+++ ‹‹እስክ ዛሬ ያላወቅነው›› +++
በዚህ ዓለም ካሉ ነገሮች ውስጥ በጣም የምታውቀው ማንን ነው? ተብለህ ብትጠየቅ መጀመሪያ ወደ አእምሮህ የሚመጣው መልስ ምንድን ነው? ‹‹ራሴን ነዋ!›› አትልም; ብዙ ሰው በጣም እርግጠኛ ሆኖ ከሚያውቃቸው ነገሮች ውስጥ የመጀመሪያው ራሱን እንደ ሆነ ሊያስብ ይችላል፡፡ በርግጥ ላንተ ከአንተ የተሻለ አንተን የሚቀርብ ሌላ አካል የለም፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ከራስህ ጋር ያለህ ቀረቤታ ራስህን ለማወቅህ ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም፡፡ ለዓይን ከቅድብ የቀረበ ምን አለ? ነገር ግን በመስታወት ካልታገዘ በቀር ዓይናችን አንድም ቀን ቅንድቡን አይቶት አያውቅም፡፡
በተለይ የኖርንበት ማኅበረሰብ እና ያደግንበት ባሕል ‹‹ራስን ስለ ማወቅ›› ያለው ግንዛቤ ትንሽ ያልጠራ ይመስላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው እድሜው ከፍ እያለ ሲመጣ ‹‹ዐዋቂ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ‹‹ዐዋቂ›› የሚለው ስያሜ ተምሮ በያዘው ዲግሪ፣ ዲፕሎማ፣ ወይም ባደረገው አንዳች ማኅበራዊ አስተዋጽዎ ምክንያት የተሰጠው አይደለም፡፡ ‹‹ራሱን የሚያውቅ›› ለማለት ነው፡፡ ሌላው ጠንከር ያለ ወቀሳና ምክር የደረሰበትም ሰው ከሚዘንብበት ትችት ለማምለጥ የሚጠቀምባት አመክንዮ ‹‹እኔ ልጅ አይደለሁም፤ ራሴን ዐውቃለሁ›› የምትል ነች፡፡ ወይ ራስን ማወቅ!
ራስን ማወቅ እንዲህ እንደምናስበው በቀላሉ የሚደረስበት ነገር አይደለም፡፡ ትክክለኛው ማንነታችንን ለማየት መጀመሪያ መውጣት የሚጠበቅብን አድካሚ የሆነ የትሕትና ዳገት አለ፡፡ ከእኛ ውጭ ያለን ሌላ ቁስ ለማየት የቻልነው እርሱ በቆመበት ቦታ ላይ ስላልቆምን ነው፡፡ ራሳችንንም መመልከት ከፈለግን መጀመሪያ እኛ የሌለንበትን ተቃራኒ አቅጣጫ ፈልገን ማግኘት አለብን፡፡ ይህ ራሳችንን ቆመን የምናይበት ትክክለኛው እና እኛ የሌለንበት ተቃራኒ አቅጣጫ ደግሞ ትሕትና ነው፡፡ እርሱ ላይ ስንቆም ራሳችንን እያየን መታዘብ ትጀምራለህ፡፡ ‹‹አሁን እንዲህ ማድረግ ትክክል ነው?›› እያልን ራሳችንን እንጠይቃለን፣ እንወቅሳለን፣ እናርማለን፡፡
ለሰው ራስን ማወቅ ምን ያህል እንደሚከብደው የምንረዳው በሌሎች ላይ ሲፈርድ ስናይ ነው፡፡ እንደ ግንድ ተሸክሞት ያጎበጠው ኃጢአቱን ትቶ የሌሎችን ስህተት ቀና ብሎ ሲመረምር፣ እንደ ግመል ገዝፎ በዓይኑ ፊት የቆመው የገዛ ድክመቱን ውጦ እንደ ትንኝ ያነሰውን የወንድሙን ጥፋት ሲያጠራ ማየት ‹‹ሰው ምን ያህል ራሱን ባያውቅ ነው?›› ያሰኛል፡፡ ጌታም በወንጌል ‹‹እናንተ እውሮች መሪዎች፤ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ›› ሲል የገሰጻቸው እንዲህ ዓይነቱን ጠባይ የተላበሱ ፈሪሳውያንን ነው፡፡(ማቴ 23፡24) በመጽሐፈ መነኮሳት እንደ ተጻፈ አንድ ወጣኒ መነኩሴ ወደ አረጋዊ አባት መጥቶ ‹‹ለምንድር ነው ሁል ጊዜ በሌሎች ላይ የምፈርደው?›› ሲል ቢጠይቃቸው፣ ‹‹እስከ ዛሬ ራስህን ስላላወቅህ ነው›› ብለው መልሰውለታል፡፡ ስለዚህ ራሱን እያጸደቀ የወንድሞቹን ስህተት ነቃሽ ለሆነ ኃጢአተኛ ሰው ፍቱን መድኃኒቱ ‹ራሱን ማወቁ› ነው፡፡
ሰዎች ራሳቸውን ሳያውቁ የሚቀሩት ስላልቻሉ ብቻ አይደለም፡፡ ራስን ማወቅ ስለማይፈልጉም ጭምር ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ‹ራስን ማወቅ› ይዞ የሚያመጣው ጊዜያዊ ሕመም ወይም ትንሽ ስቃይ አለ፡፡ ወደ ራሳችን መመልከት ስንጀምር የማንፈልገውን ‹‹እኛነት›› በውስጣችን ልናገኘው እንችላለን፡፡ በዚህም መረበሽ፣ መቆጨት፣ ኃፍረት ይሰማን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ስሜት ለማምለጥ ብለን ቅዠታዊ ዓለም ይሄድ ዘንድ ለራሳችን ልንፈቅድለት አይገባም፡፡ ለእኛ ከማንም በላይ ጠላት የሚሆንብን ይህ በውስጣችን የተደበቀውና ማወቅ የማንፈልገው ‹‹ስውር እኛነታችን›› ነው፡፡ ስለዚህም በጊዜ ራስን መርምሮ አፋጣኝ መልስ መስጠት ያስፈልጋል፡፡
