉ ታላላቅ ቅዱሳንን ተመልከት። እንደ ቅዱስ ቂርቆስ ያሉ ሰውነታቸው ያልጸና ሕፃናትን፣ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በራስ ምታት፣ በጎን ውጋትና በቁስል የሚሰቃዩ የደዌ ሰዎችን፣ ከአናብስት ጋር እንደ ተፋለመው ቅዱስ አግናጥዮስ ያሉ አረጋውያንን ታያለህ። የተሻለ እንዳገለግል ይህ ደዌ ቢርቅልኝ፣ ጉልበቴ ቢመለስልኝ አትበል። የሰውነትህ ድካም በአንተ የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ኃይል ሊያስቆመው አይችልም። ዓለምን በወንጌል ያጠመቀው እና ከሁሉ ይልቅ የደከመው ሐዋርያ ታማሚው ጳውሎስ መሆኑን አትርሳ።
+++ "አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ" መዝ 18፥1 +++
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
+++ "አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ" መዝ 18፥1 +++
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
ልክ በእጅ ይዘውት እንደሚጠፋ ፋኖስ የሚወዱትን ሰው በክንድ እንደታቀፉ ሕይወቱ ስታልፍ እንደ ማየት፣ እስከዚያች ቅጽበት ድረስ በሕይወት እሳት ይሞቅ የነበረን የቅርብ ሰው ወዲያው በሞት ሲቀዘቅዝ አጠገቡ ሆኖ እንደ መመልከት እጅግ የሚያሳዝን ነገር የለም። ከንፈሮቹ ሲዘጉ፣ ድምጹ በዝምታ ሲዋጥ፣ በተለይም ደግሞ በምትቀዘቅዝ መሬት ጉያ ውስጥ ለማኖር "አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ" በሚለው ቃል ሲሸኙት የሚሰማን የውስጥ ሁከት በምን ይገልጹታል?!
ነገር ግን ክርስቲያን የእግዚአብሔር ልጅ መጥቶ ሞትን ድል ከነሣው በኋላ "ሞት እንቅልፍ እንደ ሆነ" ያምናል። ስለዚህም የሚወድደው ሰው ሲሞትበትና የመጨረሻዋን ስንብት ሲያደርግ፣ በፍጹም ፍቅርና መሳሳት የከደናቸው እነዚያ ዓይኖች ዳግመኛ ለማየት እንደሚገለጡ እርግጠኛ ነው። አሁን "ወንድሜ" ለሚለው ጩኸቱ የማይመልሰውና የተዘጋው ልሳኑ፣ አንድ ቀን ግን የሸኘው እርሱን ለመቀበል "እንኳን ደኅና መጣህ" ለማለት እንደሚፈታ በማመን ነው።
በኦሪት ከነበሩት አንዳንዶች የሚወዱትን ሰው ሞት በምስጋና ከተቀበሉ፣ በሐዲስ ኪዳን የምንኖር እኛማ እንዴት አብልጠን ልንበረታ ይገባን ይሆን?! ምክንያቱም አሁን ሞት ስሙ እንጂ ሥልጣኑ የለም። ሞት "እንቅልፍና መንገድ፣ ሽግግርና እረፍት፣ ሰላምና የጸጥታ ወደብ" ብቻ ሆኗል። የተኛን ሰው ስናይ መልሶ እንደሚነቃ ስለምናውቅ ውስጣችን በኃዘን አይረበሽም። ተስፋም አንቆርጥም። ከእኛ ወገን ስላንቀላፉትም አንዳንዶች ይህን እናስብ። ሞት ለክርስቲያኖች በሥጋ የሚያንቀላፉት ረጅም እንቅልፍ ነው።
"ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፥ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና"
መዝ 116፥7
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/U

"ነፍሳችን ከዚህ ዓለም ሕይወት በተለየች ጊዜ፣ ክስ የሚቀርብብን ተአምራት ስላላደረግን ወይም የነገረ መለኰት ሊቅ ስላልሆንን ወይም ደግሞ ራእያትን ስላላየን አይደለም። ነገር ግን ስለ ኃጢአታችን ሳናቋርጥ ባለ ማልቀሳችን ምክንያት በዚህ በእርግጠኝነት በእግዚአብሔር ፊት እንጠየቃለን።"
ሊቁ ዮሐንስ ዘሰዋስው
(John Climacus, Author of the Divine Ladder)