ራስን ዐውቆ፣ ከራስ ጋር ተዋውቆ፣ ለንስሐ አባት ድክመትን አሳውቆ፣ የፈጣሪ ጸጋ እና ረድኤቱን እየጠየቁ በትሕትና ለመኖር ያብቃን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com

በዚህ ዓለም ያለውን ዝና ለማግኘት ምን ያህል ደከምህ? በሰዎች ፊትስ ከፍ ብለህ ለመታየት ስንት ጊዜ ራስህን ለአደጋ ጣልህ? የታዋቂነትህ ዋጋው ስንት ነው? ነገር ግን ይህን ሁሉ መሥዋዕትነት ከፍለህ የሰበሰብከው ዝና እና ክብር ተከትሎህ ወደ ሰማይ አይሄድም። ያለበሱህ የክብር ካባ፣ በራስህ ያኖሩልህ የስኬት አክሊል እዚሁ እንዳገኘሃቸው እዚሁ ጥለሃቸው ትሄዳለህ። ጻድቁ ኢዮብ እንደ ተናገረው ከእናትህ ማኅፀን ራቁትህን እንደ ወጣህ፣ እንዲሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።(ኢዮ 1፥21) ታዲያ እርቃኑን ያለ ንጉሥ ከተራው ሕዝብ፣ እርቃኑን ያለ ባለጠጋ ከደሃው፣ እርቃኑን ያለ ክቡር ከተናቀው በምን ይለያል?!
"በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን" ኤፌ 2፥6-7
እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን!
እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን!
በገነተ አበው (Paradise of the fathers) እንደ ተጻፈ፣ አንድ መነኩሴ ታርዞ በብርድ ይሰቃይ ለነበረ ምስኪን የለበሰውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ አውልቆ ሰጠው። ከጥቂት ጊዜ በኋላም በገዳም ሆኖ የሰፋቸውን ሰሌኖች ለመሸጥና የእለት ምግቡን ገዝቶ ለመመለስ ወደ ገበያ ሲወጣ፣ በመንገድ ዳር የቆመች አንዲት ዘማ ያን ለምስኪኑ ሰው የሰጠውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ ለብሳው ያያታል። ባየው ነገር የተደናገጠው መነኩሴ "የምድር መላእክት የሚለብሱትን ይህን የክብር ልብስ በከንቱ ቦታ እንዲውል አደረግኹት" እያለ ማልቀስና መቆጨት ጀመረ። ሲያዝንም ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ "አይዞህ አትዘን፤ መጎናጸፊያህን ለዚያ ምስኪን በሰጠህበት ቅጽበት ከእጅህ ተቀብሎ የለበሰው ክርስቶስ ነው። ከዚያ በኋላ ለሆነው ሁሉ አንተ ተጠያቂ አይደለህም" ሲል አጽናናው።
ተርቦ እና ተቸግሮ ለምታገኘው ምስኪን ያለ ምንም መመራመር ከእጅህ ያለውን ስጠው። እርሱ በሰጠኸው ገንዘብ ረሃቡን ከማስታገስ ይልቅ ሌላ አጉል ነገር ሊያደርግበት ይችላል። እርሱ ግን የአንተ ድርሻ አይደለም። አንተን የሚያስጠይቅህ ተመጽዋቹ ከምጽዋቱ በኋላ የገባበት ስካር ሳይሆን፣ አንተ ሳትመጸውተው በፊት የነበረበት ረሃብ ነው።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
ተርቦ እና ተቸግሮ ለምታገኘው ምስኪን ያለ ምንም መመራመር ከእጅህ ያለውን ስጠው። እርሱ በሰጠኸው ገንዘብ ረሃቡን ከማስታገስ ይልቅ ሌላ አጉል ነገር ሊያደርግበት ይችላል። እርሱ ግን የአንተ ድርሻ አይደለም። አንተን የሚያስጠይቅህ ተመጽዋቹ ከምጽዋቱ በኋላ የገባበት ስካር ሳይሆን፣ አንተ ሳትመጸውተው በፊት የነበረበት ረሃብ ነው።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
+++ "እመቤታችን ከጌታ ዕርገት በኋላ" +++
መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቅዱስ መስቀሉ ላይ ባፈሰሰው ክቡር ደሙ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን ለሐዋርያቱ አደራ ሰጥቷል፡፡ በመጀመሪያው ምዕት ዓመት በነበረው የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የጌታ እናቱ እመቤታችን የነበራት ድርሻ ትልቅ ነበር፡፡ ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ እመቤታችን በሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት ሳለች፣ የሐዲስ ኪዳኗ ቤተ ክርስቲያን ራስ እና ፈጻሚ የሆነው ክርስቶስ የተገኘባትን እርሷን ለማየት ከሁሉም የዓለም ክፍላት የሚመጡ ሰዎች ብዙ ነበሩ፡፡ ድንግልም ወደ እርሷ የመጡትን ሁሉ እየባረከች፣ ያዘኑትንም እያጽናናች፣ በንስሓ ሕይወት እንዲኖሩ በመምከር ተስፋና ደስታን እየሞላች ትሸኛቸው ነበር፡፡ በርግጥም እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በምድር ላይ ለመገለጡ፣ እንደ ሕፃናት ጥቂት በጥቂት ለማደጉና በመጨረሻም ለፈጸመው የቤዛነት ሥራው ሁሉ እናቱና አገልጋዩ ከምትሆን ከእመቤታችን የበለጠ ምስክር ከየት ሊመጣ? እርሷን ለማየት ባይጓጉ ነበር የሚደንቀን፡፡
ከሰባ ሁለቱ አርድዕት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሉቃስም ወንጌሉን ሲጽፍ በሕይወቷ ውስጥ የተፈጸሙ እርሷ ብቻ የምታውቃቸውንና ብቻዋን ሆና የሰማቻቸውን እንደ ብሥራት ያሉ ታሪኮችን በመንገር እረድታዋለች፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ በቃልም በመጽሐፍም አይሁድን ተከራክሮ ድል ባደረጋቸው ጊዜ፣ ተቆጥተው ድንጋይ ሲያነሡበትና ሲከቡት ከሩቅ በማየቷ የሰማዕትነት ሥራውን በጽናት ይፈጽም ዘንድ በጸሎቷ እንዳበረታችው በጥንታውያን የታሪክ መዛግብት ሰፍሮ እናገኛለን፡፡
እመቤታችንን የማየት ዕድል ካገኙት አንዱ የሆነው ቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘአርዮስፋጎስ እርሷን ባየ ጊዜ ሐዋርያቱ ሰው መሆኗን ባይነግሩት ኖሮ አምላክ መስላው እንደ ነበር ጽፏል፡፡ የፊቷን ደም ግባትና ሰላም፣ በእርሷም ላይ ይንጸባረቅ የነበረውን የቅድስና ብርሃን አይቶ በልጇ የማያምን እንደ ሌለም መስክሯል፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙርና የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ አግናጥዮስም ለመምህሩ (ቅዱስ ዮሐንስ) በላከለት መልእክት፣ ክርስቲያኖች በሚሳደዱበት በዚያ ዘመን የእግዚአብሔር እናቱ እመቤታችን በስደቱ ደስተኛ እንደ ሆነች፣ በመከራዎችም ውስጥ ሆና እንደማታጉረመርምና እርሷንም ይነቅፉ በነበሩ ሰዎች እንዳልተቆጣች ይናገራል፡፡
እመቤታችን በልጇ ሕይወት ውስጥ ወሳኝ ታሪኮች የተፈጸሙባቸውን ስፍራዎች መጎብኘት ትወድ ነበር፡፡ የልደቱን ነገር፣ የእረኞችና የመላክቱን ዝማሬ፣ የጥበበኞቹን ስጦታ አስባ ቤተልሔም ትሄዳለች፡፡ ከሁሉም በላይ ግን መከራ ወደ ተቀበለበት ስፍራ መሄድ ታዘወትራለች፡፡ በዚያም የተቀበላቸውን ሕማማት፣ የደረሰበትን ተዋርዶ እና መከዳቱን እያሰበች ታነባለች፡፡ ‹ይህ ልጄ የተገረፈበት፣ ይህ የእሾህ አክሊል የተቀዳጀበት፣ ይህ ደግሞ መስቀል ተሸክሞ የሄደበት፣ ይህ የተሰቀለበት ነው› ትላለች፡፡ ወደ መቃብሩ ስፍራ ስትመጣ ግን በልዩ ደስታ እየተሞላች ‹‹ይህ በሦስተኛው ቀን ከሞት የተነሣበት ቦታ ነው›› ትል ነበር፡፡
በተሰጣት ቃል ኪዳን እኛ ኃጥአን የሆንን ልጆቿን ታስምረን!

+++ "የእግዚአብሔር ዝምታ" +++
እግዚአብሔር ፍጥረታትን ከፈጠረባቸው መንገዶች አንዱ ‹በአርምሞ› ወይም ‹በዝምታ› ነው፡፡ ዝምታ የመናገር ተቃራኒ ወይም ያለ መሥራት ውጤት ነው፡፡ ሰው ዝም አለ የሚባለው ባልተናገረ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሥራ መሥራት ባቆመም ጊዜ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሶምሶምን ነፍስ ይፈልጉ የነበሩ የጋዛ ሰዎች ሶምሶም ወደ ጋዛ መምጣቱንና ወደ አንዲት ጋለሞታ ቤት መግባቱን ባወቁ ጊዜ፣ እርሱ ያለበትን ሥፍራ ከበው ማለዳ ላይ እንገድለዋለን በማለት ሌሊቱን ሙሉ አንዳች ክፋት እንዳላደረጉበት ሲናገር ‹ማለዳ እንገድለዋለን ብለው ሌሊቱን ሁሉ በዝምታ ተቀመጡ› ይላል፡፡ በሌላም ሥፍራ ኃጢአተኞች ጽድቅን በመሥራት ኃጢአትን እንደማይቃወሟት ለመናገር ‹እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል፡፡ ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ› ሲል እናነባለን፡፡(መሳ 16፥2 ፣1ኛ ሳሙ 2፥9)
ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ‹በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ አስቡ፤ ዝም በሉ› ብሎ እንደዘመረው የሰው ልጅ ዝም ባለ ጊዜ በአእምሮው ከማሰብ በቀር ምንም ዓይነት የሚያከናውነው ሥራ የለም፡፡ ምክንያቱም ማሰቡ ብቻ ተግባር ስለማይሆንለት ያሰበውን ለማሳካት የግድ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ወይም መሥራት አለበት፡፡ የእግዚአብሔር ዝምታ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ እግዚአብሔር ዝም ባለ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የሥራ እፎይታ የለም፡፡
ዝምታ ለእግዚአብሔር ሲሆን ኃይሉን የሚገልጥባት የሥራ ወቅት ትሆናለች፡፡ በእግዚአብሔርም ዝምታ ውስጥ ያለች አሳብ ፍጥረታትን የማስገኘት አምላካዊ ኃይል አላት፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ‹አሰበ› ተብሎ ሲነገር እንደ ፍጥረታት አሳብ ታስቦ ብቻ የሚቀር ሥራ መሥራት የማይችል ዝርው አድርገን እንዳንረዳ፡፡ የእርሱ አሳብ ኃይል አለው፡፡ በአሰበ እና በፈቀደ ጊዜ ሁሉን ካለመኖር ወደ መኖር የሚያመጣ ሥራን የሚሠራ ልዩ አሳብ ነው፡፡

"የዓለም ብርሃን የሆነ እርሱ እንዴት ራሱን ሊሰውር ይችላል? ፀሐይ ብታበራ እና በሁሉም ቦታ ብትገኝ እንኳን፣ የሰው ልጅ በዓለም ላይ ሊያደርገው ከሚችለው በጣም ቀላል ነገር ውስጥ አንዱ የፀሐይዋን ብርሃን ማጥፋትና ጨለማን መፍጠር ነው። ይህም እንዲሆን ዓይኑን መጨፈን በቂ ነው። ከዚያም ራሱን በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ያገኘዋል። እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር ነው። ፈጣሪው በዙሪያው እንዳይኖር የሚፈልገው ግን ሰው ነው!"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
+++‹‹አርሳንዮስን አትረብሹት!››+++
ሥጋዊ ዓይኑን ያጣ ሰው የፀሐይን መልክ ተናገር ቢሉት እንዴት ይቻለዋል? በሙቀቷ ብቻ የፀሐይን ውበት መግለጽስ እንዴት ይሆንለታል? በጎ ትሩፋት ሠርተን ከቅድስና ጣዕም ላልደረስን ሰዎች አሁን የምንናገረው ነገር ርቆ እንደ ተሰቀለ ፍሬ ነው፡፡ የልቡናን ዓይን በንስሓ እንባ አጥበው ካላጠሩ የማያዩት፣ በተጋድሎ ካላደጉ በጸጋም ካልጎለመሱ የማይደርሱበት ጣፋጭ ፍሬ፡፡ የእኛ የኃጥአን ዓይኖች ትንኝና ጥቃቅን ተሕዋስያን ሳይቀሩ ከሚመለከቱት ከዚህ ግዙፍ ዓለም የተለየ ምን ነገር አዩ? ጆሮዎቻችንስ አዕዋፍ እና አንስርት ከሚሰሙት ድምጽ በተለየ ምን ዓይነት ድምጽ ሰሙ?
ከሰው ተለይተው ወደ በረሃ በመሰደድ በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን ጥለው የሚያገለግሉ ባሕታውያን ከሚሰጣቸው አምላካዊ ጸጋዎች መካከል አንዱ ተመስጦ ነው፡፡ ሕሊናቸው የጌታዋን መልክ በማየት እና ሌሎች ረቂቅ መንፈሳዊ ቁም ነገሮችን በማሰላሰል ከፍ ብላ ትበርራለች፡፡ ነፍሳቸው ሰማየ ሰማያት ተነጥቃ ጥልቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን የጥበቡን ምሥጢር ታደንቃለች፡፡ በዚህ ዓለም ያለውን አኗኗርም ትዘነጋለች፡፡ ሥጋዊ መብል መጠጥን ትታ የጨለማ ወሬ ወደ ሌለበት የብርሃን አዳረሽ ትገባለች፡፡ በዚያም ተመስጦ ብዙ ቀን ትኖራለች፡፡ ከብዙ ቀንም በኋላ ስትመለስ ማደሪያዋ ሥጋ ደሙ ሳይደርቅና ሳይበሰብስ ያገኘችው እንደ ሆነ ትዋሐደዋለች፡፡ ነገር ግን ደርቆ ከአገኘችው በዚያው ትቀራለች፡፡