+++ፍጽምት በሆነች የንስሓ እንባ ጎርፍ እንደ በረሃ የደረቀች ነፍሳችንን በጽድቅ እናለምልም!!!+++
መልካም ሱባዔ!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
ሊቁ ዮሐንስ ዘሰዋስው
(John Climacus, Author of the Divine Ladder)
+++ፍጽምት በሆነች የንስሓ እንባ ጎርፍ እንደ በረሃ የደረቀች ነፍሳችንን በጽድቅ እናለምልም!!!+++
መልካም ሱባዔ!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://tttttt.me/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
የከበርሽ ጌታን የወለድሽ ሆይ፣ የማይታይ ቃልን የተሸከምሸው የብርሃን እናቱ አንቺ ነሽ እሱን ከወለደሽው በኋላ በድንግልና ኖረሻልና በፍጹም ምስጋና ያገኑሻል። ሰአሊ ለነ ቅድስት።
የማግሰኞ ውዳሴ ማርያም
የማግሰኞ ውዳሴ ማርያም
በዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ የሚለቀቁ ትምህርቶች እንዲደርስዎ #Subscribe #Like #Share #Comment ያድርጉ!
"በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጌታ ቃል እንዲሮጥ በእናንተም ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር... ስለ እኛ ጸልዩ"
2ኛ ተሰ 3፥1-2
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
"በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጌታ ቃል እንዲሮጥ በእናንተም ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር... ስለ እኛ ጸልዩ"
2ኛ ተሰ 3፥1-2
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
+++ "የምወደው ልጄ ይህ ነው" +++
ጌታችን ከሐዋርያቱ መካከል "አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ጴጥሮስ፣ ዮሐንስንም" ወደ ቅዱሱ የታቦር ተራራ ብቻቸውን ይዟቸው ወጣ።(ገላ 2፥9) ከተራራውም ጫፍ ሲደርሱ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የመምህራቸው ፊት እንደ ፀሐይ ሲያበራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሲሆን ተመለከቱ። እነሆም ከቀደሙት ጻድቃን ታላላቆቹ ሙሴና ኤልያስ በታቦር ተገኝተው ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።
እነዚህ የብሉይ ኪዳን ነቢያት የትንቢታቸው ፍጻሜ ከሆነው ክርስቶስ ጋር ምን ተነጋገሩ? መቼም በጊዜው ከጌታ ጋር ውለው ያድሩ እንደ ነበሩት ተማሪዎቹ ሐዋርያት "አትሙትብን" አይሉትም። በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ሱባኤ የያዙለትና ደጅ የጠኑት የድኅነት ተስፋ እናዳይፈጸም "ይቅር አትሙት" እንዴት ይላሉ? ስለዚህ ከብሔረ ሕያዋን የመጣው ኤልያስና ከብሔረ ሙታን የመጣው ሙሴ በአንድ ላይ "በኢየሩሳሌም ሊፈጸም ስላለው ስለ መውጣቱ (ስለ መከራው፣ ሞቱ)" ያነጋግሩት ነበር።(ሉቃ 9፥31)
በታቦር ተራራ ላይ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መልእክተኞች ተገናኙ። በባሕር ላይ በእግሩ የተራመደው ጴጥሮስ፣ የኤርትራን ባሕር እጁን ዘርግቶ የከፈለው ሙሴን አየው።(ማቴ 14፥29፣ ዘጸአ 14፥21) የሰማርያ ሰዎች በተቃወሙ ጊዜ "እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው" ያሉ ያዕቆብና ዮሐንስ፣ ከሰማይ እሳት አዝንሞ ሃምሳ አንዱን ወታደሮች ያስበላ ኤልያስን ተመለከቱት።(ሉቃ 9፥54፣ 2ኛ ነገ 1፥10)
ሁለቱ ምስክሮች እንደ ተሰወሩም ወዲያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ ሦስት ዳሶች እንሥራ ብሎ ጌታውን ጠየቀ። ሐዋርያው በዚህ ተራራ ላይ መቅረት የፈለገው ያለ ምክንያት አይደለም። መድኃኒታችን አስቀድሞ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ዘንድ ብዙ መከራ ይቀበልና ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲነግራቸው ቅዱስ ጴጥሮስ "አይሁንብህ፤ አይድረስብህ" ሲል ሊከላከለው ሞክሮ ነበር። ለዚህም በጊዜ "ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል" ተብሎ ተገስጾበታል።(ማር 9፥31-33) ይሁን እንጂ አሁንም ቅዱስ ጴጥሮስ ያለውን ሁሉ እድል ተጠቅሞ ጌታን ወደ ኢየሩሳሌም ከመሄድና በካህናት አለቆች እጅ ተላልፎ ከመሰጠት ማስቀረት ስለሚፈልግ "ጌታ ሆይ፦ በዚህ(በታቦር ተራራ) መሆን ለእኛ መልካም ነው" ብሎ ተናገረ።
እርሱም ይህን ገና ሲናገር ሳለ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው። ከደመናው "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ መጣ። ሐዋርያቱ ይህን ድምጽ የሰሙት ሙሴ እና ኤልያስ ከክርስቶስ ተለይተው ከሄዱ፣ እነርሱም ወድቀው ከነበሩበት ከተነሡ በኋላ ነው። ይህም ከደመናው ውስጥ ሲወጣ ስለ ሰሙት ቃል "ለማን የተነገረ ይሆን?" ብለው እንዳይጠይቁና ምስክርነቱ ለክርስቶስ ብቻ የተሰጠ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ እንዲረዱ ነው። በዚሁም ላይ ደመናው ወርዶ የጋረደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ሳይሆን ሐዋርያቱንም ጭምር ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ደመናው ጌታን ብቻ ጋርዶት ቢሆን ኖሮ፣ ሐዋርያቱ "እርሱን ስሙት" የሚለውን ቃል ራሱ ክርስቶስ ለራሱ የተናገረው ሊመስላቸው በቻለ ነበር።
ቅዱስ ጴጥሮስ "አትሙት" ያለው መምህሩን በፍጹም ልቡ ስለሚወደው መሆኑ አያጠራጥርም። ነገር ግን ጴጥሮስ ጌታን የቱንም ያህል ቢወደው፣ ፍቅሩ ግን ከወለደው ከባሕርይ አባቱ ከአብ አይደለም ሊበልጥ ሊነጻጸርም አይችልም። ታዲያ አብ በእርሱ ደስ የሚለው፣ የሚወደው፣ አንድያ ልጁ እንዲሞት ፈቃዱ ከሆነ፣ የአብን ያህል ሊወደው የማችለው አረጋዊው ጴጥሮስ ለምን "አትሙት" እያለ ይቃወማል?!
አብ ምትክ የሌለው ልጁ ወልድ ሰው ሆኖ በክፉዎች እጅ ሲንገላታ እና እስከ መስቀል ሞት ሲደርስ እያየ ዝም ያለው ስለማይወደው አይደለም። ዓለም ያለ ልጁ መከራና ሞት ስለማትድን ነው እንጂ። ከዚህ ምን እንማራለን? ዛሬም ወደ መከራ የምንገባ የጸጋ ልጆቹ የምንሆን እኛ ክርስቲያኖች "እግዚአብሔር እንዲህ ስሆን ዝም ያለኝ ስለማይወደኝ ነው" አንበል። ባገኘን ጥቂት የሥጋ መከራና ሕመም የሚበልጠውን የነፍስ ጤና የምንሸምት ከሆነ እግዚአብሔር ዝም ይላል። ዝም የሚለው መከራችንን ስለማያይ ሳይሆን ከመከራው ጀርባ ያለው ዓላማ ታላቅና የተቀደሰ እንደ ሆነ ስለሚያውቅ ነው።