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሥራ መሐል ተመስጦ ሲመጣባቸው ሥጋቸው ይዝላል፣ ኃይል አጥተው ይዳከማሉ፡፡ በዜና አበው እንደ ተጻፈ ከዚህ ጸጋ የደረሰ አንድ ባሕታዊ ፈጣሪውን በሕሊናው እየተዘከረ ሥራውን ሲሠራ ድንገት ተደሞ መጣበትና ሰውነቱ ዝሎ ወደቀ፡፡ ሥራውንም መሥራት ተሳነው፡፡ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾለት ‹‹ለሥራው የሚሆን ሥጋዊ ኃይል አንሶህ ቢሆን አተጋህ ነበር፡፡ ይህ ግን የብቃት ነውና ግፋበት›› እያለ አበርትቶታል፡፡
ታላቁ አባት ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርም አንድ ሰው ወደ በዓቱ መጥቶ የሰፋውን እንቅብ እንዲሸጥለት ይጠይቀዋል፡፡ ቅዱሱም እንቅቡን ሊሰጠው ወደ በዓቱ ከገባ በኋላ በሕሊናው የሰማዩን ነገር እያሰበ ከፈጣሪው ጋር በተመስጦ ሲነጋገር እንቅቡን ረሳው፡፡ ከበዓቱ ደጃፍ የቆመውም ሰው እንደ ገና እጁን አጨብጭቦ ቢጠራው፣ ቅዱስ ዮሐንስ ባዶ እጁን በመውጣት ‹ምን ፈልገህ ነው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ያም ሰው ‹አሁን እንቅብ ልትሰጠኝ እኮ ገብተህ ነበር ለምን ባዶ እጅህን ተመለስክ?› አለው፡፡ ቅዱሱም ‹አዎን! አዎን!› ብሎ መልሶ ወደ በዓቱ ገባ፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም እንቅቡን ረስቶ በተመስጦ ከፈጣሪው ጋር መነጋገር ቀጠለ፡፡ ከውጭ የቆመውም ሰው ለሦስተኛ ጊዜ አጨብጭቦ ቢጠራው፣ ቅዱስ ዮሐንስ ወጥቶ ‹ምን ነበር የፈለግኸው;› በማለት ደግሞ ጠየቀው፡፡ ገዢውም እንቅብ ነበር የጠየኩህ ሲለው፣ ቅዱሱ ‹እንቅብ፣ እንቅብ፣ እንቅብ› እያለ ወደ በዓቱ ተመልሷል፡፡ በዚህም ምክንያት ከወጣንያን (ጀማሪ) መነኮሳት በቀር ሕሊናቸው በአንክሮ የሚያዝባቸው ፍጹማን መነኮሳት ምንም ዓይነት ተግባረ ዕድ እንዳይሠሩ በገዳም ታዟል፡፡
በተለይ ዕረፍትና ጸጥታ ያለበትን የብቸኝነት ሕይወት የመረጡ አበው ይህን የጽሙና ጊዜያቸውን ማንም እንዲሻማባቸው አይፈልጉም፡፡ በንግግርና በጨዋታ ምክንያት ሕሊናቸው መንፈሳዊውን ነገር ከማሰብ እንዳያቋርጥ ስለሚፈሩ፣ ወደ በዓታቸው ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ የሚያቀርቡት ጥያቄ አንድ ነበር፣ እርሱም ‹ሂዱልን!› የሚል ነው፡፡ በዚህ መንገድ ሰዎችን ከበዓታቸው ደጅ ይመልሱ ከነበሩት ቅዱሳን ውስጥ አባ አርሳንዮስና አባ ጴሜን ይጠቀሳሉ፡፡ የፍጹማን መነኮሳትና ባሕታውያን አኗኗራቸው እንዲህ ነው፡፡ ፈቃዳቸው ብዙ ከሆኑ የሰው ልጆች እየሸሹ፣ የእግዚአብሔርን አንዲት ፈቃድ ሌሊትና ቀን በልባቸው በማሰብ ይኖራሉ፡፡ ብቻቸውን ሲሆኑ አይታወኩም፡፡ ሰላማቸውም እንደ ወንዝ ውኃ ይፈስሳል፡፡
እኛ በዓለም ያለን ሰዎች ግን ይህን ተረድተን ዕረፍት አንሰጣቸውም፡፡ የላመ የጣመ ምግብ ይዘን በዓታቸው ድረስ እንሄዳለን፡፡ የዓለሙን ርኩሰትና እርባና ቢስ ወሬዎች እየነገርን የጠራ ሕሊናቸውን እናደፈርሳለን፡፡ ፋታ ሳይሰጥ ለሚፈትናቸው ሰይጣን ጦር አቀባይ እንሆንባቸዋለን፡፡ ብንችል ‹ጸሎት ያደርጉልኛል› በሚል ሰበብ ከበዓታቸው አፍልሰን በከተማ ሰርቢሶቻችን እናስቀምጣቸዋለን፡፡ ያም ባይሆንልን ‹የበቁ አባት በዚህ ቦታ አሉ!›፣ ‹እኚህ አባት አያሳዝኑም!› እያልን ምስላቸውን በየሶሻል ሚዲያው በመለጠፍ ወደ ሸሹት ዓለም በዲጅታል በር ልንመልሳቸው እንሞክራለን፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላም ራሳችን በዘረጋነው ወጥመድ ተጠልፈው ሲወድቁ ደግሞ ገመናቸውን ለመዘገብና ‹አቤት መነኩሴ!› እያሉ የሐሜት ነጋሪት ለመጎሰም ግምባር ቀደሞቹም እኛው ነን፡፡ ለምን በበዓታቸው እንዲመሰጡ አንተዋቸውም?! ለእኛም የሚጠቅሙን እኛን ትተው ከፈጣሪ ጋር ሲሆኑ ነው፡፡ ግድ የለም እስኪ እነርሱን መርጠው ለተሰደዱለት እግዚአብሔር እንተዋቸው?!
በአንድ ወቅት በበረሃ ያሉ አበውን እየዞሩ መጠየቅ ልማድ ያደረጉ ወንድሞች ወደ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ መጥተው ምክረን ሲሉ ጠየቁት፡፡ ቅዱስ ቴዎፍሎስም ለእነዚህ ወንድሞች የሰጣቸው ምክር በጣም የሚያስደንቅ ነበር፡፡ ምን አላቸው? ‹‹አርሳንዮስን አትረብሹት!››፡፡ እውነት ነው፤ እኔም ‹‹አርሳንዮሳውያንን አንረብሻቸው›› ብዬ ጽሑፌን አበቃሁ!

በእኛ ላይ ሊደርሱ ካሉ ክፉ አደጋዎች የዳንባቸውን ጊዜያቶች እስኪ እናስተውል። ከእነዚያ አስከፊ ሁኔታዎች ተአምር በሚመስል መንገድ የተረፍንባቸውንና ‹ለጥቂት እኮ ነው…› እያልን የምናስታውሳቸውን ሰዓታት እስኪ ለአፍታ ደግመን እናስባቸው። በእነዚያ የጭንቅ ጊዜያቶች ሁሉ የታደገንን የጠባቂ መልአካችንን የተዘረጋች ክንድ እናያለን፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙር የነበረው ቅዱስ ፖሊካርፐስ በጠባቂ መልአኩ አማካኝነት እንዴት ከሞት በተአምር ሊተርፍ እንደ ቻለ ይናገራል፡፡ ቅዱሱ አብሮት በአገልግሎት ከሚረዳው ዲያቆን ጋር በጉዞ ሳሉ ቀኑ ስለመሸባቸው መንገድ ዳር ካለ አንድ ትንሽ ቤት ገብተው ይተኛሉ፡፡ በእኩለ ሌሊትም የፖሊካርፐስ ጠባቂ መልአክ በሕልሙ ተገልጦ ‹ፖሊካርፐስ ሆይ ሊፈርስ ነውና ፈጥነህ ይህንን ቤት ለቅቀህ ውጣ› እያለ ሶስት ጊዜ አስጠነቀቀው፡፡ ፖሊካርፐስ ራእዩን እንዳየ ያንን ቤት ለቆ በፍጥነት ወጣ፡፡ ወዲያውም ቤቱን እያየው በፊቱ ፈራርሶ ወደቀ፡፡ እርሱም ሊመጣበት ከነበረው ሞት በጠባቂ መልአኩ አማካኝነት ዳነ፡፡
ከታናሽነቴ ጀምሮ እኔን የመገበኝ፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው!
መልካም በዓል ይሁንልን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
ከታናሽነቴ ጀምሮ እኔን የመገበኝ፣ ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው!
መልካም በዓል ይሁንልን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
በትሕትናው ልዕልናን ላገኘ፣ ለፍጥረታት ባለው ርኅራኄ የአምላክ እናትን ለሚመስል፣ የተቸገሩትን ፈጥኖ መርዳት ልማዱ ላደረገው፣ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ፣ ደግ እና ሰውን ወዳጅ ለሆነው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን።
ቅዱሳን መላእክት በአንድ ኃጢአተኛ ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚደሰቱትን ያህል፣ ባልተመለሰው ኃጢአተኛ ደግሞ እንዲሁ ያዝናሉ። በአንዱ ኃጢአተኛ መመለስ የተሰማቸውን ደስታ ፈጣሪያቸውን በማመስገን እንደሚገልጹ፣ ባልተመለሰው ኃጥእ የተሰማቸውን ኃዘን ደግሞ አምላካቸውን "ማረው፣ ይቅር በለው" ብለው በመለመን ያሳያሉ። (ያዕ 5፥13) ቅዱስ ሚካኤል አሁን እንዴት እንደ ሆንን አይቶ ይዘንልን፣ አዝኖም ይለምንልን፣ ለምኖም ያስምረን!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
ቅዱሳን መላእክት በአንድ ኃጢአተኛ ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚደሰቱትን ያህል፣ ባልተመለሰው ኃጢአተኛ ደግሞ እንዲሁ ያዝናሉ። በአንዱ ኃጢአተኛ መመለስ የተሰማቸውን ደስታ ፈጣሪያቸውን በማመስገን እንደሚገልጹ፣ ባልተመለሰው ኃጥእ የተሰማቸውን ኃዘን ደግሞ አምላካቸውን "ማረው፣ ይቅር በለው" ብለው በመለመን ያሳያሉ። (ያዕ 5፥13) ቅዱስ ሚካኤል አሁን እንዴት እንደ ሆንን አይቶ ይዘንልን፣ አዝኖም ይለምንልን፣ ለምኖም ያስምረን!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
+++"እውነትም የመከር በዓል"+++
ጌታችን ከትንሣኤው በኋላ በጋራም በተናጠልም ለሐዋርያቱ እየታያቸው የትንሣኤውን አማናዊነትና ‹ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገር እየነገራቸው› አርባ ቀን ቆይቷል፡፡(ሐዋ 1:3) በአርባኛውም ቀን ሲያርግ ‹የሚያጸና፣ የሚያነጻ እና የሚያጽናና መንፈስ ቅዱስን› እንደሚልክላቸው ተስፋን ሰጣቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ኃይልን እስከሚቀበሉባት ቀን ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲቆዩ አዘዛቸው፡፡ (ሉቃ 24፡49-51) ሐዋርያቱም ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ በጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) ውስጥ በአንድ ልብ ሆነው የጌታን እናት እንደ ታቦት ከብበው በጸሎት ይተጉ ጀመር፡፡(ሐዋ 2፥14)
ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት ቀን ማለት አይሁድ በዓመት ውስጥ ከሚያከብሯቸው ታላላቅ በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን ‹በዓለ ሃምሳ› የሚውልበት ዕለት ነበር፡፡ ይህም በዓል አይሁድ ፋሲካቸውን ካከበሩ ከሰባት ሳምንታት በኋላ ባለው ሰንበት ማግስት (በእሁድ፣ በ50ኛው ቀን) ስለሚከበር ‹‹ጰንጠቆስጤ››/‹‹በዓለ ሃምሳ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዚህም ቀን እስራኤላውያን አርሰው ካመረቱት ላይ አዲሱን የእህል ቁርባን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡበትም ዕለት ስለሆነ በሌላ ስያሜ ‹የመከር በዓል› ተብሎ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም የእስራኤል መስፍን የነበረው ሊቀ ነቢያት ሙሴ በሲና ተራራ ከአምላኩ ዘንድ ሕገ ኦሪት መቀበሉንም የሚያስቡበት ቀን ነው፡፡
በተለያዩ የዓለም ክፍላት የሚኖሩ አይሁድ ከያሉበት አገር ተጉዘው በመምጣት የፋሲካንና የመቅደስ መታደስ በዓላትን በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ለማክበር ይቸገሩ ነበር፡፡ የችግሩም ምክንያት እነዚህ በዓላት በሚውሉበት ወቅት ያለው የአየር ጠባይ በጣም አስቸጋሪና ነፋሱም ማዕበል የሚቀሰቅስ በመሆኑ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚሁ ጊዜ ወደ ኢጣልያ ለመሄድ በመርከብ በተሳፈረ ጊዜ ስላጋጠመው እንግልትና ስቃይ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፏል፡፡(ሐዋ 27፡9) እርሱ ራሱም በመንገዱ መካከል አብረውት ይጓዙ የነበሩትን ሰዎች ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ ይህ ጉዞ በጥፋትና በብዙ ጉዳት እንዲሆን አያለሁ፤ ጥፋቱም በገዛ ሕይወታችን ነው እንጂ በጭነቱና በመርከቡ ብቻ አይደለም›› ሲል ጉዞውን ለጥቂት ጊዜ እንዲያዘገዩት መክሯቸው ነበር፡፡ በዓለ ሃምሳ ግን የመጀመሪያዎቹ የፀደይና የመከር ወቅት ላይ ስለሚውል የአየሩ ሁኔታ ለመርከብ ጉዞ የተመቸ ነው፡፡ ስለዚህም የፋሲካና የመቅደስ መታደስ በዓላት ላይ በኢየሩሳሌም መገኘት ያልቻሉ አይሁድ ሁሉ በጉጉት የሚጠባበቁትና ወደ ቅድስቲቱ ከተማ በመግባት ተሰብስበው የሚያከብሩት ታላቅ በዓል ነው፡፡
"በዓለ ሃምሳ" የሚለው መጠሪያ አስቀድመን እንደ ተናገርነው በኦሪቱ ለሚከበረው በዓል መታወቂያነት የሚያገለግል ስያሜ ቢሆንም፣ የጌታ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በሃምሳኛው ቀን በመሆኑ ለሐዲስ ኪዳኑም ታላቅ በዓል መጠሪያነት ቢውል የሚያውክ አይሆንም፡፡ ይሁን እንጂ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ቀን ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ስትል ለሐዋርያት በወረደው ቅዱስ መንፈስ ልዩ ስም ትጠራዋለች፡፡ ‹‹ጰራቅሊጦስ›› የሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን ‹‹መጽንዒ፣ መንጽሒ››/‹‹የሚያጸና፣ የሚያነጻ›› የሚል ትርጉም አለው፡፡
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመስና ሐዋርያቱ በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሲጸልዩ ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ፣ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው፡፡(ሐዋ 2፡2) በዚህ ክፍል ይህን ታሪክ የሚጽፍልን ቅዱስ ሉቃስ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ‹ድንገት› እንደ ሆነ ይነግረናል፡፡ ለመሆኑ ‹ድንገት› ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ጸሐፊው ቅዱስ ሉቃስ ‹ድንገት› የሚለውን ቃል የተጠቀመው ነገሩ በሰው ፍላጎት ሳይሆን ‹በእግዚአብሔር ጊዜ› የተፈጸመ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ሐዋርያት አጽናኙ መንፈስ እንደሚላክላቸው ቢነገራቸውም በየትኛው ቀን ግን እንደሚወርድ የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህም ‹ድንገት› የሚለው ቃል ሐዋርያቱ ቀኑን ፈጽመው አለማወቃቸውን ያሳያል፡፡ ሁል ጊዜ ጸጋን የሚሰጠው እግዚአብሔር ስለሆነ የሚሰጥበት ቀነ ቀጠሮ በሰጪው እንጂ በተቀባዩ አይወሰንም፡፡ ስለዚህ የተቀባዩ ሰው ድርሻ ሳይዝል ተስፋም ሳይቆርጥ የአምላኩን የሥራ ቀን በትዕግሥት መጠባበቅ ነው፡፡
የዓውሎ ነፋሱም ድምፅ ልክ ኤልያስ የምድሩን መናወጥና እሳቱን ሲመለከት በመጎናጸፊያው ተሸፍኖ ከዋሻው በመውጣት እግዚአብሔርን ለማናገር ራሱን እንዳዘጋጀ፣ ሐዋርያቱም የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲያስተውሉና ለዚያም ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የተሰማ የማንቂያ ድምፅ ነው፡፡(1ኛ ነገ 19፡12) በተጨማሪም ድምፅ ‹ኃይልን› ያመለክታል፡፡ ስለዚህ እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ የተሰማው ድምጽ ሐዋርያቱ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል መቀበላቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ እዚህ ላይ ጌታችን በዮርዳኖስ ወንዝ ከተጠመቀ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በእርሱ ላይ ሲያርፍ ያሰማው አንዳች ድምፅ አለመኖሩን ይሏል፡፡(ማቴ 3፡16) ይህም እርሱ ለደካሞች ጽንዕ የሚሆን እንጂ እንደ ፍጡር ኃይል የሚቀበል አለመሆኑን እንደሚያመለክት ነው፡፡
አስቀድሞ መድኃኒታችን ለኒቆዲሞስ ‹‹ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል›› ሲል እንዳስተማረው፣ በዚህች ቀን በነፋስ የተመሰለ መንፈስ ቅዱስ በወደዳቸው በሐዋርያት ሰውነት ያድር ዘንድ ወደ ጽርሐ ጽዮን ነፈሰ(መጣ፣ ወረደ)፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ መንፈስ ቅዱስን ከነፋሳትም መርጦ ከደቡብ አቅጣጫ በሚነፍሰው ነፋስ ይመስለዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ከሰሜኑ የሚነሣው ነፋስ ቀዝቃዛና ሰብል የሚያጠፋ በመሆኑ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ገበሬዎች ይፈሩታል፡፡ ከደቡብ አቅጣጫ የሚነፍሰው ነፋስ ግን ከምድር ወገብ የሚወጣውን ሞቃታማ አየር ይዞ ስለሚነፍስ የተዘራውን ሰብል ያበስለዋል፡፡ በዚህም ገበሬዎቹ ደስ ይሰኙበታል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ መንፈሳዊ ብስለትን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ልክ በደቡብ እንደሚነፍሰውና ሰብሎችን እንደሚያበስለው ያለ ተወዳጅ ነፋስ ነው ይላል፡፡
ቀጥሎም ለሐዋርያቱ እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፡፡ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ አስተውሉ በዚህ አንድ ታሪክ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በእሳትም በነፋስም ተመስሎ ሲቀርብ እናገኛለን፡፡ ታዲያ መንፈስ ቅዱስ የተመሰለባቸው ምሳሌዎች መብዛታቸው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዳብራራው የመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ በምልዓት የማይታወቅ መሆኑን ያመለክታል፡፡
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በእሳት መመሰል አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በዕብራውያን መልእክቱ ‹‹አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና›› ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡(ዕብ 12፡29) መንፈስ ቅዱስ በእሳት መመሰሉ፣ ከከርሰ ምድር መዓድናትን የሚያወጣ ባለሙያ ከመሬት ቆፍሮ ያወጣውን መዓድን ከትቢያው የሚለየው በእሳት እንደ ሆነ እንዲሁ፣ መንፈስ ቅዱስም ነፍሳችንን ትቢያ ከተባለ ኃጢአት ሁሉ ለይቶ ያነጻታልና በእሳት ተመሰለ፡፡ ይህንንም በተመለከተ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹የእስራኤልም ብርሃን እንደ እሳት፣ ቅዱሱም እንደ ነበልባል ይሆናል፡፡ እሾኹንና ኩርንችቱን በአንድ ቀን ያቃጥላል›› ሲል ይናገራል።(ኢሳ 10፡17) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በመጽሐፈ ምሥጢሩ ለሐዋርያቱ በሃምሳኛው ቀን በእሳት አምሳል የወረደው መንፈስ ቅዱስ ‹‹ሥጋቸውን ሳይሆን የኃጢአታቸውን እሾኽ አቃጠለ›› በማለት ያመሰጥረዋል፡፡
እነዚያ እንደ እሳት ላንቃ

ፈሉት ልሳኖች ከመታየትም አልፈው በሐዋርያቱ ላይ መቀመጣቸው፣ ደቀ መዛሙርቱ የሚያዩት ነገር ሁሉ ቅዠት ወይም ምናባዊ ሳይሆን እውነተኛ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ መሆኑን እንዲገነዘቡ ነው፡፡ ከዚያም በኋላ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ልጅ በረገጡና አመጽ ወዳድ በነበሩት አይሁድ ቅንዓትና ቁጣ ሲሞላ፣ የሰላም ልጆች በነበሩት ሐዋርያት ግን መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ (በየአቅማቸው) እንደ ሰጣቸው በሌሎች ቋንቋዎች ይናገሩ ጀመር፡፡
እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ፣ ሐዋርያትም ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መስበክ እንደማይችሉ ዐወቀ፡፡ ስለዚህም በሰናዖር ሜዳ የተበተኑትን የዓለምን ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ሰብስቦ ያኖር ዘንድ ቅዱስ መንፈሱን ላከ፡፡ የተላከውም መንፈስ ያለ አንድ ቋንቋ የማይናገረውን የሐዋርያቱን አንደበት በቅጽበት አሰለጠነው። በእውነት እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያለ አስማሪ ማን ነው?!በዚህችም እለት ሐዋርያቱ በዓለም ሁሉ ቋንቋዎች ተሞልተው ከእርሷ የወጡባት የጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) እንደ ምን ያለች ናት?! መንፈስ ቅዱስ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ታይታ የማትታወቅ ልዩ ትምህርት ቤት አደረጋት፡፡
ሐዋርያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተሟሙቀው በሰበኩት በመጀመሪያ ዕለት ስበከት ብዙዎችን አሳምነው አጠመቁ። በዚህ የመከር በዓል አይሁድ ከአዲሱ እህል ለእግዚአብሔር ቁርባን ሲያቀርቡ፣ ሐዋርያቱ ግን የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለሐዲሲቷ ቤተ ክርስቲያን ከእህል ቁርባን ይልቅ የሚወደዱ ምዕመናንን ስጦታ አድርገው አቀረቡ። በአይሁድ የመከር በዓል ቀን በሐዋርያቱ በተሰጠ ትምህርት የእግዚአብሔር እርሻ የሆኑ ምዕመናን በዝተው አብበው ተገኙ። እውነትም የመከር በዓል!!!